Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, June 2, 2012

Lives and Land Destroyed: Ethiopia for Sale

 What’s yours is mine; what’s mine’s my own
 By Graham Peebles
It is a colonial phenomenon — appropriate land for the needs of the colonists and to hell with those living upon the land, indigenous and at home. Might is right, military or economic. The power of the dollar rules supreme in a world built upon the acquisition of the material, the perpetuation of desire and the entrapment of the human spirit.

Africa has long been the object of western domination and usury under the British, French, and Portuguese of old. Now the New rulers of the World — large corporations from America, China, Japan, Middle Eastern States, India, and Europe — are engaged in extensive land acquisitions in developing countries. The vast majority of available land is in Sub-Saharan Africa.  The United Nations Permanent Forum on Indigenous Issues  report, “The Growing demand for Land, Risks and Opportunities for Smallholder Farmers,”  states “the amount of land that is potentially available for expanded rain-fed crop production is estimated to be about 2 billion hectares, 80 per cent of which is located in sub-Saharan Africa (especially Western and Central Africa) and in South America”.

Huge industrial agricultural centres are being created, off shore farms, production of crops for the investors’ home market. Indigenous people, subsistence farmers and pastoralists are forced off the land, the natural environment is leveled, purging the land of wildlife and destroying small rural communities that have lived, worked and cared for the land for centuries.

The numbers of people potentially affected by the land grab and its impact on the environment is staggering. The UN, in its report, notes that “by 2020, an estimated 135 million people may be driven from their land as a result of soil degradation, with 60 million in sub-Saharan Africa alone.” This contemporary “land grab” has come about as a result of food shortages, the financial meltdown in 2008, and in light of the United Nations world population forecast of 9.2 billion people by 2050, three main resulting pressures:
1. food insecure nations – particularly Middle Eastern and Asian countries, seeking to stabilise their food supply;
2. to meet the growing worldwide demand for agro-fuels; and,
3. by the rise in investment in land and soft commodities, such as coffee, cocoa, sugar, corn, wheat, soya and fruit.
Often investors are simply speculators seeking to make a fast or indeed slow buck, by ‘land banking,’ sitting on the asset waiting and watching for the price to inflate, then selling.  The Oakland Institute in its report, “The Great Land Grab,” found that “along with hedge funds and speculators, some public universities and pension funds are among those in on the land rush, eyeing returns of 20 to as much as 40%.” Land not as home, but as a chip to be thrown upon the international gambling table of commercialisation.

Chopping trees, cutting costs
As well, we know everything and indeed everyone has its price. Even the people and land of a country, sold into destitution by governments motivated by distorted notions of development, where people, traditional lifestyles and the environment come a distant second to roads, industrialisation and the raping of the land. People too poor to hold on to their dignity, too weak in a world built and run on power and might, to protest and demand justice for themselves and their families and rounded, responsible husbandry for the environment. And the price of land?  Well, as one would expect, bargain basement, with 99 year leases the norm and various government incentive packages. In some cases the land is literally being given away. As the Oakland Institute (OI) states in “The Great Land Grab”:
In Mali one investment group was able to secure 1000,000 hectares (ha) of fertile land for a 50 year term for free. $2.00 a hectare (roughly equal to two Olympic size athletic grounds) is the going rate.
According to The Guardian (March 21, 2011):
The lowest prices are in Africa, where, says the World Bank, at least 35 million hectares of land has been bought or leased. Other groups, including, Friends of the Earth say the figure is higher.
Ethiopia for sale
The Ethiopian government, through the Agricultural Investment Support Directorate, is at the forefront of this African Land Sale. Crops familiar to the area are often grown, such as maize, sesame, sorghum, in addition to wheat and rice, all, let us state clearly, for export to Saudi Arabia, India, China, etc, to be sold within the home market,  benefiting the people of Ethiopia — not.

The Oakland Institute research shows “that at least 3,619,509ha of land (an area just smaller than Belgium) have been transferred to investors, although the actual number may be higher.” The government claims that the land available for lease is unused and surplus.  This is disingenuous nonsense. Large areas of land are, in fact, already cultivated by smallholders subsistence farmers and pastoralists using land for grazing, all of which are unceremonially evicted. Villages are destroyed and indigenous people expelled from their homeland and forced into large scale villagization programmes. Human Rights Watch (HRW) in its report, “Waiting Here For Death,”  states:
The Ethiopian federal government’s current villagization program is occurring in four regions—Gambella, Benishangul-Gumuz, Somali, and Afar. This involves the resettlement of approximately 1.5 million people throughout the lowland areas of the country—500,000 in Somali region, 500,000 in Afar region, 225,000 in Benishangul-Gumuz and 225,000 in Gambella.
Imposed movement then, often applied with force, in order to provide pristine land, free of any inconveniences to the corporate allies.

Level growing field
There are five areas of prime, fertile land up for grabs. Gambella is the largest where unbelievably a third of the region (around 800,000 hectares) is available. Indian corporations have already snapped up 352,000 hectares and around 900 foreign investors have so far taken advantage of this giveaway. Afar, the Southern Nations Nationalities and Peoples Region, where 200,000 hectares has been leased or sold, Oromia, where three Indian companies have leased a total of 138,000 hectares, and Amhara, make up the reduced to clear rail.

With the land grab crucially goes water – and the appropriation of this vital resource, both surface and ground water. Investors are allowed to do what they will with the land they lease.  This includes diverting rivers, digging canals from existing water sources, building dams and drilling bore holes. The Oakland Institute, in its “Land Investment in Ethiopia” report quotes Saudi Star stating “that water will be their biggest issue, and numerous plans are being established (including the construction of 30 km of cement-lined canals and another dam on the Alwero River).” There are no controls imposed on foreign corporations whatsoever and no payment structure for ‘appropriating’ water is in place. These politically favoured investors are being offered carte blanche. Water supplies in Ethiopia are poor, even in the capital, where irregular mains flow is common in many neighbourhoods. There is water galore.  Ninety percent of the Nile flows through Ethiopia.  Distribution, though, is inconsistent.

In Gambella the government in 2011 offered huge areas of land to Bangalore-based food company Karuturi Global for the equivalent of $1.16 per hectare, to lease more than 2,500 sq. km (1,000 sq. miles) of virgin, fertile land for more than 50 years. This cost compared to an average rate of $340 per hectare in the Punjab district of India.  No wonder, then, that the CEO of Karuturi described “the incentives available to the floriculture industry in Ethiopia as ‘mouthwatering,’ including low air freights on the state-owned Ethiopian airlines, tax holidays, hassle-free entry into the industry at very low lease rates, tax holidays, and lack of duties,” (Oakland Institute Report). Up to 60,000 workers will be employed by Karuturi, who are paying local people less than $1 a day, which is well below the level of extreme poverty set by the World Bank.

According to the Guardian (March 21, 2011) the company will cultivate  “20,000 hectares of oil palm, 15,000 hectares of sugar cane and 40,000 hectares of rice, edible oils and maize and cotton… ‘We could feed a nation here,’” says Karmjeet Sekhon, Karuturi project manager. Land and people for a few rupees, cushioned by a cocktail of sweeteners offered by the Ethiopian government, allowing the decimation of the environment and the destruction of lifestyles – generations old. And in a hurry. The Guardian found:
The [land] concessions are being worked [by Karuturi] at a breakneck pace, with giant tractors and heavy machinery clearing trees, draining swamps and ploughing the land in time to catch the next growing season. Forests across hundreds of square km are being clear-felled and burned to the dismay of locals and environmentalists concerned about the fate of the region’s rich wildlife.
Unstable supply of staples
Around five million people in Ethiopia rely on food aid and live with constant food insecurity that will only increase under the land grab bonanza. According to the Oakland Institute’s report, “commercial investment will increase rates of food insecurity in the vicinity of the land investments” and Open Democracy reports an interview with Ethiopia’s Prime Minister Meles Zenawi, for the Financial Times (August 7, 2008), in which he predicted that “large-scale farming could bring some employment, but not much. It would not solve the problem of food insecurity.”

Intensifying food insecurity is the transfer of vast areas of land used for the cultivation of traditional staples such as Teff and other crops. This is largely responsible for costs of Teff (used to make injera – the daily bread) quadrupling in the last four years. The Guardian (April 23, 2012) reports Friends of the Earth International:  ”The result (of land sell offs) has often been … people forced off land they have traditionally farmed for generations, more rural poverty and greater risk of food shortages.” Food security will be realised when local smallholders are encouraged to farm their land, given financial support, machinery and the needed technology.  As Oxfam in its report, “Land Power Rights,” points out, “Small-scale producers, particularly women, can indeed play a crucial role in poverty reduction and food security. But to do so, they need investment in infrastructure, markets, processing, storage, extension, and research.” Keep development small, for, of, and close to the people in need, and see them flourish.

Land rights, human cost, environmental damage
The land rights of the Indigenous people of Ethiopia are, as one would expect, somewhat ambiguous. As a legacy of the socialist dictatorship of the 1960s and ’70s, the government technically owns all land. However, there is protection in law for indigenous people. The Ethiopian constitution
Article 40, 3 states:
Land is a common property of the Nations, Nationalities and Peoples of Ethiopia and shall not be subject to sale or to other means of exchange.
And 4:
Ethiopian peasants have right to obtain land without payment and the protection against eviction from their possession.
With respect to pastoralists affected by the land sell off, paragraph 5:
Ethiopian pastoralists have the right to free land for grazing and cultivation as well as the right not to be displaced from their own lands.
The UN Declaration on the Rights of Indigenous Peoples, which Ethiopia signed in 2007, making it a legally binding document, states in Article 26/1:
Indigenous peoples have the right to the lands, territories and resources, which they have traditionally owned, occupied or other- wise used or acquired.
And paragraph 2:
Indigenous peoples have the right to own, use, develop and control the lands, territories and resources that they possess by reason of traditional ownership or other traditional occupation or use, as well as those which they have otherwise acquired.
The declaration also outlines compensation measures for landowners, Article 28/1:
Indigenous peoples have the right to redress, by means that can include restitution or, when this is not possible, just, fair and equitable compensation, for the lands, territories and resources which they have traditionally owned or otherwise occupied or used, and which have been confiscated, taken, occupied, used or damaged without their free, prior and informed consent.
And Paragraph 2:
Unless otherwise freely agreed upon by the peoples concerned, compensation shall take the form of lands, territories and resources 10equal in quality, size and legal status or of monetary compensation or other appropriate redress.
The law, it would appear, is clear.  Implementation and respect for its content is required, and should be demanded of the ruling EPRDF by the donor countries to Ethiopia.
Land and People
People are not being consulted or democratically included in the decisions to transform their homeland. This contravenes the Ethiopian constitution, that states in Article 92/3:
People have the right to full consultation and to the expression of views in the planning and implementations of environmental policies and projects that affect them directly.
Hollow words to those being evicted from their land, like Omot Ochan a villager from the Anuak tribe whose family has lived in the forest near the Baro river in Gambella for ten generations. Speaking to The Observer (20 May 2012), he “insisted Saudi Star had no right to be in his forest. The company had not even told the villagers that it was going to dig a canal across their land. Nobody came to tell us what was happening.” He goes on to say, “This land belonged to our father. All round here is ours. For two days’ walk.”

Well, that was the case until the Government in their infallible wisdom leased some 10,000 hectares to their friend, the Ethiopian born Saudi Arabian oil multi millionaire, Sheik Al Moudi, (In 2011, Fortune magazine put his wealth at more than $12bn) to grow rice for his Saudi Star Company. Omot continued, “Two years ago, the company began chopping down the forest and the bees went away. The bees need thick forest. We used to sell honey. We used to hunt with dogs too. But after the farm came, the animals here disappeared. Now we only have fish to sell.” And with the company draining the wetlands, the fish will probably be gone soon too. Sheik Al Moudi plans to export over a million tonnes of rice a year to Saudi Arabia. To ease relations with the Meles regime and as The Observer states, “to smooth the wheels of commerce, Amoudi has recruited one of Zenawi’s former ministers, Haile Assegdie, as chief executive of Saudi Star.”

Traditional land rights for people who have lived on the land in Gamabella and elsewhere for centuries are being ignored and in a country where all manner of human rights are routinely violated, legally binding compensations are not being paid. Government drafted lease agreements with investors state the Meles regime will hand over the land free of any ‘encumbrances’ – people and property; anyone living or using the land to graze their livestock or pastoralists moving through. 

The Independent (January 18, 2012) reports:  “Ethiopia is forcing tens of thousands of people off their land so it can lease it to foreign investors, leaving former landowners destitute and in some cases starving.” The Government says any movement is voluntary and not enforced, a clear distortion of the facts. HRW confirms the government’s criminality:  “… mass displacement to make way for commercial agriculture in the absence of a proper legal process contravenes Ethiopia’s constitution and violates the rights of indigenous peoples under international law.”

A price worth paying, it would seem, to the Ethiopian government and those multi-nationals appropriating the land, seeing a market and capitalizing on the country’s need for dollars. Desperate in a world propelled by growth to maximize the value of every so called asset, even if it means prostituting the land, sacrificing the native people and destroying the natural environment.

Graham Peebles is Director of The Create Trust, a UK registered charity. He worked in the West Bank in 2009, running a series of education workshops for Palestinian children. He can be reached at: graham@thecreatetrust.org. Read other articles by Graham.

ኢትዮጵያዊው የረዥም ርቀት ሯጭ በድራግ ምክንያት ታገደ

ኢሳት ዜና:-
በሌላ በኩል በሮም በተካሄደው የ 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ፋንቱ ማንጌሶ በአስደናቂ  ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ በተመልካቾችና በኮሜንታሮች ዘንድ ልዩ አድናቆትን  ጭራለች።

እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ  አትሌት ህዝቅያስ ሢሳይ ለሁለት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች የታገደው ባለፈው ዓመት በተካሄደው እና ዘጠነኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት የኒውዮርክ ማራቶን ላይ  ኤሪትሮፖቲን ወይም በምህፃረ-ቃሉ ኢፒኦ ተብሎ የሚጠራቀውን ሀይል ሰጪ ድራግ ወስዶ መሳተፉ በሐኪም ምርመራ በመረጋገጡ ነው።

ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የዩናይትድስቴትስ  የፀረ-ድራግ ግብረ-ሀይል ኤጄንሲ በበኩላቸው፤ሢሳይ  ለስፖርተኞች ክልክል የሆነውን ኢፒኦ የተባለ ንጥረ-ነገር እንደወሰደ ማመኑን እና የተጣለበትን እገዳ በፀጋ መቀበሉን ገልፀዋል።

የ 24 ዓመቱ  ወጣት አትሌት ሢሳይ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ባለፈው ኖቬምበር 6  በኒዮርክ በተካሄደው ማራቶን 9ኛ ሆኖ ካጠናቀቀ በሁዋላ በተደረገለት የደም ምርመራ ነው ኢፒኦ ወስዶ መገኘቱ የተረጋገጠው።

