Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, November 22, 2012

የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው

  • የእምዬ ሚኒሊክ ሐውልትም ሊፈርስ ይችላል
Saint Petros monument
(አንድ አድርገን ህዳር 13 2005 ዓ.ም)፡-  የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው ተሾሙ።

Wednesday, November 21, 2012

በዓለማችን የሠራተኞች መብት ከሚጣስባቸው ዋነኛ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ ተገለፀ

ኢሳት ዜና:- ዓለም-አቀፉ የስራ ድርጅት ወይም ILO ኢትዮጵያ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ባግባቡ ከማይከበርባቸው የዓለማችን አገሮች ከዋነኞቹ ረድፍ የምትመደብ መሆኗን አስታወቀ። 

ድርጅቱ ይህንኑ አስመልክቶ ሰሞኑን ያወጣው ሪፖርት እንደሚጠቁመው አርጀንቲና፣ ካምቦዲያ፣ ኢትዮጵያ፣ ፉጂ እና ፔሩ የሰራተኞችን መብት የሚጣስባቸው የዓለማችን አገሮች ናቸው በማለት ይኮንናቸዋል።

ድርጅቱ ለዚህ እንደምሳሌ የጠቀሰው በገዥው ፓርቲ ጣልቃ ገብነት ዳግም የተቋቋመውን ተለጣፊውን የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ሲሆን፣ ማሕበሩ ምንም እንኳን ከአራት ዓመታት በፊት ጀምሮ የILO አባል ለመሆን ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ተለጣፊ ማሕበሩ በመንግስትም ሆነ በግል መምህራን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ለመሆኑ፣ እንዲሁም የመምህራኑን መብት በትክክል ለማስከበር የተቋቋመ ሆኖ ለመገኘቱ ሙሉ ማረጋገጫ ማግኘት ባልመቻሉ የአባልነት ጥያቄው በዓለም አቀፉ ድርጅት ዘንድ እስካሁን ድረስ ተቀባይነት ሊያገኝ አለመቻሉን ገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ ተዘረፈ

ኢሳት ዜና:- በአሁኑ ዝርፊያ ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት አጥቷል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአይቲኤስሲ ላብራቶሪ ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ ተዘረፈ፡፡

ሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ለሁለተኛ ጊዜ ሰሞኑን የተዘረፈው የ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንስቲትዩቱ ላብራቶሪ እጅግ በጣም ውድ የሆኑ፣ የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች ያካተቱና በብዙ ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ንብረቶቹን አጥቷል።

የመንግስት ጋዜጠኛው የሰራው የዜና ዘገባ ያለርሱ ፈቃድ ተቆራርጦ በቴሌቭዥን መቅረቡን አስታወቀ

ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደውንና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ውይይት አስመልክቶ በስፍራው በመገኘት ያጠናቀረው ፕሮግራም ያለአግባብ ተለውጦ እና ተቆራርጦ ለሕዝብ እንዲቀርብ መደረጉን አስታወቀ።

ሰንደቅ ጋዜጣ ይህንኑ አስመልክቶ ዛሬ እንደዘገበው፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መንገሻ በዋናነት በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት እና በሙስና ችግሮች ላይ ያተኮረውን ይህንኑ የስብሰባ ውሎ እንዲዘግብ ተመድቦ፣ ይህንኑ ውይይት በተመለከተ ከስድስት ደቂቃ በላይ የፈጀ የዜና ዘገባ ቢሰራም፣ ባላወቀው ምክኒያት እርሱ ያጠናቀረው ዜና ወደ ጎን ተትቶ፣ በስብሰባው ላይ በአካል ባልተገኘው ሌላ ባልደረባው የተሰራ ዜና ለሚድያ ፍጆታ መዋሉን አስታውቋል። 

ሰመጉ መንግስት የሚያደርሰውን ዜጎችን የማፈናቀል እርምጃ አወገዘ

ኢሳት ዜና:- የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) ወይም በቀድሞው አጠራሩ ኢሰመጉ “ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚወሰድ ከመሬት የማፈናቀል እርምጃ የዜግነት መብቶችን ማሳጣት የለበትም” በሚል ርዕስ 122ኛውን ልዩ መግለጫ ዛሬ አወጣ፡፡

ሰመጉ በዚህ መግለጫው በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ስላለው መልካም አስተዳደር ችግሮች፣የመብት ጥሰቶችና የሕዝብ ቅሬታ፣የታሰሩ ሰዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ በሰሜን ምስራቅ በኩል 21 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የለገጣፎ/ለገዳዲ ከተማ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ልዩ ዞን ሥር በከተማ አስተዳደርነት እንድትመሰረት ተደርጓል፡፡

Tuesday, November 20, 2012

የመለስ አምልኮ ፪ (ከተመስገን ደሳለኝ)

