Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, December 31, 2012

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከአገር መባረር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው

http://ethiopia.ecadf.netdna-cdn.com/Amharic/wp-content/uploads/2012/12/gubaye-ethiopian-orthodox-300x224.jpg?84cd58
ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከብፁዓን አበው ጋር
ሐራ ዘተዋሕዶ

  • ሊቀ ካህናት ለጉባኤው መግለጫ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለሰዓታት ጫና ተደርጎባቸዋል
  • ‹‹አጀንዳዬ ሃይማኖታዊ ነው፤ የሠራኹት ስሕተት ይኹን የምጠይቀው ይቅርታ የለም !!››
  • የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል
  • መንግሥት በወሰደው ርምጃ የመንበረ ፕትርክና ዓላሚዎቹ ጳጳሳት እጅ እንዳለበት ታምኖበታል
 በተወሰኑ ጳጳሳት ግፊትና በመንግሥት የደኅንነት ኀይሎች ርምጃ ትላንት ምሽት ከኢትዮጵያ ተገደው እንዲወጡ የተደረጉት ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከጥቂት ሰዓታት በፊት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ደርሰዋል፤ በሰላምና አንድነት ጉባኤው አባልም አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡ 

ቅዱስ ሲኖዶሱ የማን ነው? የእኛ ነው ወይስ?

(ከመልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ/ PDF)፦ እንግዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ከችግራችን ጋር ተወልዶ፥ ያደገው መንግሥት ፥ አቋሙን በግልጽ አሳውቆናል።  “ነገ ልትዳሪ ነው ሲሏት፥ ካልታዘልኩ አላምንም እንዳለችው ሙሽራ መሆኑ ይብቃን፥ እርማችንን እናውጣ። ስለ ነገ እናስብ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን እናስብ፥ ስለ አባቶቻችን እናስብ። የግዴታ ማክሰኞን መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም።
 
ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪው ማክሰኞ  በሚያደርገው ስብሰባ ላይ፥ ካስታወሰን መልዕክታችንን መነጋገር ያለብን፥ ዛሬንና ነገ ብቻ ነው። የመንግሥትን አቋም ባይገርመንም የሚጠበቅ ስለሆነ ሰምተነዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ግን ማክሰኞ ይለይለታል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማነው ወይ የኛ የኦርቶዶክስያዊያኑ ነው! አለበለዚያ፥ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመንግሥት ነው። እንደኔ እንደኔ  የቅዱስ ሲኖዶስም ቢሆን፥ ግልጽ ይመስለኛል።  ይህንን ለመረዳት፥ ወደ ፊት ሁለት ቀን ጠብቆ ማየት ሳይሆን፥ ወደ ላ ብዙ ዓመታትን ማስታወስ ይበቃል። 

Sunday, December 30, 2012

ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው

በዮሐንስ አንበርብር, Ethiopian reporter
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱትን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ጁነዲን በፓርላማ የሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ሊጠየቁበት የሚችል የሕግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል፣ በምክር ቤት አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ምክር ቤቱ እንዲያነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ በመንግሥት ቀርቧል፡፡ 

ጥያቄው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ወይም በፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በኩል መቅረብ ያለበት መሆኑን የምክር ቤቱ ደንብ ያዛል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች፣ ጥያቄው በየትኛው አካል መቅረቡን ለመረዳት እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ላይ ሚስጥራዊ ያሉዋቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ

-    የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የኢሕአዴግ ዕጩ ሆነው የተወዳደሩበትን ሰነድ አቀረቡ
-    የምርጫ አስፈጻሚዎች ለኢሕአዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ አለን ይላሉ
-    አንድ ለአምስት አደረጃጀት ለምርጫ ቅስቀሳ እየዋለ ነው በማለት ኮነኑ

በየማነ ናግሽ, Ethiopian reporter
መድረክንና መኢአድን ጨምሮ ዋነኛ ተቃዋሚዎች የተሰባሰቡበት 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ለፓርላማው አፈ ጉባዔ ክስ እንደመሠረቱበት ገልጸው፣ አገኘናቸው ያሉዋቸውን አንዳንድ ሚስጥራዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ፡፡

Monday, December 24, 2012

የኢትዮ ቴሌኮምና የፍራንስ ቴሌኮም ኮንትራት ትላንት ተጠናቀቀ

የቀድሞውን የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ማኔጅመንት በመረከብ ከሁለት ዓመታት ከስድስት ወራት በፊት ኢትዮ ቴሌኮም ብሎ ሥራውን የጀመረው ፍራንስ ቴሌኮም፤ ኮንትራቱን ከትናንት በስቲያ አጠናቀቀ፡፡ ኩባንያው ኮንትራቱን በማጠናቀቁ ቢሰናበትም አራት የሥራ ኃላፊዎች ግን በኮንትራት እንዲቀጥሉ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

Sunday, December 23, 2012

Mesert Mebrate vs Melese Zenawi


፮ኛውን ፓትርያርክ የሚያስመርጥ ኰሚቴ በመሰየሙ ዜና ላይ ብፁዓን አባቶች እየተናገሩ ነው

ኢትዮጵያ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ረቡዕ ታኅሣሥ 10 ቀን 2005 ዓም ፮ኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ የሚያስመርጥ ኰሚቴ መሰየሙን ከአዲስ አበባ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

Saturday, December 22, 2012

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ

 http://www.ginbot7pf.org/wp-content/themes/ducos/js/timthumb.php?src=http://www.ginbot7pf.org/wp-content/uploads/2012/12/GPF-Pict-4.jpg&w=577&h=220


 የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችን በዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን።

የህወሓት የብረት መዳፍ


(ተመስገን ደሳለኝ)
የድህረ-መለስ ዝግመተኛውና መቋጫ ያጣው የፖለቲካ ማዕበል፣ አሁንም አዳዲስ ክስተቶችን ማሳየቱን አላቋረጠም፡፡ ዝነኛው ‹‹የመለስ ራዕይ›› መፈክርም ግንባሩን የታሰበውን ያህል ወደ አንድ ለማሰባሰብ አቅም ያጠረው ይመስላል፡፡ ጥገናዊ ለውጦቹም እንዲሁ አትራፊ መሆን አልቻሉም፡፡ መሀል አራት ኪሎ በሚገኘው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ግድግዳ ላይ የተሰቀለው የመለስ ፎቶም ‹‹ሸምጋይ›› አልሆናቸውም፡፡ 

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ።

ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።”


      (DEC. 21/2012 ታኅሣስ 12/2005 ዓ/ም/ PDF):- በዚህ ታሪካዊ የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተሰይመው የተላኩት ልዑካን በፍጹም መከባበር ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት በስፋት ተወያይተዋል።

Wednesday, December 19, 2012

ሽጉጥ ያስመዘዘ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ

ከዳዊት
Gibi Gebriel Ethiopian Orthodox church
(አንድ አድርገን ታህሳስ 9 2005 ዓ.ም)፡- በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል  ገዳም (በተለምዶ ግቢ ገብርኤል) እየተባለ የሚጠራው የቤተክርስትያን ቅጥር ውስጥ  በምዕመናን እና በገዳሙ አመራሮች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ድንጋይ መወርወሩንና የገዳሙ ገንዘብ ቤት ኃላፊ የሆኑት መምሬ ንጉሴ የታጠቁት ሽጉጥ መምዘዛቸውን በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
ምዕመናኑንና የገዳሙን አመራር ለልዩነት የዳረገው ምክንያት የሰበካ ጉባኤ አባላት አመራረጥ ሂደት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንደ መረጃ ምንጮቻችን በ2003 ዓ.ም ወርሃ መጋቢት በተደረገ ምርጫ ዘጠኝ አባላት ያሉት ሰበካ ጉባኤ የገዳሙንና የሃይማኖቱን ቃለ አዋዲ በጠበቀ መልኩ ወደ ስራ ገብተው ነበር፡፡ ከአዲሱ ሰበካ ጉባኤ በፊት የነበሩት የሰበካ ጉባኤ አባላት የገዳሙን ገንዘብ በመመሳጠር ሲዘርፉ በመቆየታቸው የተነሳ የስራ ዘመናቸውን ሳያጠናቅቁ እንዲሰናበቱ ተደርገው ነበር፡፡

Monday, December 17, 2012

Children for Sale- KRO Brandpunt

KRO Brandpunt documentary about Dutch / Ethiopian Adoptions. Falsified birthcertificates, falsified relinquishments, false information to court, misleading of parents. Watch the video on Children for Sale-KRO Brandpunt- Part one.

Sunday, December 16, 2012

በማረቃ ወረዳ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ተገደለ

ኢሳት ዜና:- ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም ማንነቱ ያልታወቀው ግለሰብ የተገደለው በወንጀል ተጠርጥሮ ከተያዘ በሁዋላ ነው። ግለሰቡን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ በስም አልታወቀም። ይሁን እንጅ የወረዳው ፖሊስ ግለሰቡ ሊያመልጥ ሲል ተገደለ የሚል ምክንያት መስጠቱን ለማወቅ ተችልኦል።

የተርጫ ዞን የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር አለማየሁ ጦፉ ግድያ መፈጸሙን ባይሸሽጉም ፣ ዝርዝሩን ከስብሰባ እንደወጡ እንደሚሰጡ ቢገልጹም ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ልናገኛቸው አልቻልንም።

በጅጅጋ በዘራችን ብቻ የንግድ ድርጅቶቻችንን ተቀማን በማለት ነዋሪዎች ገለጹ

Jijiga town at night
ኢሳት ዜና:- በሶማሊ ክልል በጅጅጋ ከተማ ተወልደው ያደጉ  በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት በአማራ ክልል በመገኘት የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አክብረው በተመለሱ ማግስት የንግድ ድርጅቶቻችሁን አስረክቡ እንደተባሉ ገልጸዋል።

ቀደም ብሎ ታይዋን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የልብስ እና የተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ ሱቆችን ከፍተው ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች እንደገለጹት፣ መንግስት ሱቆቻቸውን እንዲያስረክቡ ያደረጋቸው ፣ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች የንግድ ድርጅቶችን በብዛት ይዘዋል በሚል ምክንያት ለክልሉ ተወላጆች ለማስረከብ ነው። 

Thursday, December 13, 2012

በሁለት ቀናት ልዩነት ሦስት ጊዜ ቀብሯ የተፈጸመው ወላድ ጉዳይ እያነጋገረ ነው


ቤተልሔም ሰለሞን
- አስከሬኗ ከመቃብር ወጥቶ ተገኝቷል
በታምሩ ጽጌ
የመጀመርያ ልጇን በቀዶ ሕክምና ከተገላገለች በኋላ ደም ፈሷት ሕይወቷ ያለፈው የ27 ዓመት ወጣት የቀብር ሥርዓቷ ባለፈው ቅዳሜ፣ እሑድና ከትናንት በስቲያ ሰኞ የመፈጸሙ ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ 

ሟች ቤተልሔም ሰለሞን ልጅ ወልዳ ለመሳም ዘጠኝ ወራትን ስትጠብቅና የእርግዝናዋንም ሁኔታ ስትከታተል ቆይታ የመውለጃዋ ዕለት በመድረሱ፣ ጎፋ ማዞሪያ ወደሚገኘው ሮያል የጽንስና የማኅፀን ሕክምና ከፍተኛ ክሊኒክ የሄደችው ኅዳር 27 ቀን 2005 ዓ.ም. ነበር፡፡ 