የእገዳው ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ከተመረመረበት ቀን ጀምሮ ሲሆን፤ በኒውዮርኩ ማራቶን ያገኘውም ሆነ ከዚያ በፊት ያስመዘገባቸው ውጤቶች ሁሉ እንደሚሰረዙበት ተገልጿል። በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ታሪክ፤ አንድ ኢትዮጵያዊ አትሌት ለስፖርተኞች የተከለከለን ንጥረ-ነገር  መውሰዱ ሢሰማ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በሌላ በኩል በሮም በተካሄደው የ 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ፋንቱ ማንጌሶ በአስደናቂ ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ በተመልካቾችና በኮሜንታሮች ዘንድ ልዩ አድናቆትን  ጭራለች። ውድድሩ እንደተጀመረ ሩማኒያዊቷ አንድሪያኖቫ ከሁሉም አትሌቶች በፍጥነት ሩጫ ተለይታ መውጣትና  ለጥቂት ዙሮች በረዥም ርቀት ልዩነት  በመምራት ሜዳውን ተቆጣጠረችው።ይሁንና አንድሪያኖቫ  ሩጫዋን አቋርጣ ለመቆም የተገደደችው ውድድሩ ገና ከግማሽ ብዙም ሳያልፍ ነበር።

ውድድሮች ሲጀመር አፈትልኮ በመውጣት በረዥም ርቀት ከመራ በሁዋላ ወደ መሀከል ላይ አቋርጦ የሚወጣው ኢትዮጵያዊ አትሌት በቅፅል ስሙ፦”ሾላ” ተብሎ እንደሚጠራ ይታወቃል።የሮሙን ውድድር በቴሌቪዥን መስኮት የተከታተሉ እና በቲዩቦች የተመለከቱ ኢትዮጵያዊያን፦ አንድሪያኖቫን፦” ሾላ” ሲሏት ተደምጠዋል።

አንድሪያኖቫ አቋርጣ ከወጣች በሁዋላ  በቀሪዎቹ አትሌቶች ፉክክሩ  ቀጠለ። ውድድሩ አንዱ ዙር እሰከሚቀረው ድረስ እጅብ ብለው ሢሮጡ ከነበሩት አትሌቶች መካከል ዕውቋ ከንያዊት አትሌት ፓሜላ ጄሊሞ ተለይታ በመውጣት ወደ ፊት ስትገሰግስ ሁሉም-  ያለ ጥርጥር  የወርቁ ባለቤት እሷ እንደሆነች ገመቱ።

ዓይኖች ሁሉ በጀሊሞ ላይ ባፈጠጡበት ሰዓት አረንጓዴ ቲ-ሸርት በጥቁር ቁምጣ የለበሰች ጠይም አትሌት  እንደተወርዋሪ ኮከብ እየተምዘገዘገች ከሁዋላ ተፈትልካ ወጣች። “ፓሜላ..” እያሉ ስለ ኬንያዊቱ አትሌት ማሸነፍ በእርግጠኝነት እየተቀባቡ ሲያወሩ የነበሩት ኮሜንታተሮች ፦ ”ኢትዮጵያዊቷ ማጊሶ መጣች..ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ…” ማለት ጀመሩ።

ፋንቱ  እየባሰባት መጣች። ፍጥነቷን ጨመረች። ልክ ውድድሩ ሊጠናቀቅ መቶ ሜትር ሲቀር ካሜላን ደርባ በማለፍ እንደ አቦ ሸማኔ ተወነጨፈች።ጋዜጠኞችንም፣ታዳሚዎችንም ባስደነቀ ልዩ ሁኔታ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጀች። ፋንቱ ወድድሩን ያጠናቀቀችው በ 1 ደቂቃ 57. 56 ሰከንድ ሲሆን፤ይህም በኢትዮጵያ የመቶ ሜትር ውድድር ታሪክ የመጀመሪያው ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል። የዓለም ሳይሆን-የኢትዮጵያ ሪከርድ።

ፋንቱ በሮም ይህን  ድል በመቀዳጀቷም፤  በጎልደን ሊግ ውድድር ከኬኒያዊቷ ካሜላ ጋር ተካታለች። ፋንቱን እና ካሜላን በመከተል ሦስተኛ የወጣችው ሩሲያዊቷ ማሪያ ሳቪኖቫ ስትሆን፤የብሪታኒያዋ ኢማ ጃክሰን  ውድድሩን 2፡00 ከ 08 ሰከንድ በማጠናቀቅ 10 ኛ ወጥታለች። በእንግሊዛዊቷ ውጤት ያዘነው ቢቢሲ፦”ጃክሰን ከተወዳዳሪዎቹ  አንድኛቸውን እንኳን ማሸነፍ አልቻለችም ” ብሏል።

በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሁለት የተቃዋሚ ፓርተዎች አባላትን አፍነው ወሰዱ

ኢሳት ዜና:-
የኢሳት የደባርቅ ወኪል ባስተላለፈው መረጃ መሰረት በትናንትናው እለት ቀድሞ የመኢአድ አባል የነበረውና በምርጫ 97 ቅንጅትን፣ በምርጫ 2002 ደግሞ አንድነት ፓርቲን በመወከል ሲንቀሳቀስ የነበረውን አቶ ስለሺ ጥጋቤን አፍነው ወስደውታል።

ግለሰቡ ከተያዘ በሁዋላ ቤቱ ለ2 ሰአታት ሲበረበር እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።  የአቶ ስለሺ ጥጋቤ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደገለጡት፣ ፖሊሶች እና የደህንነት ሰዎች ግለሰቡን አፍነው ወደ አዲስ አበባ ወስደውታል።

በጭልጋ ወረዳ ደግሞ የመኢአድ አደራጅ የሆነው አቶ መለሰ አስሬ ትናንት ቤቱ ሲፈተሽ ከቆየ በሁዋላ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስዷል። ግለሰቦቹ ታፍነው ስለተወሰዱበት ምክንያት እና የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም። አንድነት ፓርቲም ሆነ መንግስት በግለሰቦቹ መታሰር ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የለም።

ይሁን እንጅ ዘጋቢያችን እንደሚለው ከዋልድባ ገዳም እና ከራስ ዳሸን  ጋር በተያያዘ በአካባቢው ከሚታየው ውጥረት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። የደባርቅ ወረዳ ወጣቶች ከዋልድባ፣ ከራስ ደጀን እንደሁም ከመልካም አስተዳዳርና ፍትህ እጦት ጋር በተያያዘ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር በተደጋጋሚ እንደሚላተሙ ይታወቃል።

 የደባርቅ መምህራን የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን በማለት ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው። በጭልጋ ወረዳም እንዲሁም መምህራን የስራ ማቆም እድማ ማድረጋቸው ይታወሳል።

Thursday, May 31, 2012

10ሩ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች

ነብዩ ኃይሉ
አቶ መለስና ጓደኞቻቸው አምባገነን ስርአትን ለመቀየር ነፍጥ አንስተው፣ በጭቆና ላለመኖር ሲሉ በህይወታቸው ተወራርደዋል፤ አላማቸውን ለማሳካት ገድለዋል ሞተዋል፡፡ ድል ቀንቷቸው የዛሬ 21 አመት አምባገነኑን የደርግ ስርአት አስወግደው ምኒሊክ ቤተመንግስት ሲገቡ ኢትዮጵያን በለውጥ ጎዳና ሊመሩ፣ ዴሞክራሲን በማስፈን በሀገሪቱ አዲስ ታሪክ እንዲያኖሩ የሚያስችል ዕድል ነበራቸው ፡፡ አምባገነኑን የኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያምን ደርግ ካስወገዱ በኋላ ግን አምባገነኑን የአቶ መለስ ዜናዊን ስርአት ከማስቀመጥ ባለፈ በግንቦት 20 ድል ታሪክ ሊሰሩ አልቻሉም፡፡ 

ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለበት፣ በተለያዩ ጎራዎች የተሰለፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ዶጋ አመድ አድርጎ ግንቦት 20, 1983 ዓ.ም የተቋጨው ጦርነት አንድን ወታደራዊ አምባገነን መሪ በኃይል በማስወገድ የይምሰል ዴሞክራሲያዊ ስርአትን(pseudo democracy) የገነባ ሲቪል አምባገነን መተካት የተወሰነ ቡድንን ወይም ግለሰቦችን ፖለቲካዊ የበላይነት(hegemony) ለማረጋገጥ ያለመ እንዳልነበር በትጥቅ ትግሉ ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦች ያረጋግጣሉ፡፡ የህወሓት ነባር ታጋይና የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገብሩ አስራት ሰኔ 19,2002 ለወጣችው አዲስ ፕሬስ ጋዜጣ አሞራው ስለተባለ የህወሓት ጀግና ታጋይ ሲያስረዱ ‹‹አሞራው ቀና ብሎ እየተደረገና እየሆነ ያለውን ነገር ቢያይ ይገርመው ነበር›› ካሉ በኋላ የአቶ መለስ መንግስት በአሞራውና በሌሎች ታጋይ ሰማእታት መስዋዕትነት ስልጣን እየነገደ መሆኑን አብራርተዋል፡፡  

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን የያዘበት ተመሳሳይ ወቅት አምባገነናዊ ኮሚኒስት ስርአቶችን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የጀመሩት የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ለውጥ ማምጣታቸውን Carleton UniversityInstitute of European and Russian Studies  አጥኚ የሆኑት ድራጎስ ፖፓ (DRAGOS POPA) ሮሜኒያንና ቡልጋሪያን ነቅሰው ያመላክታሉ፡፡ የባልካን ሀገራትም ሁለት አስርት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ እምርታ ማምጣታቸውን  The democratic transformation of the Balkans በሚል ርዕስ የቀረበው የሮዛ ባልፈር እና ኮሪና ስትራቱላት (Rosa Balfour and Corina Stratulat) ጥናት ያመላክታል፡፡

ጥናቱ የባልካን ሀገራት በአጭር ጊዜያት ውስጥ ሶስት መሰረታዊ ለውጦችን ማስመዝገባቸውን ያስረዳል‹‹ከጦርነት ወደ ሰላም፣ ከኮሚኒዝም የእዝ ኢኮኖሚ ወደ ነፃ ገበያ እንዲሁም ከአንድ ፓርቲ አገዛዝ ወደ መድብለ ዴሞክራሲ ተለውጠዋል›› ይላል፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ባለፉት 21 አመታት የታየውና አሁንም ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለግንቦት 20 ድል የወጣውን  የህይወት ግብር እና በድሉ ማግስት የተገኘውን የግንቦት 20 ፍሬ ስናወራርድ ውጤቱ ኪሳራን የሚያመላክት ነው፡፡ይህ ጽሁፍ በህወሓት በስተመጨረሻም በህወሓት/ኢህአዴግ መሪነት ለ17 አመታት በተደረገው ፅኑ ትግል የተገኘው የግንቦት 20 ድል ሊያመጣ ያልቻላቸውን አስር አንኳር ነጥቦች ይፈትሻል፡፡   

ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ያለመቻሉ
ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ በሂደት ውጤት የሚያስገኝ ጥረት ነው፡፡ ጤናማ ሂደት እስከኖረ ድረስም የግንባታው እድገት አይቀሬ ውጤት ነው፡፡ ዛሬ በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታቸው ምሳሌ የሚሆኑት ሀገራት በቅፅበታዊ ለውጥ/ክስተት ካሉበት ደረጃ ላይ አልደረሱም፡፡ ከ1983 ግንቦት 20 ወዲህ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደት ውስጥ መግባቷን የአቶ መለስ መንግስት ሲናገር ይደመጣል፡፡

ሆኖም ሂደቱ አንዴ ወደ ፊት ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደኋላ ሲንሸራተት ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ ተኮላሽቷል፡፡ ምርጫ ቦርድም ሆነ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ወይም የእንባ ጠባቂ ተቋም በኢህአዴግ ‹‹ሞተር›› የሚንቀሳቀሱ፣ በመንግስት ሳምባ የሚተነፍሱ በህዝብ አመኔታ የሌላቸው የስም ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ናቸው፡፡ የአቶ መለስ መንግስት በ21 አመት የስልጣን ዘመኑ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባት አለመድፈሩ/አለመፈለጉ የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራ ማሳያነው፡፡  
ከተፅዕኖ ነፃ የሆኑ የፍትህ አካላትን መገንባት አለመቻሉ
በኢትዮጵያ ለህግ የሚሰጠው ቦታ ከፍ ያለ ነው፡፡ ህግን የማክበር እና ለፍትህ አካላት አመቴታና ክብር የሚሰጥ ባህላዊ መሠረትም አለ፡፡ ይህ ባህላዊና ሞራላዊ መሠረት በተለይ ከደርግ መንግስት ስልጣን መያዝ በኋላ የመሸርሸር ምልክት ማሳየት ጀመረ፡፡ “የደርግ ሹማምንት በፍትህ አካላት ላይ የተለያዩ ጫናዎችን በማሳደር ፍርድን ለማጣመም ጥረት ያደርጉ ነበር” የሚሉት አቶ አለማየሁ አዱኛ በህግ አማካሪና ጠበቃነት ይሰራሉ፡፡ አቶ አለማየሁ እንደሚሉት ከመንግስት አካላት ጫና ቢኖርም የፍትህ አካላቱ ከነበራቸው ጠንካራ መሠረት አንፃር ነፃነታቸውን ያስደፈሩ አልነበሩም፡፡

