በየማነ ናግሽ
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ፍላሚንጎ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ሦስት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጠኞች መኖርያ ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ::
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ፍላሚንጎ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ሦስት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጠኞች መኖርያ ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ::
ከትናንት በስቲያ ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ የተነሳው ይኼው የእሳት ቃጠሎ መንስዔ ያልታወቀ ሲሆን፣ የሁለት ጋዜጠኞችን ቤትና ንብረት ሙሉ ለሙሉ ሲያወድም የሦስተኛው ጋዜጠኛ ንብረት በከፊል ሊድን ችሏል:: በአጠቃላይ በመቶ ሺዎች ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል::
ጋዜጠኞቹ ደባስ ባይለየኝ፣ በቀለ ተመስገንና ኢትዮጵያ በዲቻ ሲባሉ፣ እሳቱ የተነሳው ብቻውን ከሚኖረው ከኢትዮጵያ በዲቻ ክፍል ነው ተብሏል:: እሳቱ ሦስቱ ጋዜጠኞች የሚኖሩበትን የመንግሥት ቤት ሙሉ ለሙሉ ሲያወድም፣ አጠገቡ ወደሚገኘው አቢሲንያ ሆቴልና ሌሎች ቤቶች እንዳይዛመት በአካባቢ በነበሩ ፖሊሶችና ነዋሪዎች ርብርብ መከላከል መቻሉ ታውቋል::
ቁጥራቸው እስከ ስድስት መቶ የሚገመት ነዋሪዎች ተረባርበው ቃጠሎውን ሲያጠፉ፣ በአካባቢው የሚገኙ ፖሊሶችም ከነዋሪዎች ጋር በመሆን እሳቱን ለማጥፋት ሲንቀሳቀሱ ተመልክተናል:: ነዋሪዎቹንም ምሥጋናቸውን ችረዋቸዋል::
ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ፖሊሶች ቀድመው ሲደርሱ፣ በአካባቢው የሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማና የፌዴራል ፖሊሶችም ተቀላቅለው እሳቱን ለመከላከል ችለዋል:: በቦታው አግኝተን ያነጋገርናቸው ምክትል ሳጅን አንቺአየሁ ብርሃኑና ሳጅን ሱንዱቅ አብዱልቃድር ይህንኑ አረጋግጠውልናል::
ነዋሪዎቹ የእሳት ቃጠሎውን በማጥፋት ላይ ሳሉ ዘግይቶ የደረሱት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኤጀንሲ ሠራተኞች በነዋሪዎቹ ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል:: ስልክ ከተደወለ አንድ ሰዓት ያህል ዘግይተው መድረሳቸው በነዋሪዎች ተነግሯቸዋል:: ፖሊሶችም ይህንኑ አረጋግጠዋል::
ዘግይተው ደረሱ የተባሉት የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በመጥፋት ላይ የነበረውን እሳት ጨርሰው ማጥፋት የቻሉ ሲሆን፣ ይህን ያህል ጊዜ ለምን እንደዘገዩ ላቀረብንላቸው ጥያቄ የመንገድ መዘጋጋትን በምክንያትነት አቅርበዋል::
ፖሊሶቹ ግን ከዚህ በፊትም በአካባቢው ተመሳሳይ አደጋ ደርሶም ዘግይተው መድረሳቸውን ተናግረዋል:: በየአካባቢው የእሳት አደጋ መከላከል ጣቢያ እንዲኖር ሲያስቡ የነበሩ አንዳንድ ነዋሪዎች፣ ‹‹የሠፈሩ ሰው ባይኖር’ኮ አልቀናል ነው የሚባለው›› ሲሉ ቅሬታቸውን ለድርጅቱ ሠራተኞች አቅርበዋል::
No comments:
Post a Comment