22 አካባቢ በሚገኘው አክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ከተሰቀለው ግዙፉ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ምስል ስር ‹‹መለስ ኩለ መንኡ ንህዝቢ ዘወፈየ ጂግና ወዲ ህዝብ ኢዩ›› (መለስ ሁለመናውን ለህዝብ የሰጠ ጀግና የህዝብ ልጅ ነው) የሚል የትግርኛ መፈክር ይታያል፡፡ 

በመላ ሀገሪቱ ከተሞችና ገጠሮች የመለስ ፎቶ ያልተሰቀለበት ጉራንጉር ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡ የምንዱባኖች ጠላና ጠጅ ቤቶች እንኳ ሳይቀሩ ‹‹የመለስ ራዕይን እናሳካለን›› የሚል መፈክር ሊወድቅ ባንጋደደ በራቸው ላይ እንዲለጥፉ ተገደዋል፡፡

የሰውየው ሞት በይፋ ከተነገረ ወዲህ የኢህአዴግ አመራርና ካድሬዎች ከፖለቲከኛነት ወደ ‹‹ሀዋርያነት›› ተቀይረዋል፡፡ በየደረሱበት ስለ‹‹መለስ ራዕይ›› ሲቃ እየተናነቃቸው ይሰብካሉ፡፡ ያነበሩት መንግስት የመቀጠሉን አስፈላጊነት በእርሳቸው ስም ለማሳመን ቀን ከሌት እየባተቱ ነው፡፡ አዳዲስ ምእመናኖችንም እያጠመቁ ደቀ-መዛሙርታትን በማብዛቱ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ሰው ዝር በማይልበት ጭው ባለ ምድረ በዳ ሳይቀር ይጮኻሉ ‹‹የመለስን ራዕይ እናሳካለን!››… ከብሔራዊ ቲያትር እስከ ታላቁ ሩጫ ድረስ ያሉ ህዝባዊ መድረኮች የታላቁ መሪ ራዕይ ይዘከርባቸዋል፡፡ 

Monday, November 19, 2012

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ወደ ግብፅ ሊጓዙ ነው

በዮሐንስ አንበርብር
(ሪፖርተር ጋዜጣ) - ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላትን ያካተተ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥትን በመወከል፣ ኢትዮጵያ የምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በዓባይ ወንዝ ላይ ምንም ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ለማስረዳት፣ የኢትዮጵያንና የግብፅን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚል ተልዕኮ ይዞ ወደ ግብፅ ሊያቀና ነው፡፡

“መገንጠል ለሚፈልግ ግዜዉ ሲደርስ መገንጠል መብቱ ነዉ” – በረከት ስምኦን

ኢትዮጵያን ነገስታት መርተዋታል፤ ወታደራዊ አምባገነኖች ጨፍረዉባታል፤ ዛሬ ደግሞ ዘረኛ አምባገነኖች ቁም ስቅሏን እያሳዩዋት ነዉ። እቺን ለአስተዋይ መሪዎች ያልታደለች የአስተዋዮች አገር ዛሬ አለም የሚያዉቃት በድህነት፤ በረሀብና በስደት ነዉ። ድህነት፤ ረሀብና ኋላ ቀርነት ኢትዮጵያ ላይ የተደቀኑ ታላላቅ አደጋዎች ቢሆኑም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈራት ድህነትና ረሀብ ሳይሆን ወያኔ በግድ የጫነባት የመገነጣጠል አደጋ ነዉ።

 

በአባቶቻችን የደም መስዋዕትነት ተከብሮ የኖረዉ የኢትዮጵያ አንድነት የሚያሳስባቸዉ ኢትዮጵያዉያን “መገንጠል” የሚሉትን አደጋ ሲሰሙ ልባቸዉ የሚቀልጠዉ ወያኔ ህግ በመንግስቱ ዉስጥ መገንጠል ይቻላል ብሎ ስለጻፈ ብቻ አይደለም። አያሌ ኢትዮጳያዉያንን የሚያሳስባቸዉና የሚያስፈራቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቁልፍ ቁልፉን የስልጣን ቦታዎች ቆንጥጠዉ የያዙት ሰዎች የሚናፍቃቸዉ የኢትዮጵያ አንድነት ሳይሆን የኢትዮጵያ መበታተን በመሆኑ ነዉ። ከእነዚህ የኢትዮጵያን ዉድቀትና መበታተን ከሚመኙ ከሀዲ ሰዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ በረከት ስምኦን ነዉ።

Sunday, November 18, 2012

የኢቲቪ ጋዜጠኞች ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ

በየማነ ናግሽ
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ፍላሚንጎ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ሦስት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጠኞች መኖርያ ቤትና ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወደመ::