Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, February 6, 2013

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር በተፈበረከ መረጃ መንግስት ሊያስረው እንደሚፈልግ ገለፀ


“የኢህአዴግ ስርአት መወገድ አለበት፤ ሙሉ ጊዜዬን ለፖለቲካ ስራ በማዋል ስርአቱን ለመታገል ተዘጋጅቻለሁ”ሀብታሙ አያሌው
ethiopian env
ላለፈው አንድ አመት የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ሀብታሙ አያሌው ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል በኢሜልና በስልክ የማያውቃቸው መልዕክቶች እየደረሱት እንደሆነ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡

በፈጠራ መረጃዎች ብዙዎች እንደታሰሩ ያስታወሰው ሀብታሙ ከዚህ መልዕክት ጀርባ በስውር የሚንቀሳቀሱ የመንግስት የደህንነት ሀይሎች እጅ እንዳለበት እንደሚያምን አስረድቷል፡፡ አያይዞም ያለው ስብዕናና ሀይማኖታዊ አስተዳደግ ከሽብርና ጥፋት ሊያቀራርበው እንደማይችል ተናግሯል፡፡

Un forgiveness historical crime committed by Ethiopia regime


 In this week, the Ethiopian Television (ETV) was announcing to release false and fabricated docummentory film called "JIHADAWI HAREKAT" on today. Ethiopian muslims were protesting for more than one year against the regime's interferance in their religious affair. The Ethiopian regime imposing the new Alhabash religion idiology without their will. Different organizations were raising their concern to the Ethiopian government officials that they should stop stirring this flaming issue which can lead decent Ethiopian muslims to fanatic, and following this, 31 Ethiopian muslims reconcilation representatves have been confined in prison and are accused of creating instability and bring slamic state in Ethiopia.

Tuesday, February 5, 2013

በየመን ስደተኛው ላይ ግፉ ቀጥሏል፡፡ ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ ልጆች ሀረጥ IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ

ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በአረብ ሀገር…
በግሩም ተ/ሀይማኖት

ዕለት ከዕለት በየመን ኢትዮጵያዊያን ስደተኛ ላይ የሚሰራው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትና ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ሀገሬ የገቡት በየመን በኩል ነው እና ወደ ሀገራቸው ሳይሆን ወደ የመን ነው የምመልሰው ብሏል፡፡ ማለት ብቻም አይደለ አፍሶ እያመጣ የመን መሬት ቀይ ባህር ዳርቻ እየጣላቸው ነው፡፡ ከሳዑዲ ተመላሾቹን ገንዘብ ይዘዋል፡፡ 

Monday, February 4, 2013

ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው የህወሃት ጀሌ ተጋለጠ

(አዲስ ቮይስ) በጋዜጠኛ አበበ ገላው እና በቤተሰቡ ላይ  ህገወጥ በሆነ መንገድ  በተከታታይ ስልክ በመደወል ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር  የሞከረው ግለሰብ ማንነት ተጋለጠ።

ጋዜጠኛ አበበ ገላው የግለሰቡን ማንነት ለማጣራት ለበርካታ ሳምንታት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትልና ምርመራ መደረጉን  እና ድምጹም  ልምድ ባላቸው የፎረንሲክ ኤክስፐርቶች የተመረመረ መሆኑን ገልጾ በዚሁ መሰረት ይህን ህገወጥ የሆነ ድርጊት ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ ሙሉጌታ ካህሳይ የተባለ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ጀሌ መሆኑእንደተደረሰበት  ገልጿል።

ግለሰቡ በተለይ በአለፈው ወር ላይ ወደ ኢሳት ሬድዮ የአድማጮች መልእክት መቀበያ በመደወል በተለይ ለጋዜጠኛው በተወው መልእክት ደምህን እንጠጣለን እንዲሁምቤተሰቦችህን እንፈጃለን፣ በአዲስ አበባ ያለህን ቤት እናቃጥላለን የሚሉ ሁለት ተከታታይ መልእክቶችን አስቀምጦ እንደነበር ታውቋል።