Saturday, December 8, 2012

ቅዱስ ሲኖዶሱ ‘አቡነ መርቆርዮስ ቀደም ሲል በተወሰነላቸው መሠረት መመለስ ይችላሉ’ አለ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ በሰሜን አሜሪካው የሰላምና አንድነት ኰሚቴ አስተናጋጅነት፣ ፫ኛውን እርቀ-ድርድር ባለፈው ረቡዕ ዳላስ፣ ቴክሳስ ውስጥ መጀመራቸው፤ ለዚሁ ውይይት፣ ያዲሳባው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬ ልዑካን፣ የስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬ ልዑካን እየተሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል። ምን ላይ ናቸው? እስካሁን የሰማንው ነገር የለም፣ ደውለን ለማግኘት ያደረግንው ጥረትም አልተሳካም።

Friday, December 7, 2012

የሹም-ሽሩ ምስጢርና ዋናው ጠቅላይ ሚኒስትር!

በሰሎሞን ተሰማ ጂ. (semnaworeq.blogspot.com)
EPRDF's election of three Deputy Prime Ministers1
New appointees

ባለፈው ሐሙስ በተደረገው የኢህአዴግ/ወያኔ የካቢኔ ሹም-ሽር ላይ በርካታ አስተያየቶች በመደመጥ ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም የበርካቶቹ አስተያየትና ትንተና እዚህ ግባ የማይባልና፣ በወያኔዎች አማርኛም “ውኃ የማይቋጥር” ሆኖ ስላገኘሁት፣ የኔን አስተውህሎት ላቀርብ ወደድኩ፡፡ 

በቅድሚያ ግን፣ በሀገር ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ ፖለቲካ ማኅበሮች/ፓርቲዎች መሪዎች እየተቀባበሉ የሚደጋግሙት ነገር ያው የተለመደውን ነው፤ “ሹመቱ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ አይደለም!” ምናምን የሚል ወቀሳ አይሉት ትችት፣ እንዲያው የንፉግና የፈሪ ጩኸት ነው፡፡ 

አስደንጋጭ መረጃዎች ፣- የማዕከላዊ ዘግናኝ ግፎችና ግፈኞቹ

ከዚህ በፊት ታማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮች ባገኘነው መረጃዎች ላይ ተመስርተን ባስነበብናቸው የተለያዩ ዘገባዎች ኮሚቴዎቻችንና ሌሎች ታሳሪ ወንድሞቻችን ላይ በማዕከላዊ የደረሰባቸውን ግፍና ሰቆቃ በመጠኑ ለማስቃኘት ሞክረናል፡፡ 

ዘወትር ሰላምን ሲሰብኩና መቻቻልን ሲያስተምሩ የኖሩትን ኮሚቴዎቻችንንና ዓሊሞቻችንን በግድ የሽብር ድርጊት ልትፈጽሙና ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ስትንቀሳቀሱ እንደነበር የሀሰት ቃል ስጡ በሚል አንድ ኢትዮጵያዊ የራሱ ወገን የሆነ ኢትዮጵያዊ ላይ ያደርሰዋል ተብሎ የማይታሰብ አረመኒያዊ ድርጊት ፈጽመውባቸዋል፡፡

የሰሞኑ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመትና ፖለቲካ

ከዋና ዋና የአፍሪቃ ቀንድ አጥኚዎችና ታዛቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት Rene Lefort የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ “መለስ ከመቃብራቸው እየገዙ ነው። ግን ይህ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ጽሁፍ አውጥተዋል።
 
Rene Lefort ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ኃላፊ ፒተር ሃይን ላይን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሰሞኑን የተሰጠውን ሶስት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ይገመግማሉ። በአስተዳደሩ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች እንደገና የመንግሥቱን ስልጣን እየተቆጣጠሩ ናቸው ያሉትንም ያብራራሉ። ስለሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ዕድገት አሃዝና የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ አንድምታ በተመለከተ አውስተዋል።

Thursday, December 6, 2012

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ደብዳቤ ጻፉ

  •  “የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ” ደብዳቤውን እንዲያውቁት የተባሉት መስሪያ ቤቶች
  •  ከስልጣኔ ውጪ ነው ያደረኩት ፤ በችኮላ የተጻፈ ደብዳቤ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ፤ በስሜትና በችኮላ የሆነ ነገር ነው ፤ ስለ ሰራሁት ስህተት አቡነ ናትናኤል ይቅርታ አድርጌልሃለሁ ብለውኛል” ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ
  •  “ይህ የእናንተ ጉዳይ አይደለም አያገባችሁም” አቃቢ መንበር አቡነ ናትናኤል
(አንድ አድርገን ህዳር 27 2005 ዓ.ም)፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አራተኛ ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ ከነሙሉ ክብራቸውና ማዕረጋቸው ወደቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ የሚጋብዝ ከኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ደብዳቤ መጻፉ ተሰማ፡፡ 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች መካከል ቀኖና ተጣሰ በሚል ምክንያት በሁለቱ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት በሰሜን አሜሪካው የሰላም ኮሚቴው አስተባባሪነት ሶስተኛውን የእርቀ ሰላም ድርድር ረቡዕ ህዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ዳላስ ውስጥ መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ለዚህው እርቀ ሰላም ጉባኤ ከአዲስ አበባው  ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ አባል፣ ፫ኛ/ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ አባል ፬ኛ/ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ በጸሐፊነት  የተወከሉ ሲሆን ከአሜሪካው ሲኖዶስ ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አባል፣ ፫ኛ/ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አባል ፬ኛ/ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በጸሐፊነት ተወክለዋል፡፡ 

