Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Saturday, October 27, 2012
Friday, October 26, 2012
ኢቲቪ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነገረው! .....አቤ ቶክቻው
በመላው ሀገሪቱ ለአረፋ በዓል የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውሟቸውን አሰሙ። ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም (ነጠላ ሰረዝ) ኮሚቴዎቻችን እና ሌሎች
ንፁሐን ይፈቱ (ነጠላ ሰረዝ) ምርጫው ህገወጥ ነው (ነጣላ ሰረዝ) ግድያው ይቁም (አራት ነጥብ) እና በሌላ ነጠላ
ሰረዝ ደግሞ ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን ዎችን ከቢጫ ካርድ ጋር አንግበው ለመንግስት አበርክተውለታል!
Wednesday, October 24, 2012
ሐሙስን ከሚኒስትሩ ጋር!
ዕለቱ ሐሙስ ነው፡፡ ቀኑ ደግሞ ‘08’፡፡ ወርሃ ጥቅምት፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢህአዴግ ግንባር ቀደሞች ተሰብስበናል፡፡ በታሪካዊው የ”FBE” አዳራሽ፡፡ ታሪካዊ ማለቴ ቆራጡ መንጌ የፖለቲከ ርዮት ያጠጣበት የነበረ አዳራሽ በመሆኑ ነው፡፡ ካለመናችሁ ወንበሮቹን እዩአቸው፡፡ መደገፊያዎቹ ላይ “ፖ/ት ይላሉ፡፡ ፖለቲካ ት/ቤት እንደማለት፡፡
በቀኝ እጃቸው ሴቷ ማጭድ ወንዱ መዶሻ ይዘው ግራ እጃቸውን “የሁሉም ሐገር ሠራተኞች ተባበሩ!” የሚል መፈከር ያነገቡ የሚመስል ቅርፅም መግቢያው ላይ አለ፡፡ እናስ ታሪካዊ አይደለም ትላላችሁ?! እኛም ግንባር ቀደሞቹ በዚህ ታሪካዊ አዳራሽ ታሪካዊ ስብሰባ እያደረግን ነው፡፡ ሰብሳቢዎቻችን ደግሞ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም እና የ ዩኒቨርስቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ ናቸው፡፡
መለስ እና የባነር ላይ ታሪኮቹ.......
Meles and his Banner |
አዲስ አበባ አዲሱን ዓመትና መስቀልን የተቀበለቸው በአበቦች አጊጣና በችቦ ደምቃ ሳይሆን የአቶ መለስን ፎቶዎች በያዙ ሰፋፊ ባነሮች ተከፍና ነው፡፡ በመሆኑም 2005 ዓ.ምን ዘመነ ባነር ብየዋለሁ፡፡ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከአቶ መለስ ፎቶ ስር ልዩ ልዩ ጥቅሶች የሰፈሩባቸው ባነሮችን ከየመግቢያና
መውጫ በሮቻቸው ላይ ማንጠልጠላቸው ግዴታ የተጣለባቸው ይመስላል፡፡
አንዳንዶቹማ የብረት አጥሮችን በሙሉ ባነር
ዘርረውባቸው መስሪያ ቤታቸውን የልብስ ማስጫ አስመስለውታል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በህንፃዎቹ ግድግዳ ፖስተሮችን ለጣጥፈው
ጭራሽ ፎቶ ቤት ለመሆን ጥቂት ቀርቷቸዋል፡፡ ኧረ ጋለሪ ሆነዋል ብል ይቀላል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አንስተን ከአንድ
ጓደኛዬ ጋር ስንወያይ “አንደ አጀማመራቸው ከሆነ ከምንበላው እንጀራ ላይም ሳይለጥፉበት አይቀሩም!” ብሎኛል
እየተንገሸገሸ፡፡
ከኦሮሞ ህዝብ ጀርባ...
(ከተመስገን ደሳለኝ)
እንደ መግቢያ
1975 ዓ.ም.፡፡ በመሀል ሀገር የነበረው የፖለቲካ ግለት ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ወደ ጠረፍ እና የገጠር ከተሞች አፈገፈገ፡፡ በ‹‹ምርጥ መኮንኖች›› የተመሰረተው መንግስትም አንፃራዊ ሰላም ያገኘ መሰለ፡፡ አስቀድሞ ‹‹ወታደራዊ ክንፍ›› አቋቁሞ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ለማቀጣጠል ሞክሮት የነበረው አብዮት ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎት ከሸፈ፡፡
1975 ዓ.ም.፡፡ በመሀል ሀገር የነበረው የፖለቲካ ግለት ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ወደ ጠረፍ እና የገጠር ከተሞች አፈገፈገ፡፡ በ‹‹ምርጥ መኮንኖች›› የተመሰረተው መንግስትም አንፃራዊ ሰላም ያገኘ መሰለ፡፡ አስቀድሞ ‹‹ወታደራዊ ክንፍ›› አቋቁሞ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ለማቀጣጠል ሞክሮት የነበረው አብዮት ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎት ከሸፈ፡፡
ለክፉ ቀን ‹‹አማራጬ›› ያለው ወታደራዊ ክንፉም ቢሆን ለሶስት በመከፈሉ በእጅጉ ተዳከመ (ትግል በቃን ብለው ወደ ምዕራብ ሀገራት ለመሰደድ በወሰኑ፣ ኢህአፓን ይዘን እስከመጨረሻው እንፋለማለን ባሉና ‹‹ኢህአፓ ዴሞክራት አይደለም›› በሚል ተገንጥለው ‹‹ኢህዴን›› የተባለ አዲስ ድርጅት በመሰረቱ) ከዚህ በተቃራኒው በመገንጠል እና በብሄር ጥያቄ ዙሪያ የተሰባሰቡት ሻዕቢያ፣ ህወሓት እና በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ የተሻለ ድርጅታዊ አቅም መፍጠር ቻሉ፡፡…በሁለት ወጣት ታጋዮች የሚመራ ከህወሓት የጦር ሰፈር (ደደቢት) የተነሳ አንድ ልኡክ ከኢትዮጵያ መንግስት የመረጃ ሰራተኞች እና የገጠር ካድሬዎች አይን ተሸሽጎ በከፍተኛ ጥንቃቄ ጉዞ ጀምሯል፡፡ መድረሻ ነጥቡ ‹‹ደባዜን›› የተሰኘች ከተማ ነች፡፡
የቃሊቲና ቂሊንጦ ወህኒ ቤቶች ገመና
ከኢንጂባራው ዘላለም
ውድ አንባቢያን፣ ባለፈው ፅሁፌ ላለፉት ዓመታት የገጠሙኝን የእስር ቤት ገመናዎች ከብዙ በጥቂቱ ዋና ዋና ነጥቦችን እንዳስቃኘኋችሁ የሚታወስ ነው፡፡ ስለ ሸዋ ሮቢት ወህኒ ቤት ላስጐበኛችሁ ቃል ገብቼ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ደጋግሜ ሳስበው ስለቃሊቲና ስለ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች ለአንባቢያን ያስተላለፍኩት መልዕክት በቂ መስሎ ስለአልታየኝ እንደገና መፃፉን መረጥኩኝ፡፡
ውድ አንባቢያን፣ ባለፈው ፅሁፌ ላለፉት ዓመታት የገጠሙኝን የእስር ቤት ገመናዎች ከብዙ በጥቂቱ ዋና ዋና ነጥቦችን እንዳስቃኘኋችሁ የሚታወስ ነው፡፡ ስለ ሸዋ ሮቢት ወህኒ ቤት ላስጐበኛችሁ ቃል ገብቼ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ደጋግሜ ሳስበው ስለቃሊቲና ስለ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች ለአንባቢያን ያስተላለፍኩት መልዕክት በቂ መስሎ ስለአልታየኝ እንደገና መፃፉን መረጥኩኝ፡፡
የኢህአዴግ የስህተት ጉዞና የተቃዋሚው ያለመስማማት ጉዞ
ኢህአዴግ ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከዚች ሰዓድረስ ከሰራቸው መልካም ስራ ይልቅ ያጠፋው ጥፋቶች በይበልጥ ጎልተው ይታያሉ፡፡ የሀገሪቱን ህገመንግስት በመጣስም ቢሆን ኢህአዴግ ከሚከሳቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች በበለጠ ደረጃ ራሱ ሲጥስ ይስተዋላል፡፡ ኢህአዴግ ከግልጽነቱ ይልቅ ግልጽነት የጎደለው አሰራሩ ይበልጣል፡፡
ለዚህም አቶ በረከት ስምኦን ስለድርጅቱ ግልጽ አለመሆን በራሳቸው አንደበት ከቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መታመም ጋር ተያይዞ ለህዝብ አለመነገሩ ከድርጅቱ ግልጽነት ማጣት እንደሆነ እንደመልካም ነገር አስረድተዋል፡፡ ኢህአዴግ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር ሞት ጋር በተያያዘ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ለማዳመጥ እንደቻልነው አብዘኛው የተጀመሩትንና የተሰሩትን ሁሉ እርሳቸው መሆናቸውን ሲናገሩ እንደነበረ ሰምተናል፡፡
ኦህዴድ ለአራት ለመሰንጠቅ ጫፍ ደርሷል
ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በተደጋጋሚ ተሰብስቦ መግባባት ያልቻለው ኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ በአራት ቡድን ተከፍሎ ውዝግብ ውስጥ እንደገባ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለፁ፡፡ ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ታማኝ የዜና ምንጮች እንደሚያረጋግጡት ኦህዴድ በአሁኑ ጊዜ በግልጽ ለአራት ቡድኖች ተከፍሏል፡፡
ቡድኖቹ 1ኛ ኦህዴድ- መለስ 2ኛ ኦህዴድ-አባዱላ 3ኛ ኦህዴድ- ኦሮሚያ 4ኛ ኦህዴድ- አድፋጭ በሚል የሚታወቁ ሲሆን፣ የተካረረ ፍጥጫ ውስጥ የመግባት አዝማሚያ ታይቶባቸዋል፡፡ ንጮቻችን እንደሚያስረዱት “ኦህዴድ- ለመለስ” የሚባለው ቡድን ከህውሓት ጋር የቀረበ ግንኙነት ያለውና “ከመለስ ራዕይ ውጪ ምንም ዓይነት ሐሳብና እንቅስቃሴ ማድረግ የለብንም” የሚል ክርክር በማንሳት ኦህዴድ ውስጥ የተጀመረውን የስልጣን ይገባኛል ጥያቄ እንዲጠፋ ጥረት የሚያደርግ ነው፡፡
የእስክንድር ነጋ ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ ለክርክር ተቀጠረ
Eskendir Nega |
ከሰሰበት የሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በ18 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውሳኔውን በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ
ለክርክር ለጥቅምት 27 ቀን 2005 ዓ.ም. ተቀጠረ፡፡
የሥር ፍርድ ቤት ያስተላለፈበትን የጥፋተኝነት ፍርድና የቅጣት ውሳኔ በመቃወም ‹‹ንፁህ ነኝ፣ የቀረበብኝ
ማስረጃ የለም፡፡ ፍርድ ቤቶች የተከበሩ ተቋማት በመሆናቸውና የበቀል፣ የአፈናና የጭቆና መድረክ መሆን ስለሌለባቸው
በነፃ ልለቀቅ፤›› በማለት ነሐሴ 9 ቀን 2004 ዓ.ም. ይግባኝ ማለቱን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው አቤቱታ
ያስረዳል፡፡
Tuesday, October 23, 2012
በገርባ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ ነው
Gerba town killing in South Wollo |
ኢሳት ዜና:-የፌደራል ፖሊስ አባላት 4 ንጸሁን ዜጎችን ፣ ሁለቱን አስረው በመውስድና በመረሸን ሁለቱን ደግሞ
በተቃውሞው ቦታ ላይ ከገደሉ በሁዋላ ፣ ሌሊቱን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በርካታ የገርባ ቀበሌ ወጣቶችን
ማሰራቸው ታውቋል።
ትናንት ምሽት በርካታ ወጣቶች ከተደበቁበት ቦታ በመሆን ስልኮችን ወደ ኢሳት ቢሮ እየደወሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቤቶችን እያስከፈቱ ሲሰፈትሹ እንደነበር ድምጻቸውን ዝቅ በማድረግ ሲናገሩ አምሽተዋል። እስካሁን
ድረስ የታሰሩትን ሰዎች ቁጥር በውል ለመለየት ባይቻልም፣ የ106 ሰዎችን ዝም ዝርዝር የያዙ የፌደራል ፖሊስ
አባላት በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ በአህባሽ አስተምህሮ ተከታይነታቸው ከሚታወቁ ሰዎች ጋር በመሆን ቤቶችን
እየፈተሹ አንዳንድ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል።
የህወሀቱ መስራች አቶ ስብሀት ነጋ፦”የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም” አሉ
Mr. Sibhat Nega |
ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሀት ይህን ያሉት <የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከ አቶ መለስ ሞት በሁዋላ ምን ለውጥ ይኖረዋል?>በሚል ርዕስ ከጀርመን ምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። በበርሊን
በተደረገውና ኢትዮጵያ፤ኬንያ እና ማላዊ ላይ ባነጣጠረው በዚሁ ስብሰባ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት አቶ ስብሀት
ነጋ አቶ መለስ ቢሞቱም ፖሊሲን በተመለከተ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይኖር ተናግረዋል።
<<መለስ አንድ ሰው ነው፤በ አንድ ሰው ሞት የድርጅቱ ዓላማ አይቀየርም፤ስለዚህ በ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል የፖሊሲ ለውጥ አይኖርም” ነው ያሉት አቶ ስብሀት። መንግስታቸው
የደርግ ተከታዮችንና የፊውዳል ርዝራዦችን ለመቆጣጠር ብዙ ዓመታት እንደሠራ የጠቀሱት አቶ
ስብሀት፤<<በደርግ የተበላሸውን የ ኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተማር ብዙ ጊዜ አጥፍተናል>ብለዋል።
የትግራይ ተወላጆች፤ ዘርና ሀይማኖት ላይ ባነጣጠረው የአቶ ስብሀት ንግግር ማዘናቸውን ገለጹ
ኢሳት ዜና:-”አቦይ ስብሃት ፤’ሥልጣን ከአማራውና ከኦርቶዶክሱ በመራቁ ደስ ብሎናል’ሲሉ መናገራቸው አገር ወዳዶቹን የትግራይ ልጆች አሳዝኖናል ሲሉ በሲያትልና አካባቢው የሚኖሩ ተወላጆች ገለጹ። የትግራይ
ተወላጆቹ የ አቶ ስብሀት ነጋን ወደ በርሊን መምጣት በማስመልከት ባወጡት መግለጫ፤ አቶ ስብሀት ገዛ ተጋሩ
በተባለው ፓልቶክ ክፍል ቀርበው ሥልጣን- ከአማራውና ከ ኦርቶዶክሱ በመራቁ ደስ ብሎናል በማለት በመናገራቸው
ምስጢሩ ያልገባቸው አንዳንድ የዋሀንን ቢደሰቱም፤ እኛ አገር ወዳድ የትግራይ ተወላጆች ግን በጣም አዝነናል”ብለዋል።
“ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን
Babimein North Ethiopia |
(በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ) ኤርትራዊ ሆነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት የተሸከሙት አቶ በረከት ስምዖን
በኢትዮጵያ ላይ የሚፈርድ፣ ዜጎችን የሚያሸማቅቅ፣ ለአገራቸው የተሰውትን የሚያናንቅና በተለይም በውድ አገራቸው
የሚመኩ ወገኖችን የሚያኮስስ ንግግር ማድረጋቸው በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ ቅሬታ ማስነሳቱ ታወቀ። አቶ ስዬ
አብርሃ፣አቶ ገብሩ አስራት፣ እነ አቶ ተወልደን በስም በመጥራት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ ያደረጉት አቶ በረከት
“አንድነትና አንድ አገር” የሻዕቢያ መዝሙር መሆኑን በመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠል ለሚፈልጉ ጊዜው ሲደርስ
እንደ ኤርትራ መገንጠል መብታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በሚኒስትር ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት
ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ይህንን የተናገሩት Eritrean Oppositions Arabic Paltalk በሚሰኝ
የኤርትራ ተቃዋሚዎች የፓልቶክ መወያያ ክፍል እንግዳ ሆነው ባካሄዱት የጥያቄና መልስ ነው።
Six Killed Hundreds Injured in Ethiopia as Muslim Protesters Clash with Police
Awramba Times (Addis Ababa) – Atleast Six people have been killed and hundreds wounded in South Wollo on Sunday when members of the federal police clashed with local ordinary Muslims, Awramba Times sources said.
ኢሳት ዜና:- በገርባ የፌደራል ፖሊስ አባላት 2 ሰዎችን ረሸኑ፣ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል :: የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የማቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ይላሉ በአማራ
ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በገርባ ቀበሌ በትናንትናው እለት የወረዳው ፖሊስ አባላት ሆን ብለው በጫሩት ግጭት 4
ሰዎች ሲገደሉ 2ቱ በልዩ ሀይሎች ተወስደው መረሸናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የሙስሊሞች ተቃዉሞና የፖሊሶች ግድያ
Addis Ababa |
በግጭቱ ከተገደሉት አንዱ ፖሊስ መሆኑን አቶ ሽመልስ አስታዉቀዋል።በስልክ ያነጋግርናቸዉ የአይን
ምስክሮች እንደሚሉት ግን ግጭቱ የተፈጠረዉ ገርባ መስጊድና አካባቢዉ ነዉ። ሁለቱን አነጋግረናል።
ኢትዮጵያን የተመለከተ ውይይት በበርሊን
Sibhat Nega |
Sunday, October 21, 2012
ጉዞ ኃይለ ማርያም - ከአረካ እስከ አራት ኪሎ
በዮናስ አብይ
Prime Minister Hailemariam Desalegn |
የ43 ዓመቱ ጐልማሳ መንገሻ መንዳዶ የተወለደባትንና አድጐ የተማረባትን አነስተኛዋን የአረካ ከተማን ለቆ መኖርያውን በአርባ ምንጭ ከተማ ካደረገ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ዛሬ የሥራ ጠባዩ በፈጠረለት አጋጣሚ ሙሉ ጊዜውንና ኑሮውን በአርባ ምንጭ ላይ በመመሥረቱ አልፎ አልፎ
በአዕምሮው ውልብ ከሚሉበት ትዝታዎች በስተቀር ስለተወለደባት የአረካ ከተማ ሲያወሳ አይሰማም፡፡
ነገር ግን
ስለተወለደባት ከተማ ከማይረሳቸው የልጅነት ትውስታዎቹ ውስጥ አንድ አስገራሚ ታሪክን ከተማሪነት ዘመኑ መዝዞ
በፈገግታና ኩራት በተሞላበት ሁኔታ ሲያወጋ፣ ያድማጭን ጆሮ በጉጉት ሊያቆም እንደሚችል በቅድሚያ ከገጽታው ደማቅነት
መረዳት ይቻላል፡፡ የታሪኩ ክስተት ወደኋላ 28 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ 300 ኪሎ ሜትር
በምትርቀው በአረካ ከተማና በነዋሪዎቿ ታላቅ የመደነቅ ስሜትን ስለፈጠረ የአንድ ጎበዝ ተማሪን አስደናቂ ጉዳይ
ያወሳል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)