ኢሳት ዜና:-ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ የአቶ መለስ መንግስት ከመላው ዓለም ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተነሱበት ነው። የኢትዮጵያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነ አንዷለም አራጌ መዝገብ በሽብርተኝነት በተከሰሱ 24 ሰዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በ አቶ መለስ መንግስት ላይ ከ ዓለም ዙሪያ ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩ ነው።

በፍርድ ቤቱ ብይን ላይ ተቃውሞ ካሰሙት መካከል አንዱ፤ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ነው።የዩ.ኤስ ስቴት ዲፓርትመንት ፤ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ የኢትዮጵያ ያ ፍርድ ቤት ያሳለፈው የጥፋተኝነት ብይን እጅግ እንደሚያሳስበው በመጥቀስ፤ ውሳኔው በኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር ህግ ይዘት እንዲሁም፤ አገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ዋስትና በሰጠቻቸው፤ በፕሬስ እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አተገባበር ዙሪያ ከባድ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ብሏል።