ይህ ሁኔታ የደርግ ባለስልጣናት ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ህጋዊ ከለላ ከመስጠት ይልቅ ግልጽ ፖለቲካዊ እርምጃ ይወስዱ ነበር፡፡ የደርግ አምባገነንነትና ጨፍጫፊነት አጠያያቂ ባይሆንም እነዚህ ህገወጥ እርምጃዎች የሚወስዱት በማናለብኝነት በተወጠሩ ባለስልጣናት “የጐበዝ አለቆች” እንጂ በፍትህ አካላት አልነበረም፡፡ ህወሓት /ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ግን ሁሉንም ተቋማት በአንድ የፖለቲካ አስተሳሰብ የማጥመድ አባዜ የፍትህ አካላትንም አልተወም፡፡ ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ እና ፍርድ ቤቶች ከመጋረጃ ጀርባ በኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚሰጡ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን “በህግ” ስም ያስተላልፋሉ፡፡ ኢህአዴግ እራሱ ያፀደቀውን ህገ መንግስት በመጣሱ የፍትህ አካላትን ነፃነት ከመጋፋት ባለፈም፣ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ የሚያደርሱ አፋኝና ኢፍትሀዊ ‹‹ህጐችንም›› በማፅደቅ ፍትህንና ህጋዊ ስርዓትን የሚያዋርዱ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ ግንቦት 20 ነፃ የፍትህ አካላት እንዲለመልሙ አለማድረጉ ሌላው የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራ ነው፡፡
ብሔራዊ ስሜትን መናዱ (ኢትዮጵያዊነትን ማኮሰሱ)
ብሔራዊ ስሜት መናድ ለአንድ ሀገርና በውስጧ ለሚኖሩ ዜጎች ደህንነት አደጋን ይደቅናል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያዊነት የሚንዱና ጎጣዊ ማንነት ላይ የሚያተኩሩ ፖለቲካዊ እሳቤዎችን በህዝቡ ውስጥ እንዲዘሩና እንዲስፋፉ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያን ጥንተ ታሪክ በመካድ ህዝቦች በግድ የተጠፈሩባት ‹‹የአጤ ምኒሊክ ፍጡር›› አድርገው ያስቀምጧታል፡፡ ይህ አስተሳሰብ ህወሓት ስልጣን ላይ ሳይወጣ ያራምደው እንደ ነበር ግልፅ ነው፤(የኤርትራ ህዝብ ትግል ከየት ወዴት 1979ን ልብ ይሏል) የአስተሳሰቡ መነሻ የኢትዮጵያን ጥንተ ታሪክ በመካድ ቢነሳም መጨረሻው የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚል ክፉ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ነው፡፡

 ይህ የፀረ ኢትዮጵያዊነት ውጤት በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን መጀመሪያ ኤርትራን በማስገንጠል ተጀምሮ በ1987ቱ ህገ-መንግስት አንቀፅ 39ን በማካተት መሰረቱን አጠናከረ፡፡ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ በተነሳው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጦስ ከሁለቱም ሀገራት ‹‹ወደ ሀገራቸው› የተሸኙ ዜጎችን ሰቆቃ ለተመለከተ፣ የተሳሰረን ህዝብ ‹‹የራስን እድል በራስ በመወሰን›› ሰበብ መነጠል የሚያመጣውን ስነልቦናዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጦስ ለማገናዘብ አይቸግረውም፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ አደገኛ አስተሳሰቡን ለማረቅ የሚፈልግ አይመስልም፡፡ 

የአቶ መለስ መንግስት አራምዳለሁ ለሚለው ‹‹የልማታዊ መንግስት›› ፍልስፍና ብሔራዊ ስሜት የጎላ ሚና እንዳለው ምሁራን የተለያዩ ሀገራትን ልምድ በመጥቀስ ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ተፋልሶ ውስጥ የሚዋትተው የአቶ መለስ ኢህአዴግ ከኢትዮጵያዊነት ጋር መላተሙ ሌላው የድህረ-ግንቦት 20 ክስረት አመላካች ነው፡፡
የብሔር ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱ
በ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ይስተጋቡ ከነበሩ የፖለቲካ ጥያቄዎች ውስጥ የብሔር ጥያቄ አንደኛው ነው፡፡ ኢህአዴግ ይህን ጥያቄ እንደ ሰንደቅ አንስቶ የብሔረሰቦችን እኩልነት እንዳረጋገጠ ይናገራል፡፡ የብሔር እኩልነት የግንቦት 20 ፍሬ እንደሆነም ደግሞ ደጋግሞ ለማሳመን ጥሯል፡፡ ሆኖም ከግንቦት 20 በኋላም ተገፋን ተጨቆንን የሚሉ የብሔር ቡድኖች በየምክንያቱ ብቅ ብቅ ማለት ቀጥለዋል፡፡ ኢህአዴግ በቋንቋ ከመማርና ከመዳኘት ባለፈ ብሄረሰቦች ራሳቸውን የምር እንዲያስተዳድሩ የሚፈልግ አይመስልም፡፡ 

አቶ ገብሩ አስራትም በኢትዮጵያ የብሔረሰቦች መብት እንዳልተከበረ ያምናሉ፡፡ አቶ ገብሩ ‹‹ህወሓት ከጋርዮሽ አመራር ወደ አንድ ሰው ብቸኛ መሪነት›› በሚለው ፅሁፋቸው ብሔሮች በአካባቢያቸው ጉዳይ ፖለቲካዊ ስልጣን ኖሯቸው እንደማይወስኑና በአካባቢያቸው ኢኮኖሚያዊ ልማት ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ፡፡  ለዚህም ይመስላል ከህወሓትና ከፌደራል መንግስት የሚወከሉ አካላት በክልል አስተዳደሮች ውስጥ ጣልቃ ገብ ተሳትፎ ያላቸው፡፡ 

 በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በቁጥር 39 የተሰራጨው መረጃ እንዳመለከተው ‹‹ኦሮሚያ የምትተዳደረው በክልሉ ም/ቤት በተመረጡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሳይሆን ከህወሓት በተመደቡት አቶ ገ/ተንሳይ ወ/ትንሳይ ነው፡፡›› ይኸው መረጃ አያይዞም ቀደም ሲልም ሰለሞን ጢሞ የተባሉ የህወሓት ሰው ኦሮሚያን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ያስተዳድሯት እንደ ነበር አስታውሷል፡፡ የሌሎች ክልሎች ብሄረሰቦችም ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል እንደሌላቸው ይነገራል፡፡ 

በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብቻ በጭፈራ የሚታየውና በስርአቱ ተቺዎች ዘንድ ‹‹የብሔር ብሄረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› የሚል ስላቅ የሚገለፀው ‹‹እኩልነት›› በፖለቲካው መድረክ አይታይም፡፡ ይህ ሁኔታ ተጨማሪ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራ ሆኗል፡፡  
ፍትሀዊ ያልሆነ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መስፈን (corny capitalism)
የአቶ መለስ መንግስት በ21 አመት የስልጣን ቆይታው ሊያሳካ ካልቻላቸው መሰረታዊ የህዝብ ጥቅሞች መካከል ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አለማረጋገጡ ዋንኛው ነው፡፡ መንግስት በኢኮኖሚ ውስጥ የሚያደርገው የበዛ ጣልቃ ገብነት፣ ኢትዮጵያውያን በኢኮኖሚው ውስጥ ፍትሀዊ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያግዝ እንደሆነ ሹማምንቱ በተለያዩ መድረኮች ከመግለፅ አይታክቱም፡፡ መንግስትም የሚያንቀሳቅሳቸውን ግዙፍ ድርጅቶችም ከእጁ ለማውጣት አይፈልግም፡፡ የበታፈነ ደረጃ የተፈቀደው ‹‹የነፃ ገበያ ስርአት›› ሁሉንም የንግድ ህብረተሰብ ክፍል እኩል ተጠቃሚ አላደረገም፡፡ 

ኢህአዴግ ራሱ ያወጣውን ህግ ተላልፎ የፈለፈላቸው፣ በቢሊየን የሚቆጠር ካፒታል የሚያንቀሳቅሱትን የገዢው ፓርቲ ንብረት የሆኑ ኩባንያዎችን በማጠናከር እንዲሁም ከመንግስቱ ጋር ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች የተለየ ጥቅም የሚያገኙበት ሁኔታ ፈጥሯል፡፡  የዘርፉ ባለሙያዎች ይህንን ስርአት ኮርኒ ካፒታሊዝም (crony capitalism) በሚል ይጠሩታል፡፡ ኮርኒ ካፒታሊዝም የሀገሪቱ ሀብት ከስርአቱ ጋር ስምም ወደ ሆኑ ጥቂት ባለፀጋ ግለሰቦች እንዲፈስ የሚያደርግ ስርአት ነው፡፡ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ኢኮኖሚም ሆነ ቁሳዊ ልማት ጥቂቶችን ብቻ ተጠቃሚ ማድረጉ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች መሀከል የሚጠቀስ ከመሆኑም በላይ አስተዳደሩ ለተዘፈቀበት ሙስና ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው፡፡ 
የሙስና መስፋፋት
ፕሮፌሰር ሰይድ ሐሰን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ትንታኔዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡ እኚህ ምሁር ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደ ስርአት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡በቅርቡ ‹‹ሙስና ኡ!  ኡ! እሪ! እሪ!›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ ዓለም ባንክ ባደረገው ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስና አደገኛ ስርአነት ወደ መሆን መሸጋገሩን ያብራራሉ፡፡ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ፣ ጉምሩክና የገቢዎች ባለስልጣን፣ የወረዳ አስተዳደርና ማዘጋጃ ቤቶች ሙስና በእጅጉ የተንሰራፋባቸው ናቸው፡፡ 

የህወሓት አንጋፋ መሪ የነበሩት አቶ ስብሀት ነጋም ሙስና በሀገሪቱ አደገኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ እንዳሳሰባቸው በይፋ መግለፃቸውና አቶ መለስም የመንግስት አካላትም በአደገኛ ሙስና ዘፈቃቸውን ማመናቸው ሙስና ከድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች መሀከል የሚጠቀስ ሆኗል፡፡                                                                                      
ስርአቱን የሚተቹ አካላትን ማፈን
የህወሓት/ኢህአዴግ ታጋዮች ደርግን ከተዋጉበት ምክንያት አንዱ የደርግ ተቃውሞን የማፈን እርማጃ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ታጋዮቹ ደርግን አስወግደው ሌላ ‹‹ደርግ›› መተካታቸውን የሚያስረዱ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ስርአቱን የሚተቹ አካላትን የአቶ መለስ መንግስት ማሰር የጀመረው በቅርቡ ባይሆንም፣ በአረብ ሀገራት የተከሰተውን መነሳሳት ተከትሎ የተቃውሞ ፖለቲካ አመራሮችንና ጋዜጠኞችን ‹‹በሽብር›› ሰበብ ቃሊቲ አውርዷል፡፡ በይፋም ሆነ በኢመደበኛ ወጎች መንግስትን መተቸት የሚያስጠይቅበት ደረጃ በመድረስ ላይ ይገኛል፡፡ 

መንግስት ስርአቱን የሚተቹ አካላትን ለማሸማቀቅ የሚጠቀምባቸው መንገዶች ሰላማዊ ትግልን የሚያደናቅፉ ከመሆናቸውም በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብሶትና ተቃውሞ ወደ ግብታዊ አብዮት የመምራት ውጤትም ሊያስከትል ይችላል፡፡ በሰላማዊ ትግል ተስፋ ቆርጠው መሳሪያ ያነሱ ቡድኖችን ያበራከተው ይህ አካሄድ፣ ከኢህአዴግ ጋር ልዩነት ያላቸው የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ ትግል እንዲሳተፉ አለማበረታታቱ የአቶ መለስ ስርአት የድህረ-ግንቦት 20 ክስረት አንድ አካል ነው፡፡      
ነፃ የሲቪክ ማህበራት አለመጠናከራቸው
ነፃ ማህበራት በአንድ ሀገር ላይ ዴሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ሚካኤል ባራቶን (Michael Bratton) ‹‹CIVIL SOCIETY AND POLITICAL TRANSITION IN AFRICA›› በሚል ፅሁፋቸው ከቀዝቃዛው ጦርነት መጠናቀቅ በኋላ ነፃ ማህበራት በዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸው ሚና እየተጠናከረ እንደመጣ ያስረዳሉ፡፡ አያይዘውም ነፃ ማህበራት ይህን አበርክቷቸውን እንዲወጡ የመንግስትን ኃይል የሚዘውሩ አካላት ፈቃደኝነት አስፈላጊ መሆኑን አበክረው ይገልፃሉ፡፡ የነፃ ማህበራት አበርክቶ በኢትዮጵያ ከመዳከም አልፎ የተዳፈነ ይመስላል፡፡

ኢህአዴግ ከ1997 በፊት በአንፃራዊ መለኪያ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸውን ማህበራት፣ ከድህረ 97 በኋላ ነፃነታቸውን የሚጋፋና ህልውናቸውን የሚፈታተን ህግ በማፅደቅ አልፈስፍሷቸዋል፡፡ የማህበራቱን ነፃነት በመጋፋት የፓርቲውን ፖለቲካ የሚያራምዱ ግለሰቦችን በአመራር ደረጃ በማስረግ ጭምር ተሳትፏቸውን አዳፍኗል፡፡ 

መንግስት ነፃ ማህበራት የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ ባህልና ግንዛቤ በማዳበር የሚያበረከረቱትን አስተዋፅኦ ከማበረታታት ይልቅ፣ ከዚምባቡዌ፣ ሲንጋፖርና ሩሲያ የተወሰዱ አደገኛ ልምዶችን የቃረመ አደገኛ የበጎ አድራጎትና የሲቪክ ድርጅቶች አዋጅ አፅድቋል፡፡ በዚህ ህግ ምክንያት የመስራት አቅማቸው የተሸመደመደ እና ወደ ሌላ ዘርፍ ስራቸውን የቀየሩ ማህበራት ቁጥር በርካታ ነው፡፡

ይህ ማህበራትን የማዳከምና ነፃነታቸውን የማሳጣት ስትራቴጂ በቀጥታ የህዝቡን የነፃነት የመደራጀት መብት የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ ዴሞክራሲ የማይዋጥላቸው አምባገነን መንግስታት ተግባር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር 21 አመታትን በምኒሊክ ቤተመንግስት ያሳለፈው የአቶ መለስ መንግስት ነፃ ማህበራትን በስልት ማዳከሙ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች መካከል ይጠቀሳል፡፡ 
         
የነፃ ፕሬስስ ሀሳብን የመግለፅ መብት አለመከበሩ
 ኢህአዴግ ወደ ስልጣን እንደወጣ ከወሰዳቸው አበረታች እርምጃዎች ውስጥ የፕሬስና ሀሳብን የመግለፅ መብትን “መፍቀዱ” ነው፡፡ መንግስት ይህ መብት ህገመንግስታዊ እንዲሆን ቢያደርግም በተግባር ግን አፋኝ እርምጃዎችን ከጅምሩ መውሰዱ ነፃ ፕሬስ እንዳይዳብር እንቅፋት ሆኗል፡፡የአንድ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መገለጫ የሆነው የፕሬስና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በኢትዮጵያ አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ መንግስት ላይ ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጠኞች እና ሀሳባቸውን በይፋ የሚገልፁ ፖለቲከኞች መታሰር፤ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የአደባባይ ምሁራንን አርቋል፡፡ 