Tuesday, December 4, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ የካቢኔ አደረጃጀት እያነጋገረ ነው

 -    ካቢኔው በሕገ መንግሥቱ መሠረት አንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ይኖረዋል
-    የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ያላቸው ሁለት ባለሥልጣናት ተሹመዋል
-    አዲሱ አደረጃጀት ከሌሎች ሕጐች ጋር ተቃርኖ አለው እየተባለ ነው 

በዮሐንስ አንበርብር
የሥራ አስፈጻሚውን ከፍተኛ ሥልጣን በማግኘት አገሪቱን መምራት ከጀመሩ ሁለት ወራት ከቀናት ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ ካቢኔያቸውን በአዲስ መልክ እንዳደራጁ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም መሠረት የሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችንና የሌሎች ሚኒስትሮችን ሹመት አፀድቀዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ የካቢኔ አደረጃጀትም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ካቢኔ) በሕገ መንግሥቱና በመመሥረቻ አዋጁ የተጣለበትን ኃላፊነቶች በብቃት ለመወጣትና የአስፈጻሚነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ለማድረግ፣ እንደ አዲስ በሦስት ዘርፎች መዋቀሩ አስፈላጊ መሆኑን ለፓርላማው አስታውቀዋል፡፡

Saturday, December 1, 2012

አዲሱ የስልጣን ክፍፍልና አመክንዮው: (በዳዊት ተሾመ)

 እንደ መግቢያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን የካቢኒያቸውን ሽግሽግና አዲስ ተሿሚ ሚኒስትሮቻቸውን ትላንት (ህዳር 20፣ 2005 ዓ.ም) በፓርላማ በመገኘት አሹመዋል:: አዲሱ ካቢኔም ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትሮች ሲኖሩት የአራት ሚኒስቴሮችን ሽግሽግም ያካተት ነው:: የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሚኒሰቴር አቶ ጂነዲ ሳዶ ከሃላፊነት በማንሳት በአቶ ሙክታር ከድር ተተክተዋል:: የጤና ጠብቃ እና የንግድ ሚኒስትር ሚኒሰቴር ዲኤታ የነበሩት ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱና አቶ ከበደ ጫኔ  እንደየቅደምተከትል ለሚመሯቸው ተቋሞች ሚኒስቴር ሆነዋል:: የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

Friday, November 30, 2012

የህወሐት ኢህአዴግ የፖለቲካ ጭንቀት

Uten navn
ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል
ትዝብቴን ብገልፅ (ቁጥር 2)     ከአስገደ ገብረስላሴ ወልደሚካኤል (መቀሌ):- ከጠቅላይ ሚንስተር ህመምና ህልፈተ ህይወት ተያይዞ ሃገራችን በወሬና በስብሰባ እየተናጠች እንደ ከረመች ሁሉም ዜጎች የሚያስታውሱት ነው። ለነበሩ ስብሰባዎችም ብዙ ገንዘብ እንደተጠየቀ የቅርብ ትዝብታችን ነው። ያ አልበቃም ብሎ አሁንም ለአንድ ፓርቲ ህወሐት ኢህአዴግ ለማጠናከር ተብሎ 80 ሚልዮን ህዝባችን፣ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ፣ የህወሃት ኢህአዴግ ፓርቲ አባላትና የአጋር ፓርቲዎች አባላት፣ የከተማ የገጠር ህዝቦች በስብሰባ ተጠምደው እየተናጡ ይገኛሉ።

ለዚሁ ለማስረጃነት ያህል ባለፈው ሳምንታት ከ11/02/05 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል በትግራይ ዘኖች ወረዳዎች ከተሞች ተንቀሳቅሼ ነበር። በተንቀሳቀስኩባቸው ቦታዎች ያየሁትና የታዘብኩት ቢኖር በዚህ ፅሑፌ አንድ በአንድ አርእስት በመስጠት ለአንባብያን እንዲደርስ አድርጌላሁ። የትግራይ ህዝብ 100% በግድ የህወሐት ኢህአዴግ አባል ፓርቲ እንዲሆን እየተገደደ ይገኛል።አሁን ግዜው የመኸር ወቅት ሁኖ የገጠር ህዝብ የዘራውን ሰብል ለማጨድና ለመውቃት ሌት ተቀን የሚረባረብበት ሰዓት ነበር። 

Thursday, November 29, 2012

ሰበር ዜና፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 3 ም/ጠቅላይ ሚኒስቴሮችን አስተናገደች፣

Ethiopian Plarliament Playing toys
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና የተለያዩ ድህረገጾች ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ሦሥት ም/ጠቅላይ ሚኒስቴሮች እንደሚኖራቸውና ሃገሪቱንም በቡድን እንደሚመሩዋት መገለጹ የሚታወቅ ነው። ከዚያም ተያይዞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ሁለት ተጨማሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴሮችን እና አንድ ወሳኝና ቁልፍ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርነቱን ቦታ ለህወሓት በማስረከብ አጸድቀዋል። 

Wednesday, November 28, 2012

አምባገነኖችን እንዴት እንታገል?


ከበትረ ያዕቆብ
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው ትልቅ የአመራር ክፍተትና አሁንም ድረስ ውስጥ ውስጡን የቀጠለው የስልጣን ሽኩቻ አምባገነኑን ስርአት ክፉኛ አዳክሞታል፡፡ 

በኢህአዴግ ቤት ውስጥ የተፈጠረው መጠላለፍ እና በጥርጣሬ አይን መተያየት ከውጫዊው ጫና ጋር ተዳምሮ ዛሬ የ21 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረውን አንባገነናዊ ስርዓት ለማስወገድ ከምን ግዜውም በላይ አመቺ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝቡ አገዛዙን ለማስወገድ ለትግል መነሳት እንዳለበት ደግመው ደጋግመው ጥሪ እያስተላልፉ ይገኛሉ፡፡  

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በማንኛውም ማተሚያ ቤት እንዳይታተም መመሪያ ተላለፈ


“ጋዜጣው ቆሻሻ ይዘት ያለውና አመፅ ቀስቃሽ ነው” አቶ ሽመልስ ከማል በሚኒስትር መአረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ም/ሀላፊ  “የአቶ ሽመልሽ ንግግር የወረደ ቢሆንም የማተሚያ ችግሩ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳስተባበሉት እንዳልሆነ በግልፅ ያረጋግጣል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት“  ጋዜጣችን እንዲቋረጥ አቶ ሽመልስ ሊያዙ እንደሚችሉ ቅንጣት አልጠራጠርም” አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት ፓርቲ ም/ህዝብ ግንኙነት ኃላፊና የኤዲቶሪያል ቦርድ አባል “ስራችንን አላቆምንም መረጃዎችን በኦን ላይን ሚዲያ ለማሰራጨት ዝግጅታችንን ጨርሰናል” ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ  

በናዝሬት በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 4 ከንቲባዎች ተቀያየሩ

ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በተደረገ ግምገማ ላለፉት አራት ወራት በስልጣን ላይ ቆይተው የነበሩት የናዝሬት ወይም የአዳማ ዋና ከንቲባ እና ከእኝሁ ባለስልጣን ጋር ግንኙነት አላቻው የተባሉት የከተማዋ የኦህዴድ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርጓል።

ገምጋሚዎቹ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት የነበሩ ሲሆን ግምገማውም በመልካም አስተዳዳር፣ በከተሞች እድገት፣ በኪራይ ሰብሳቢነትና በልማት ሰራዊት አደረጃጃት ላይ ያተኮረ ነበር።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ላለመውሰድ ወሰኑ

ኢሳት ዜና:-በ2005 ዓ.ም ለሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማና የአካባቢ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፓርቲዎች ጋር ለመነጋገር በአዳማ ከተማ ምርጫ ቦርድ በጠራው ስብሰባ ፒቲሽን የተፈራረሙት የ34 ፓርቲዎች ህብረት፤ የምርጫ ችግሮች ሳይፈቱ  የመወዳደሪያ ምልክታቸውን እንደማይወስዱ በአንድ ድምጽ መወሰናቸው ታወቀ፡፡

የዶላር ዋጋ እየወደቀ ነው ተባለ


ኢሳት ዜና:-የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ በ17 በመቶ ጨምሮ በ16.35 ብር እንዲመነዘር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መወሰኑ ይፋ ከተደረገበት መስከረም 2003 ዓ.ም. ወዲህ ባሉት ሁለት ዓመታት፣ የብር ምንዛሪ አቅም እየቀነሰ ከ10 በመቶ በላይ ወርዷል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነው።

በኅዳር 2004 ዓ.ም. የየዕለቱ የውጭ ምንዛሪ ዋጋን በሚያመለክተው መረጃ መሠረት የአንድ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 17 ብር  ከ20 ሳንቲም የነበረ ሲሆን፣ በኅዳር 2005 ዓ.ም. ያለው መረጃ የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ ወደ 18. ብር ከ20 ሳንቲም ከፍ ብሎአል፡፡

ባለፉት 10 አመታት በአዲስ አበባ የተገነባው ከአጼ ሚኒሊክ ጀምሮ ከተገነባው ይበልጣል ሲሉ አቶ ኩማ ደመቅሳ ተናገሩ

ኢሳት ዜና:-ከንቲባው ይህን የተናገሩት  በቅርቡ የአዲስ አበባ 125ኛ አመት ክብረ በአል ሲጠናቀቅ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ነው። አቶ ኩማ ከተማዋን የቆረቆሩትን እና በከተማዋ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉትን በሙሉ በማውገዝ የኢህአዴግን ስራ ለማሞካሸት ሞክረዋል።

በነገሥታቱ ዘመን የከተማዋ የመሬት ይዞታ ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና ለጦር አበጋዞች ተከፋፍሎ አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪዎች ሲሰቃዩ እንደኖሩ፣ የከተማዋ ዕድገት ማስተር ፕላንን ያልተከተለ በመሆኑና በመኳንንቱና በመሳፍንቱ ግላዊ ፍላጐት ተወስኖ ቆይቷል ሲሉ ነው ከንቲባው የገለጹት።

Tuesday, November 27, 2012

በአላማጣ ታፍነው የተወሰዱ ከ20 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም

ኢሳት ዜና:-በራያና አዘቦ ፣ በአላማጣ ከተማ ከኤልክትሪክ መስመር መቃጠል ጋር በተያያዘ በጥርጣሬ የተያዙ ከ20 በላይ ግለሰቦች ወደ ማይጨው ከተማ ተወስደው መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገሩም ፣ ዘመዶቻቸው እንዳይጠይቋቸው በመደረጉ ስለደህንነታቸው ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም።

ወጣቶች የታሰሩት ለኢንቨስተሮች ተብሎ የተዘረጋውን የኤልክትሪክ ምሰሶ አቃጥላችሁዋል በሚል ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ታፍነው የተወሰዱት ወጣቶች በእስር ቤት ጉዳት ሳይደርስባቸው አልቀረም። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

በራስ አሉላ አባነጋ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ዜናዊ ተቀየረ (ከእየሩሳሌም አርአያ)

በትግራይ ተምቤን - አቢይ አዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።

በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።

Thursday, November 22, 2012

የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው

  • የእምዬ ሚኒሊክ ሐውልትም ሊፈርስ ይችላል
Saint Petros monument
(አንድ አድርገን ህዳር 13 2005 ዓ.ም)፡-  የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው ተሾሙ።

Wednesday, November 21, 2012

በዓለማችን የሠራተኞች መብት ከሚጣስባቸው ዋነኛ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ ተገለፀ

ኢሳት ዜና:- ዓለም-አቀፉ የስራ ድርጅት ወይም ILO ኢትዮጵያ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ባግባቡ ከማይከበርባቸው የዓለማችን አገሮች ከዋነኞቹ ረድፍ የምትመደብ መሆኗን አስታወቀ። 

ድርጅቱ ይህንኑ አስመልክቶ ሰሞኑን ያወጣው ሪፖርት እንደሚጠቁመው አርጀንቲና፣ ካምቦዲያ፣ ኢትዮጵያ፣ ፉጂ እና ፔሩ የሰራተኞችን መብት የሚጣስባቸው የዓለማችን አገሮች ናቸው በማለት ይኮንናቸዋል።

ድርጅቱ ለዚህ እንደምሳሌ የጠቀሰው በገዥው ፓርቲ ጣልቃ ገብነት ዳግም የተቋቋመውን ተለጣፊውን የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ሲሆን፣ ማሕበሩ ምንም እንኳን ከአራት ዓመታት በፊት ጀምሮ የILO አባል ለመሆን ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ተለጣፊ ማሕበሩ በመንግስትም ሆነ በግል መምህራን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ለመሆኑ፣ እንዲሁም የመምህራኑን መብት በትክክል ለማስከበር የተቋቋመ ሆኖ ለመገኘቱ ሙሉ ማረጋገጫ ማግኘት ባልመቻሉ የአባልነት ጥያቄው በዓለም አቀፉ ድርጅት ዘንድ እስካሁን ድረስ ተቀባይነት ሊያገኝ አለመቻሉን ገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ ተዘረፈ

ኢሳት ዜና:- በአሁኑ ዝርፊያ ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት አጥቷል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአይቲኤስሲ ላብራቶሪ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ ተዘረፈ፡፡

ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ለሁለተኛ ጊዜ ሰሞኑን የተዘረፈው የ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንስቲትዩቱ ላብራቶሪ እጅግ በጣም ውድ የሆኑ፣ የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች ያካተቱና በብዙ ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ንብረቶቹን አጥቷል።

የመንግስት ጋዜጠኛው የሰራው የዜና ዘገባ ያለርሱ ፈቃድ ተቆራርጦ በቴሌቭዥን መቅረቡን አስታወቀ

ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደውንና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ውይይት አስመልክቶ በስፍራው በመገኘት ያጠናቀረው ፕሮግራም ያለአግባብ ተለውጦ እና ተቆራርጦ ለሕዝብ እንዲቀርብ መደረጉን አስታወቀ።

ሰንደቅ ጋዜጣ ይህንኑ አስመልክቶ ዛሬ እንደዘገበው፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መንገሻ በዋናነት በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት እና በሙስና ችግሮች ላይ ያተኮረውን ይህንኑ የስብሰባ ውሎ እንዲዘግብ ተመድቦ፣ ይህንኑ ውይይት በተመለከተ ከስድስት ደቂቃ በላይ የፈጀ የዜና ዘገባ ቢሰራም፣ ባላወቀው ምክኒያት እርሱ ያጠናቀረው ዜና ወደ ጎን ተትቶ፣ በስብሰባው ላይ በአካል ባልተገኘው ሌላ ባልደረባው የተሰራ ዜና ለሚድያ ፍጆታ መዋሉን አስታውቋል። 

ሰመጉ መንግስት የሚያደርሰውን ዜጎችን የማፈናቀል እርምጃ አወገዘ

ኢሳት ዜና:- የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) ወይም በቀድሞው አጠራሩ ኢሰመጉ “ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚወሰድ ከመሬት የማፈናቀል እርምጃ የዜግነት መብቶችን ማሳጣት የለበትም” በሚል ርዕስ 122ኛውን ልዩ መግለጫ ዛሬ አወጣ፡፡

ሰመጉ በዚህ መግለጫው በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ስላለው መልካም አስተዳደር ችግሮች፣የመብት ጥሰቶችና የሕዝብ ቅሬታ፣የታሰሩ ሰዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ በሰሜን ምስራቅ በኩል 21 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የለገጣፎ/ለገዳዲ ከተማ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ልዩ ዞን ሥር በከተማ አስተዳደርነት እንድትመሰረት ተደርጓል፡፡

Tuesday, November 20, 2012

የመለስ አምልኮ ፪ (ከተመስገን ደሳለኝ)

22 አካባቢ በሚገኘው አክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ከተሰቀለው ግዙፉ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ምስል ስር ‹‹መለስ ኩለ መንኡ ንህዝቢ ዘወፈየ ጂግና ወዲ ህዝብ ኢዩ›› (መለስ ሁለመናውን ለህዝብ የሰጠ ጀግና የህዝብ ልጅ ነው) የሚል የትግርኛ መፈክር ይታያል፡፡ 

በመላ ሀገሪቱ ከተሞችና ገጠሮች የመለስ ፎቶ ያልተሰቀለበት ጉራንጉር ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡ የምንዱባኖች ጠላና ጠጅ ቤቶች እንኳ ሳይቀሩ ‹‹የመለስ ራዕይን እናሳካለን›› የሚል መፈክር ሊወድቅ ባንጋደደ በራቸው ላይ እንዲለጥፉ ተገደዋል፡፡

