Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, August 10, 2012

የአቶ መለስ መሰወር የስልጣን ሽኩቻና ፍርሀትን ጋርጧል ተባለ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአቶ መለስ ለረጅም ግዜ ከስልጣን መሰወር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻ፤ በአፍሪካው ቀንድ ደግሞ፤ ፍርሀትን እንደፈጠረ ፋይናንሳል ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ ዘገበ።

መንግስት አቶ መለስ ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ቢናገርም፤ የአቶ መለስ ዜናዊ መሰወር ግን የጎሳ ፖለቲካን አደጋዎች እንዲያገጡ በሚያደርግና፤ ስርአቱን ለአደጋ በሚያጋልጥበት መለኩ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻን ጭሯል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።

በደሴ ከተማ ሙስሊሞች ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተጋጩ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የጁመኣን ሶላት ጸሎት ለማድረስ ዛሬ በደሴ አረብገንዳ የተሰባሰቡ ሙስሊሞች ከፖሊስ ጋር ሲጋጩ ውለዋል።

በደሴና አካባቢዋ የሚገኙ ሙስሊሞች አረብገንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ለመስገድ በሚሰባሰቡበት ወቅት፣ በስፍራው ሲጠባበቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በመስጊዱ ጸሎት ማድረስ አይቻልም በማለት መከልከላቸውን ተከትሎ ነው ችግሩ የተፈጠረው።

ገዢው ፓርቲ ህዝብን ያረጋጋሉ የተባሉ ካድሬዎችን ወደ ገጠር አሰማራ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ከፍተኛ የህዝብ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ገዢው ፓርቲ ህዝብን ለማሳመን ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውን ካድሬዎች ወደ ገጠር መላኩ ታውቓል።

የብአዴን ካድሬዎች በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ህዝቡን እንዲያረጋጉ እንዲሁም የህዝቡን ስሜት እንዲያጠኑና ወደ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ተልከዋል። ካድሬዎቹ ህዝቡን ለማሳመን ምን ማለት እንዳለባቸው በትክክል እንደማያውቁ፣ ይልቁንም ራሳቸው ካድሬዎቹ በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።

ኢምሬት ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያውያን እንስቶች በእሳት አደጋ ሞቱ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በኢምሬት አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ የስድስት ሰዎች ሕይወት ሲቀጥፍ፣ ከነኚህም አንደኛዋ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ መሆኗን  “ዘ-ናሽናል” የተሰኘው ድረ ገጽ ዘገበ።

“አጅማን” ከተማ አቅራቢያ “አል-ሃሚድያ” የተሰኘ አካባቢ በሚገኝ ቪላ ውስጥ በድንገት ቤታቸው ውስጥ እሳት መነሳቱን ያዩት እናት፣ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸው የስልክ ጥሪ ያደርጋሉ። ሆኖም በደቂቃዎች ልዩነት ከእሳቱ ይወጣ በነበረው ከፍተኛ ጭስና ንዳድ የተነሳ፣ የ7፣ የ11 እና የ14 ዓመት እድሜ ያላቸው ሴት ልጆቻቸው፣ እንዲሁም የኢንዶኔዥያና የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሁለት የቤት ሰራተኞቻቸውን ጨምሮ እርሳቸውም ሲሞቱ፣ የ15 ዓመት ዕድሜ ያለው ልጃቸው ግን በመስኮት ዘሎ ሕይወቱን ማትረፉ ታውቋል።

ፍትህ ጋዜጣ ዛሬም እንዳትታተም ተከልክላለች

ግራ የገባኝ ግን ጋዜጣዋ የታገደችው በዝግ ችሎት መሆኑ ነው፡፡ እንድትወረስ የተወሰነውም በዝግ ችሎት ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት (በዝግ ችሎት) ሶስት ክስ እንደተመሰረተብኝ በሬዲዮ ሰማሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ዛሬ ከሶስት ጓደኞቼ ጋር ምስ እየበላሁ ሳለ በምግብ ቤቱ የሬዲዮ ፋና ዜና እየተላለፈ ነው፡፡ ዜናው ቀጥሏል፡፡ "የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ሶስት ክሶች ተመሰረቱበት፡፡

ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ስራ ድርጅትም በተመስገን ላይ በቀረቡ ክሶች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሁለተኛ ተከሳሽ ሆነዉ ጉዳያቸዉ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍረድ ቤት 16ተኛ ወንጀል ችሎት ታይቷል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ “የጁነዲን ሳዶን ባለቤት ያሰርኩት በሽብርተኝነት ጥርጥሬ ነው” አለ

ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሁለት ሣምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሽብር ተግባር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረገ ሲል ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ። 
የፌዴራል ፖሊስ የውጪና ሕዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር አበበ ዘሚካኤል ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው በሰጡት ቃለ ምልልስ ወ/ሮ ሃቢባ የተያዙት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር በተያያዘ ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ ከፍ/ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ መሠረት ነው። 

Thursday, August 9, 2012

በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ በእገታው ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ወጣቶች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ታሰሩ በአማራ ክልል የክልሉ ባለስልጣናትን ጨምሮ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪዎች፣ የሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ባለስልጣናትና ሌሎች የክብር እንግዶች ተሰርቶ ያልተጠናቀቀ መንገድ ተረክበዋል በማለት በአካባቢው ነዋሪዎች መታገታቸውን ሰንደቅ ዘገበ።

ከፍተኛ የፖሊስ አዛዦች ሙስሊሙ ማህበረሰብ ህገመንግስቱን ለመናድ ከሞከረ ውጤቱ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠነቀቁ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጀመሩት ተቃውሞ አንድ አመት ሊመላው ጥቂት ወራቶች ብቻ በቀሩበት በዚህ ጊዜ፣ የፖሊስ አዛዦች ተቃውሞው የሚቀጥል ከሆነ የከፋ ጉዳት ይከተላል ብለዋል።

የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ወርቅነህ ገበየሁ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፖሊስ ፕሮግራም ላይ ቀርበው እንደተናገሩት  ፣  ሙስሊሞች ፍላጎታቸውን በሀይል ለመጫን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ርብርብ የማይቆም ከሆነ ውጤቱ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። 

የርዕዮት ዓለሙ መጽሐፍ ምን ይል ይሆን?

 በብዙአየሁ ወንድሙ, Finote netsanet
በፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት 14 ዓመት ጽኑ እስራትና 33ሺ ብር ተፈርዶባት በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቅጣቱ ወደ አምስት ዓመት ጽኑ እስራት ተቀይሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ “የኢህአዴግ ቀይ እስክሪብቶ” የሚል መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ አስመርቃለች፡፡ 

በምረቃው ዕለት ርዕዮት ባትገኝም ወላጆቿ፣ ወንድሞቿ፣ እህቶቿ፣ ጓደኞቿ፣ የሞያ አጋሮቿ፣  አድናቂዎቿና ዘመድ አዝማዶቿ በተገኙበት ባለፈው ቅዳሜ በራስ አምባ ሆቴል በደማቅ ሥነ ሥርዓት የመጽሐፍ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ርዕዮት ዓለሙ “የኢህአዴግ ቀይ እስክሪብቶን” ለመፃፍ ምን አነሳሳት? የመጽሐፉ ይዘትስ ምን ይሆን? ለእስር የበቃችበትን ምክንያት እንዲህ ብላ ነው የገለፀችው፡- “ገዢው ፓርቲ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ጉዳይን የወረቀት ጌጥ ሲያደርገውና ያለ ፍትሀዊ ውድድር ራሱን በ ‹አውራፓርቲ› ነት ሾሞ ስመለከት አዘንኩ፤ ከዚያም ፃፍኩ፡፡

የርዕዮት ዓለሙ መጽሐፍ ከአዟሪዎች ላይ እየተነጠቀ ነው

- ጋዜጠኛዋ በስር ፍርድ ቤት የተወሰነባት የ14 ዓመት እስር እና የ33ሺህ
ቅጣት ወደ 5 ዓመት እስራት ዝቅ ተደርጓል
- መፅሐፏ ባለፈው ቅዳሜ ተመርቋል

ባለፈው ቅዳሜ ለነምርቃት የበቃው የርዕዮት አለሙ መፅሀፍ ከአዟሪዎች እጅ በፖሊሶች እየተነጠቀ መሆኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተሰማሩ መፅሀፍ አዟሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

በተለይ በላናቻና በቦሌ አካባቢ የመፅሀፍ የሚሸጡ ግለሰቦች እንደተናገሩት ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ፖሊሶች የርዕዮትን መፅሀፍ ለይተው በመንጠቅ አባረዋቸዋል፡፡ በ “ሽብርተኝነት” ተከሳ በሦስት ክሶች ጥፋተኛ ከተባለች በኋላ 14 ዓመት እስራትና 33 ሺህ ብር ቅጣት የተፈረደባት ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ በጠየቀቺው ይግባኝ ጥፋተኛ በተባለችበት 1ኛና 3ኛ ክስ ጥፋተኛ ልትባል የሚያስችል ማስረጃ ባለመቅረቡ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ይግባኙን የሰማው ጠ/ፍ/ቤት ወሰነ፡፡ፍ/ቤቱ በሰጠው ውሳኔ በሽብርተኝነት በመሳተፍ እና አመራር በመሰጠት የሚያሰኝ ማስረጃ አለመቅረቡን ጠቅሶ አንድ ሰው አንቀጽ ተጠቅሶ ስለተከሰሰ ብቻ መቀጣት የለበትም በማለት ሁለቱን ክሶች ውድቅ አድርጐታል፡፡ 

ብታምኑም ባታምኑም፤ ፌስ ቡክን በመጠቀማቸው ሰራተኞች ሃርድ እየተሰጣቸው ከስራም እየተባረሩ ነው!

ከዚህ በፊት በፌስ ቡክ የመልዕክት ሳጥኔ ውስጥ አንድ ወዳጄ አላባ አካባቢ ወደ ሶስት የሚጠጉ የመንግስት ሰራተኞች በፌስ ቡክ ላይ ፖለቲካ ነክ ፅሁፍ ለጥፋችኋል ተብለው ከስራ መባረራቸውን ነገሮኝ ነበር። 

እኔ ግን ይሄንን ነገር ከራሳቸው ከተባራሪዎቹ ሰዎች ካልሰማው በስተቀር የመንግስቴን ስም “በከንቱ” አላጎድፍም ብዬ ስልካቸውን እንዲልክልኝ ጠየኩት። (እንዴት ያለሁ ልማታዊ ወገኛ እንደሆንኩ ብቻ ግራ ቀኝ ልብ አድርጉልኝ!) ልጁ ግን ስልካቸውን ፈልጌ ልክልሃለሁ ብሎኝ ሳይልክልኝ ቀረ።  እኔም ያንን ወሬ አላወራም ብዬ ፀጥ አልኩ።

Wednesday, August 8, 2012

አቶ ጁነዲን ከሥልጣናቸው ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ እነ ሚሚ ስብሀቱ ጠየቁ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን  ከሃላፊነታቸው ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ እነሚሚ ስብሀቱ  መንግስትን አሣሰቡ።

“ዛሚ ኤፍ.ኤም “ ተብሎ በሚጠራው  የነሚሚ ስብሀቱ ራዲዮ ጣቢያ በየሳምንቱ አርብ  በሚተላለፈው የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ የተሰኘ ፕሮግራም ላይ መደበኛ ተወያይ የሆኑት የኢቲቪዎቹ መሰረት አታላይ እና ሳሙኤል ፍቅሬ፣ የኢትዮጵያ ፈርስት ድረ-ገጽ አዘጋጅ  ቤን ፣የቀድሞ የኢነጋማ ጸሀፊ የነበረውና  ከማህበሩ ተለያቶ  ወደ መንግስት የገባው  ወንድወሰን ከበደ ባለፈው አርብ ባደረጉት ውይይት መንግስት  የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩን ከሃላፊነታቸው አንስቶ በህግ እንዲጠቃቸው አሣስበዋል።

ጋዜጠኛዋ በምሽት በደህንነቶች ተጠለፈች

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን በሽብርተኝነት ለመክሰስ የወሰነው የኢህአዴግ መንግስት፤ አንዲት ጋዜጠኛን በምሽት  በደህንነቶች በማስጠለፍ  በተመስገን ላይ በሀሰት እንድትመሰክር  ትዕዛዝ እና ማስፈራሪያ መስጠቱን የማዕከላዊ ምንጮቻችን አጋለጡ።

ምንጮቻችን እንዳሉት፤  በአንድ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ የምትሠራ ጋዜጠኛ  ባለፈው ሐሙስ ምሽት ከቢሮዋ ወጥታ በኮንትራት ታክሲ ወደ ቤቷ በምታመራበት ወቅት  የደህንነት ሀይሎች ታክሲዋን አግተው በመጥለፍ ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ይወስዷታል።

ደህንነቶቹ ጋዜጠኛዋን ወደ ወንጀል ምርመራ ክፍል በማስገባት፦”ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ያለሽን ግንኙነት ደርሰንበታል። ሀጎስ ኪዳኔ የተባለና  ከአልሸባብ ጋር አብሮ የሚሠራ የሻዕቢያ ሰው ከ አልሸባብ በአንቺ በኩል ለተመስገን በርካታ ብር እንደተላከለት ስለመሰከረ እና ይህንንም ተመስገን ስላመነ፤ አንቺም ፍርድ ቤት ቀርበሽ ይህንኑ እንድትመሰክሪ እንጠይቅሻለን” ብለዋታል።

ደህንነቶቹ በማያያዝም፦ ጋዜጠኛዋ ፍርድ ቤት ቀርባ የተባለችውን የማትመሰክር ከሆነ፤እርሷም አብራ ከተመስገን ጋር  እንደምትከሰስ አስፈራርተዋታል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከወር በፊት የላኪ ስም፦”አል ሸባብ “የሚል በሀሰት የተቀነባበረ ደብዳቤ በአድራሻው እንደደረሰው በይፋ ማጋለጡ ይታወሳል።

ከዚያም የላኪ ስም፦”ሐጎስ ኪዳኔ “የሚል ሆኖም  በይዘቱ ቀደም ሲል በአልሸባብ ስም ከተፃፈው ደብዳቤ ጋር ተመሣሳይ የሆነ  የሀሰት ደብዳቤ በድጋሚ እንደደረሰው ይፋ በማድረግ ፤መንግስት እሱንና ፍትህ ጋዜጣን በሀሰት  ለመወንጀል እያቀናበረ ባለው ሴራ በመፍራት  ፍትሕ ጋዜጣ  የአቋም ለውጥ እንደማታደርግ አስታወቀ።

ብዙም ሳይቆይ  ፍትህ ጋዜጣ ታገደች።ጋዜጣዋ በታገደች ከሁለት ሳምንት ብዙም ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ነው የደህንነት ሀይሎች እንስት ጋዜጠኛን በመጥለፍ፦” ተመስገን፤  ሆጎስ ኪዳኔ ከተባለ የሻዕቢያ ሰው ጋር ግንኙነት አለው ብለሽ መስክሪ፤ ባትመሰክሪ አንችም ትታሰሪያለሽ” በማለት እያስፈራሩ ያሉት።

በምሽት ተጠልፋ ማዕከላዊ የተወሰደችው ጋዜጠኛም በቀረበላት ጥያቄ በመደንገጥ “አስብበታለሁ” የሚል ምላሽ መስጠቷን የጠቀሱት ምንጮቻችን፤ ምላሿን እሰከ ዛሬ ጠዋት 3፡00 ድረስ ማዕከላዊ ቀርባ እንድትሰጥ ገደብ እንደተቀመጠላት ጠቁመዋል።

ጋዜጠኛዋ በተመስገን ላይ ከመሰከረች ምንም ችግር እንደማያጋጥማት ቃል የተገባላት ሲሆን፤ ለመመስከር ፈቃደኛ ካልሆነች ግን ክስ ተመስርቶባት ወደ ወህኒ እንደምትወርድ ተነግሯት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደምትገኝ ለማወቅ ተችሏል።

ቀደም ሲልም በተመሳሳይ  የፍትህ አምደኛ  መምህርት ርዕዮት ዓለሙን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀሩ፦ በነፃ መለቀቅ ከፈለገች  በሀሰት እንድትመሰክር እንዳባበሏት፤”ሆኖም ለመመስከር ፈቃደኛ ካልሆንሽ ግን  እስር ቤት  ትበሰብሻታለሽ”ብለው  እንዳስፈራሯት መዘገባችን አይዘነጋም።

ሄላሪ ክሊንተን “ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር  ሄላሪ ክሊንተን በሰሞኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ፦_“ቻይና የአፍሪቃን ሀብት እየዘረፈች ነው” ማለታቸው፤ ቤጅንግን አስቆጣ።

ሰሞኑን ወደ ሰባት የ አፍሪቃ አገሮች ጉዞ ያደረጉት ሄላሪ ክሊንተን በሴኔጋሉ ጉብኝታቸው ባደረጉት ንግግር  የ አፍሪቃ አገሮች ለዲሞክራሲ እና ለ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መረጋገጥ ከመስራት ውጪ አማራጭ እንደሌላቸው  በማሣሰብ፤ሌላ አጋር ፍለጋ  ባልሆነ መንገድ እየሄዱ ያሉት ከዚህ ተጠያቂነትለማምለጥ  እንደሆነ በማብራራት ወቅሰዋል።

Monday, August 6, 2012

ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ የኢትዮጵያ ህዝብ በሃገር ውስጥ እና በውጭ አገር በሚያደርገው ትግል አጋር መሆኑን አስታወቀ።

6 August 2012, ETHSAT NEWS,የኢትዮጵያ ህዝቦች በአገር ውስጥና በውጭ ሃገር በመደራጀት እየታገሉ መሆናቸውን ተገንዝቤያለው ያለው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ ከዚህ የህዝብ አብራክ የወጣ የመከላከያ ሰራዊትም በህቡዕ ተደራጅቶ የትግል አካል ለመሆን መዘጋጀቱን በመግለጫው አስታውቋል::  

የንቅናቄው ቃል አቀባይ ሻምበል ኤፍሬም ተካ ከኢሳት ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መከላከያ የፖሊስና የደህንነት ኃይል በህቡዕ ሲደራጅ መቆየቱን አመልክተው ለትግል ለተዘጋጀው የኢትዮጵያ ህዝብ መከታ ሆኖ ከጎኑ ለመቆም ዝግጅቱን አጠናቋል ብሏል። 

Sunday, August 5, 2012

ትንሽ ወሬ፤ “መለስን ጥራ ሲሉት በረከት መጣ!”

በመጀመሪያ ርዕሱን ቁልብጭ ለማድረግ ብዬ የተከበሩትን ሰዎች አንተ በማለቴ ይቅርታ ጠይቃለሁ። (በቅንፋችንም ካለፉት ጊዜያት ልምድ በመነሳት ባለስልጣኖቻችንን እኔ የተከበሩ ብዬ ስጠራ አንዳንድ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች የተቀበሩ ብለው እንደሚያነቡ ተደርሶበታል።

 ነገር ግን ይህ አግባብ አለመሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ። ምክንያቱም ቀብር ገና ነውና…! የተቀበሩ አይባልም እላለሁ!)ትለንት ቀን ላይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዜና እወጃ “የአቶ መለስ ጤና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ” የሚል ዜና ሰምተን፤ አለቅጥ ተደስተን፣ ልባቸን በሀሴት ሰክራ ዋለች። 

‹‹እኛ ስራችንን ጨርሰናል፤ ከዚህ በኋላ ኃላፊነቱን መወጣት ያለበት ህዝቡ ነው!!››

በፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ: ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ባለፉት ሁለት እትሞች ፍትህ ገበያ ላይ አልዋላችም፣ አንዱ ታትሞ ሲታገድ አንዱ ሳይታተም ነው የታገደው፤ ስትል እንደነበረው የማይታወቅ ቡድን እየከለከለህ ነው? በትክክል የከለከለህ አካል አይታወቅም ብዬ ነው፡፡ በመጀመሪያ የሆነው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሀምሌ 13 ቀን ለምትወጣው ጋዜጣችን ሀምሌ 12 ቀን ለህትመት ስንሄድ ሳንሱር አድርጎ ‹‹አላትምም›› በማለቱ አርብ ዕለት አልወጣችም፡፡

ለምን እንዳላተሙም ሄደን ስንጠይቃቸው የስራ ኃላፊዎቹ የመጀመሪያ ገፅ ላይ ያሉትን ‹‹እነዚህ እነዚህን ዜናዎች ቀይሩ›› አሉን፤ ይህ ሳንሱር መሆኑንና መስሪያ ቤቱ ጽሑፍ ተቀብሎ ከማተም ውጪ የፍርድ ቤት ስራ ሊሰራ እንደማይችል፣ ‹‹ይሄ ያስከስሳል አያስከስምም፣ ይህ ወንጀል ነው አይደለም›› የሚል ስልጣንም እንደሌለው አስረድተን የማተም ግዴታ እንዳለበት ስንነግራቸው ‹‹ተነጋግረን እንወስን›› ብለው ለከሰአት በኋላ ቀጠሮ ሰጥተው አሰናበቱን፡፡ ያው ብርሃንና ሰላምን እንዲህ ሲል በጎን ከሚመራው አካል መመሪያ ለመቀበል እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ሆኖም ከሰዓት በኋላ 8፡30 ስንሄድ ‹‹ይውጣ!›› እያሉ ይማገቱ የነበረበትን ሁኔታ ትተው ጋዜጣዋ እንዲታተም ተፈቀዷል አሉንና ታተመች፡፡