የፍትህ
ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ይታወቃል። በቀረበበትም እለት
በርካታ አድናቂዎቹ እና የፍትህ ጋዜጣ አንባቢ ወዳጆች ፍርድ ቤቱን አጨናነቀውት የነበረ ቢሆንም ዳኛ አልተሟላም
በሚል ሰበብ ለዛሬ ነሐሴ 16/2004 ዓ.ም ተቀጥሮ ነበር።
በዛሬው እለት የተመስገንን ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛው የተከሰሰበት ወንጀል ዋስትና አያሰጥም በሚል ወደ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንዲወሰድ እና በቀጣይ ነሀሴ 28/ 2004 ዓ.ም እንዲቀርብ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በዛሬው እለት የተመስገንን ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛው የተከሰሰበት ወንጀል ዋስትና አያሰጥም በሚል ወደ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንዲወሰድ እና በቀጣይ ነሀሴ 28/ 2004 ዓ.ም እንዲቀርብ ቀጠሮ ሰጥቷል።