የሰውየው ሞት በይፋ ከተነገረ ወዲህ የኢህአዴግ አመራርና ካድሬዎች ከፖለቲከኛነት ወደ ‹‹ሀዋርያነት›› ተቀይረዋል፡፡ በየደረሱበት ስለ‹‹መለስ ራዕይ›› ሲቃ እየተናነቃቸው ይሰብካሉ፡፡ ያነበሩት መንግስት የመቀጠሉን አስፈላጊነት በእርሳቸው ስም ለማሳመን ቀን ከሌት እየባተቱ ነው፡፡ አዳዲስ ምእመናኖችንም እያጠመቁ ደቀ-መዛሙርታትን በማብዛቱ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ሰው ዝር በማይልበት ጭው ባለ ምድረ በዳ ሳይቀር ይጮኻሉ ‹‹የመለስን ራዕይ እናሳካለን!››… ከብሔራዊ ቲያትር እስከ ታላቁ ሩጫ ድረስ ያሉ ህዝባዊ መድረኮች የታላቁ መሪ ራዕይ ይዘከርባቸዋል፡፡ 

Monday, November 19, 2012

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ወደ ግብፅ ሊጓዙ ነው

በዮሐንስ አንበርብር
(ሪፖርተር ጋዜጣ) - ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላትን ያካተተ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትን በመወከል፣ ኢትዮጵያ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዓባይ ወንዝ ላይ ምንም ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ለማስረዳት፣ የኢትዮጵያንና የግብፅን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚል ተልዕኮ ይዞ ወደ ግብፅ ሊያቀና ነው፡፡

“መገንጠል ለሚፈልግ ግዜዉ ሲደርስ መገንጠል መብቱ ነዉ” – በረከት ስምኦን

ኢትዮጵያን ነገስታት መርተዋታል፤ ወታደራዊ አምባገነኖች ጨፍረዉባታል፤ ዛሬ ደግሞ ዘረኛ አምባገነኖች ቁም ስቅሏን እያሳዩዋት ነዉ። እቺን ለአስተዋይ መሪዎች ያልታደለች የአስተዋዮች አገር ዛሬ አለም የሚያዉቃት በድህነት፤ በረሀብና በስደት ነዉ። ድህነት፤ ረሀብና ኋላ ቀርነት ኢትዮጵያ ላይ የተደቀኑ ታላላቅ አደጋዎች ቢሆኑም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈራት ድህነትና ረሀብ ሳይሆን ወያኔ በግድ የጫነባት የመገነጣጠል አደጋ ነዉ።

 

በአባቶቻችን የደም መስዋዕትነት ተከብሮ የኖረዉ የኢትዮጵያ አንድነት የሚያሳስባቸዉ ኢትዮጵያዉያን “መገንጠል” የሚሉትን አደጋ ሲሰሙ ልባቸዉ የሚቀልጠዉ ወያኔ ህግ በመንግስቱ ዉስጥ መገንጠል ይቻላል ብሎ ስለጻፈ ብቻ አይደለም። አያሌ ኢትዮጳያዉያንን የሚያሳስባቸዉና የሚያስፈራቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቁልፍ ቁልፉን የስልጣን ቦታዎች ቆንጥጠዉ የያዙት ሰዎች የሚናፍቃቸዉ የኢትዮጵያ አንድነት ሳይሆን የኢትዮጵያ መበታተን በመሆኑ ነዉ። ከእነዚህ የኢትዮጵያን ዉድቀትና መበታተን ከሚመኙ ከሀዲ ሰዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ በረከት ስምኦን ነዉ።

Sunday, November 18, 2012

የኢቲቪ ጋዜጠኞች ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ

በየማነ ናግሽ
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ፍላሚንጎ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ሦስት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጠኞች መኖርያ ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ::

Friday, November 16, 2012

በኦህዴድ ውስጥ የተፈጠረው ችግር እንደቀጠለ ነው

ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ እንደቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የኦሮሞ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት   አሁንም በችግር  እየታመሰ ነው፡

በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱ ተነገረ

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱን ጮህቱም ሰሚ ማጣቱን አንዲት የመንግስት ባለስልጣን ገለጹ። ሥለችግሩ ብናነሳም የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ምን አገባችሁ በሚል መሳለቂያ ያረጉናል ሲሉም ምሬታቸውን ሲገልጹ በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ታይተዋል።

አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያ የመደራጀት መብትን አግዳለች አለ

ኢሳት ዜና:-አለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያን የማህበራትን የመደራጀት ነጻነት ከገደቡ ቀንደኛ 5 ሀገራት አንዶ መሆኖን አስታወቀ።

ጄኔቫ የሚገኘው አለም አቀፉ የሰራተኞች ማህበር ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳስታወቀው የመሰባሰብና የመደራጀት ነጻነት ካፈኑና አደገኛና ፍጹም የሆነ ገደብ የጣሉ ሲል ካወጣቸው 32 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ካምቦዲያ፣ ፊጂ፣ አርጀንቲናና ፔሩ በዋነኝነት አስቅቀምጦቸዋል።

የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ

ኢሳት ዜና:-በሀና  ማሪያም  አካባቢ  መንግስት  የሚያደርገውን  መኖሪያ  ቤቶችን  የማፍረስ ዘመቻ  አስፈፃሚ  የሆኑ  የፌድራል  ፖሊሶች  ህፃን  በናትዋ  ጀርባ  ላይ  እንዳለች  በዱላ  መተው  መግደላቸው  ተዘገበ።

በደራ ወረዳ በአንዲት ሴት ላይ የተፈጸመውን ግፍ በይፋ ያጋለጡት የቀበሌው ሊቀመንበር ቃለምልልስ ሰጡ

ኢሳት ዜና:- በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ ማድረጉን፣ እንዲሁም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ከተደረገ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም ብልቱን እንድትስም ማስደረጉን እንዲሁም  የመንግስት ሹሙ ግለሰቡዋን በእርግጫ በመምታቱ የስድስት ወር ልጅ እንድታስወርድ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።

Thursday, November 15, 2012

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፦ "በንብረት ጉዳይ ዳግም ፍርድ ቤት እንዳልቀርብ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ" አለ

ኢሳት ዜና:- “እኔም ሆንኩ ባለቤቴ በንብረት ውርስ ምክንያት መከራከር አንፈልግም፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት ከዛሬ በኋላ እንዳልቀርብ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ይሰጥልኝ፤” ሲል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፍርድ ቤትን ጠየቀ።

በፈጠራ የሽብርተኝነት ወንጀል ተከሶ የ18 ዓመት እና  ፅኑ እሥራትየተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ዓቃቤ ሕግ እንዲወረስ ስለጠየቀበት ንብረት ቤተሰቡም ሆነ እሱ መከራከር እንደማይፈልጉ ለፍርድ ቤቱ  ያስታወቀው ትናንት ነው።

የ”ጉዞ ኃይለማሪያም” አንድምታ

“ቤተመንግስት ለመግባት፤መለስ ልብ መግባት”

ከጥበቡ ግርማ ሙላቱ
ጥቅምት 10 2005 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው የሪፖርተር ጋዜጣ ልዩ ዕትም ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኋላ ታሪክ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡ የዘገባውን ተኣማኒነት ለማጎልበት ጋዜጣው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቀድሞ የሥራ ባልደረቦችንና ወዳጆች አግኝቶ ለማነጋገር ብዙ የደከመ ይመስላል፡፡ 

የእምዬን ወደ አብዬ ይብቃ ለዴሞክራሲ ያልበቃው ኢህአዴግ ነው!

Sibehat Nega
በቅርቡ የመወያያ አጀንዳ ሆነው ከሰነበቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ የሚጠቀሰው አንድ የህወሓት አንጋፋ ባለስልጣን “የኢትዮጵያ ህዝብ ለዴሞክራሲ ብቁ አይደለም” በማለት ህዝቡን መዝለፋቸውን የሚገልፀው መረጃ ነበር፡፡ እኚህ አንጋፋ ባለስልጣን በተለያዩ ጊዜያት የህወሓት/ኢህአዴግን እኩይ አላማና ፍላጎት ያለአንዳች እፍረት በይፋ በመናገር አነጋጋሪ መሆን ጀምረዋል፡፡

 ሰውየው ሆነብለውም ይሁን አምልጧቸው የሚናገሯቸው ሀሳቦች፣ የአምባገነናዊ ስርዓቱን እኩይ አስተሳሰብ ለአደባባይ እንዲውል የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን አይነት አስተሳሰብ ባላቸው አካላት እየተገዛ እንደሆነ እንዲገነዘብ የሚረዳ ነው፡፡

አምባሳደር ተወልደ ዓጋመ ከፓርቲው ለቀቁ (እየሩሳሌም አርአያ)

የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ (በቅጽል ስማቸው ተወልደ ዓጋመ) በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው እንደለቀቁ ምንጮች አረጋገጡ። ባለፈው በተካሔደው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበው ከማ/ኰሚቴ አባልነት እራሳቸውን እንዳገለሉ አስታውቀዋል።

በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ከ 1993ዓ.ም በሑዋላ ተዛውረው በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ያለሙያቸው ተመድበው ቆይተዋል። በተጨማሪ ባለቤታቸው ሮማን ገ/ስላሴ በፓርቲው ሊ/መንበር « አይኖዋን ማየት አልፈልግም» ተብለው ከፓርቲው ርቀው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰዋል።

Tuesday, November 13, 2012

የሀይንሪኽ በል ድርጅት ከኢትዮጵያ የመውጣት ውሳኔ

መንግሥታዊ ያልሆነው የጀርመናውያኑ የሀይንሪኽ በል ድርጅት ኢትዮጵያን ለቆ እንደሚወጣ እና በአዲስ አበባ የሚገኘውን ጽሕፈት ቤቱንም እስከ ፊታችን ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚዘጋ አስታወቀ። 

በደራ ወረዳ አንዲት ሴት የባሉዋን ብልት በአደባባይ በገመድ እንድትጎትትና እንድትስም ተደረገ

Torturing
ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ አድርገዋል።

የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊውና ፖሊሶች በመቀጠልም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ካስደረጉ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም ብልቱን እንድትስም አስደርገዋል። በእርግጫ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጅ አስወርዳለች። በድርጊቱ አልሳቃችሁም የተባሉትም ተደብድበዋል።

ኢትዮጵያ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አባል ሆና መመረጡዋ ተተቸ

United Nations human right
ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰሞኑን ባካሄደው ምርጫ አስከፊ ሰብአዊ መብቶችን ጥሰት የሚፈጽሙ በርካታ አገሮችን መምረጡ በሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ትችት ቀርቦበታል።

የሰብአዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅቶች እንዳሉት ሰኞ እለት ከተመረጡት 18 አገሮች መካከል መስፈርቱን የሚያሟሉ አገሮች ሶስት ብቻ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ለአፍሪካ 5 መቀመጫዎችን የሰጠ ሲሆን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ኬንያና ሴራሊዮን ለቦታው ተመርጠዋል። ጃፓን ፣ ካዛኪስታን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ፓኪስታንና ዩናይትድ አርብ ኤምሬትስ ደግሞ የኤስያ ፓስፊክ አገሮችን መቀመጫዎች ወስደዋል።