ሀሳባቸው የሚገልፁ ጋዜጠኞችና ተቺዎች ከእስር ጋር ተፋጠው ለመስራት ተገደዋል፡፡ ኢህአዴግ ያወጣቸው የፕሬስና የፀረ ሽብር አዋጆች ኢትዮጵያውያን ሀሳባቸውን በፕሬስ ውጤቶች እንዳይገልፁ የሚጠፍር ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን እንዳያገኙ አግዷል፡፡ በተለይም ኢህአዴግ በቅርቡ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በኩል ቅድመ ምርመራን ለመጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩ ከላይ ያየናቸው የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሀገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንዲከስም አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲያብብ በሚረዱት የፕሬስ ውጤቶች አለማደግ ብሎም መመናመን የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራ ሌላው ማሳያ ነው፡፡
ሀገሪቱ በአንድ ጠቅላይ አምባገነን መሪ ስር መውደቋ
ጠቅላይ አምባገነንነት በአጭር ጊዜ የሚገነባ ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ከመገንባት የበለጠ ጊዜና ወጪ ይጠይቃል፡፡ ይህን አምባገነናዊ ስርአት ለመገንባት መንግስት በህዝቡ ሁሉን አቀፍ የህይወት ፈርጅ ውስጥ ቁጥጥር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በትምህርት ፣ በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ፣ በባህልና ኪነጥበብ ውስጥ ፖለቲካዊ ቁጥጥር በማድረግ እንዲሁም ፖለቲካዊ እንነታቸውን በማጥመቅ አቶ መለስ ጠቅላይ አምባገነን መሆንን መርጠዋል፡፡ 

በ2002 ምርጫ 99.6 በመቶ በሆነ ውጤት ፓርላማውን የተቆጣጠረው የአቶ መለስ መንግስት አውራ ፓርቲ መሆኑን በመግለጽ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ተንኮታኩቶ ጠቅላይ አምባገነን ስርዓት መደላደሉን አብስሯል፡፡ ግንቦት 20 አቶ መለስን በኢትዮጵያ አንግሷል፡፡ በሀገሪቱ ላይ ብቸኛው አድራጊና ፈጣሪ አቶ መለስ ናቸው፡፡ ሙገሳቸውም ሆነ ወቀሳቸው ድጋፋቸውም ሆነ ተቃውሟቸው እንደ እግዜር ቃል ይታያል፡፡ ለግንቦት ሃያ የተከፈለው መስዋዕትነት አቶ መለስን የሀገሪቱን ቁንጮ ከማድረግ ያለፈ ውጤት ያመጣ አይመስልም፡፡ የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሓት/ኢህአዴግ ነፃ የሚወጣውን የድል ቀን እንዲጠብቅ ሳያስገድዱት የሚቀር አይመስልም፡፡

Source: http://www.ethiomedia.com/2012_report/fenote_forty_four.pdf,  ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ, page 2

Wednesday, May 30, 2012

በሚድሮክ ወርቅ እና በሻኪሶ ህዝብ መካከል ያለው አለመግባባት ድርጅቱን አደጋ ላጥ ጥሎታል ተባለ

ኢሳት ዜና:-
ንብረትነቱ የሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ የሆነውና በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር የሚገኘው ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ በሻኪሶ አካባቢ ሕገወጥ ሠፈራ ይቁምልኝ ሲል ሲያካሂድ የነበረው ሙግት በፊዴራልና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በኩል ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ቢዝነሱ ሥጋት ላይ መውደቁን ምንጮች ጠቆመዋል፡፡

ሚድሮክ ወርቅ በሻኪሶ ለገደንቢ አካባቢ ሰዎች ተደራጅተው አነስተኛ ከተማ በመመሥረት ግልጽ ዘረፋ እየፈጸሙብኝ ነው ሲል ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አቤቱታ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ኩባንያው እንደሚለው የተደራጁ ዘራፊዎች ሕጋዊ በሆነ ይዞታው ውስጥ በመግባት በቁፋሮ የወጡ ድንጋዮችን ወስደው በመከስከስ ወርቅ አምራች ነን የሚሉ ናቸው ብሏል፡፡ድርጊቱ በመስፋፋቱም አካባቢው በድንጋይ ክምር በመሞላቱ “ሮክ ሲቲ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

የሼሁ ኩባንያ ድርጊቱን እንዲያሰቆሙለት በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታ አቅርቦ አጥጋቢ ምላሸ እንዳልተሰጠው በዚህም ምክንያት ቢዝነሱ ጭምር አደጋ ላይ መውደቁን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡  ኩባንያው በአካባቢው ያለውን የወርቅ ማእድን እየዘረፈ ፣ ነገር ግን ለሻኪሶ ህዝብ ምንም ያስገኘለት ጥቅም የለም በሚል ምክንያት ከሁለት አመት በፊት የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ዝርፊያው መባባሱ እየተነገረ ነው።

የአካባቢው ህዝብ ሚድርኦክ ኩባንያን በመቃመው ሰላማዊ ሳልፍ ባደረገበት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ የተወሰኑ ሰዎች መገደላቸውና በርካቶች ታስረው አሁንም ድረስ ፍርድ ቤት በመመላለስ ላይ ይገኛሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ የኩባንያውን ወርቅ እየወሰዱ ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ላይ መሆናቸውን አንድ የአካባቢው የተቃዋሚ አባል ለኢሳት መናገራቸው ይታወሳል።

ሚድሮክ ባለፈው ዓመት መጨረሻ 19 ቢሊየን ብር የሸያጭ ተስፋ ያለውና 33ሺ ኪሎግራም  የወርቅ ክምችት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማግኘቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የሼሁ የወርቅ ኩባንያ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነ የወርቅ ማምረት ፈቃድ ባለቤትና አምራች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሁለት ከፍተኛ ደረጃ ወርቅ ማዕድናት የማምረት ፈቃድ አለው፡፡በለገደንቢ የካባ ወርቅ ማዕድንና በሳካሮ የመሬት ውስጥ ለውስጥ ማዕድን ማምረቻ ነው ኩባንያው ከፍተኛ የሆነ ትርፍ እያጋበሰ ነው። ሚድሮክ ኩባንያ ስራ ከጀመረበት እኤአ 1997  አንስቶ ላለፉት 15 አመታት ከወርቅ ማእድናቱ ስላገኘው ትርፍ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም።

ኩባንያው ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ትርፋማ ቢሆንም፣ ለረጅም ጊዜ የትርፍ ግብር ከፍሎ እንደማያውቅ መረጃዎች ያመለክታሉ። ሺክ አላሙዲን በአለማችን ያለውን የሀብት መሰላል በፍጥነት እንዲወጡ ከረዷቸው ድርጅቶቻቸው መካከል ሚድሮክ ወርቅ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በቅርቡ ተጨማሪ መሬቶችን ለኩባንያው ለማስረከብ በጉጂ ዞን ውስጥ በተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ቢታዘዙም የተወሰኑ ቀበሌዎች ነዋሪዎች አሻፈረኝ ማለታቸው ይታወሳል።

Tuesday, May 29, 2012

ኢትዮጵያ ውስጥ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በየጊዜው እየታወከ ነው

ኢሳት ዜና:-
ዘጋቢዎቻችን ተዘዋውረው ያነጋገሩዋቸው የአዲስ አበባና የክልል ነዋሪዎች እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ፍጹ ም እየታወከ በመምጣቱ እርስበርሰም ሆነ በውጭ ካሉ ዘመዶቻቸው ጋር  መገናኘት አልቻሉም። በያዝነው ሳምንት የሞባይል አገልግሎት በተደጋጋሚ ሲቆራረጥ እንደ ነበር ነዋሪዎች ገልጠዋል። በተለይ ወጣቶች የኢንተርኔት አገልግሎት በየደቂቃው እየታወከባቸው በፌስቡክና በኢሜል ከጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት አልቻሉም።

አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ጋዜጠኛ ” መንግስታችን የኢንተርኔት አገልግሎቱን እያወከ አስቸግሮናል፣ ተራ ብሎጎቻችን ሁሉ እየተዘጉብን ደንግጠናል።” ብሎአል። የአሁኑ ተደጋጋሚ የፌስ ቡክ እና የሞባይል መታወክ ከጋዜጠኛ አበበ ገላው አጋጣሚና እና  ከሙስሊሙ ተቃውሞ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ዘጋቢዎቻችን የጠየቁዋቸው አስተያየት ሰጪዎች ይገምታሉ።

መንግስት የአበበ ገላው ፍሪደም “ነጻነት” የሚለው ቃል በኢንተርኔት እንዳይሰራጭ ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረጉ ይታወቃል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያንም ለጁመአ ተቀውሞ መልእክቶችን በኤስ ኤም ኤስና በፌስ ቡክ መላላካቸው ገዢው ፓርቲ ተጨማሪ የማወክ ስራ እንዲሰራ ሳያደርገው አይቀርም። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የጋዜጠኛ አበበ ገላው ፍሪደም “ነጻነት” የሚለው ቃል በሞባይል ብሉቱዝ ሰዎች ከመቀባባል አልፈው አዟሪዎች በሲዲ አባዝተው እየሸጡት ነው።

መንግስት በአሁኑ ጊዜ ምንም አይነት የተቃውሞ ድምጾችን ለመስማት ትእግስቱ እንደሌለው የሚወስዳቸው እርምጃዎች እንደሚያመላክቱ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ኢሳት ቀደም ብሎ በአረብ ሳት ስርጭት በጀመረ በወራት ውስጥ እንዲታፈን ሲደረግ፣ የኤርትራ ቴሌቪዥን ደግሞ አንዳንድ የኢሳት ዝግጅቶችን ከዩቱዩብ ላይ እየወሰደ ማስተላላፍ እንደጀመረ ገዢው ፓርቲ በተመሳሳይ ስራ የኤርትራ ቴሌቪዥን የአረብ ሳት ስርጭት እንዲቋረጥ አድርጓል። 

ይሁን እንጅ ገዢው ፓርቲ የራሱንም ጣቢያ አብሮ እንዲታወክ በማድረጉ በአሁኑ ጊዜ በአረብሳት ይተላለፍ የነበረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተቋርጧል። የውስጥ ምንጮች እንደሚናገሩት በኢትዮጵያ መንግስትና በአረብ ሳት ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ ቅራኔ እና ውዝግብ ተከስቷል።

በራስ መተማመን የጎደለው የሚመስለው የመለስ መንግስት፣ በአገር ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦችን ለማፈን በአታሚዎች በኩል ያወጣው ህግ ነጻ ሚዲያውን ያሳሰበ ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።  በተመሳሳይ ዜና ማተሚያ ቤቶች የቅድመ ምርመራ ውል እንዲፈርሙ እየወተወቱ ያሉት የግሉ ፕሬስ ተቋማት በውስጣቸው ያለባቸውን ክፍተቶች ለመድፈን የሚረዳቸውን ሁለት ዓይነት አደረጃጀቶች ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። 

ምንጮቻችን እንደገለጹት አሳታሚዎቹ ለሚያጋጥሙዋቸው ችግሮች በጋራ ሆነው ድምጻቸውን ለማሰማት አለመቻላቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት አንድ ጠንካራ ማህበር ለማቋቋም ከሰምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡በተጨማሪም ከመንግስት ማተሚያ ቤቶች ጥገኝነት ለመላቀቅ “የኢትዮጵያ ሚዲያ ዴቨሎፕመንት አክስዮን ማህበር” የተሰኘ የንግድ ማህበር ለማቋቋም ተሰማምተው ወደ ምስረታ ሒደት ተሸጋግረዋል፡፡

አ/ማህበሩ 500ሺብር ካፒታል የሚኖረው ሲሆን የአንዱ አክስዮን ዋጋ አንድ ሺብር ሆኖ በ500 አክስዮኖች የተከፋፈለ ነው፡፡አክሰዮን ማህበሩ ማንኛውንም የሕትመት ሥራ ለማከናወን፣የዲጂታል ቱክኖሎጂ ሕትመት ኢንዱስትሪ ውስጥ ለማሰተዋወቅ፣ሚዲያ ነክ በሆኑ ሌሎች ሥራዎች ላይ መዋዕለ ንዋዩን ለማፍሰሰ የሚያልም ነው፡፡

ሌላኛው “የኢትዮጵያ ፕሬስ አሳታሚዎች ማህበር” የሚል ጊዜያዊ መጠሪያ የተሰጠው ማኀበር አባላቱ ጠንካራ አቋም በመያዝ በተደራጀ መልክ ችግሮቻቸውን ለመፍታትና ለኢንዱስትሪው ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

 አሳታሚዎቹ ከሳምንት በፊት የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ያቀረበውንና ቅድመ ምርመራን ያሰፍናል በሚል የተቃወሙትን ውል በተመለከተ አማራጭ ሃሳባቸውን ለማኔጅመንቱ ካቀረቡ በኃላ በጉዳዩ ላይ ተወያይተው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የማተሚያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ጥሪ እንደሚያደርጉላቸው ገልጸው ከተሰናበቱ በኃላ መልሰው አልተገኛኙም፡፡

መለስ ኢትዮጵያን እንዴት እየመራት ነው?

BY ሪቻርድ ዳዉደን, (የሮያል አፍሪካን ሶሳይቲ ዳይሬክተር), ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ
መለስ ዜናዊ ለውጭ እንግዶች ሲናገሩ በጣም የተዋጣላቸው ናቸው፡፡ ለሚያስተዳድሯቸው ኢትዮጵያውያን ሲናገሩ ግን እጅግ አስቸጋሪና ገታራ ናቸው፡፡ ባለፈው ጊዜ በካምፕ ዴቭድ የG-8 ሀገራት ስብሰባ ላይ ከሚሳተፉ 4 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አንዱ ነበሩ፡፡ እርዳታ ሰጪዎች መለስን ይወዷቸዋል፡፡ እራሳቸውም ብዙ ያነበቡ፤ሀሳቦችን ሲገልፁ ቁጥሮችን የሚደረድሩና ትኩረት ማድረግ የሚችሉ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ለብዙ መቶ ዘመናት የኖረች ሀገር እንደመሆኗ እርሷን ማስተዳደር ከብሮክራሲያዊ ስራ የዘለለ ልዩ ጥበብ የሚጠይቅ አይደለም፡፡ እርዳታው ደግሞ ልክ የወንዝ ያክል በዓመት ወደ 4 ቢያንስ ዶላር ይጎርፋል፡፡ በዚያ ላይ መለስ በሶሚሊያና በሱዳን በኩል ባሰማሯቸው ወታደሮቻቸው የአሜሪካ ዘብ ናቸው፡፡ ከቀድሞ አጋራቸውና የቀጠናው አታራማሽ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ባለበት የሚቀጥል ጠላትነት አሏቸው፡፡

አንድ የመለስ ሁኔታ የጨነቀው የአሜሪካ ዲፕሎማት ሰውዬው “የሙባረክ አባዜ” አለባቸው ብለውኛል፡፡ “ለሙባረክ የግብጽን ሚና በቀጠናው ምን አንደሆነ እንጂ ግብጽ ውስጥ ምን (አደገኛ ሁኔታ) እየተካሄደ እንደሆነ ፈጽሞ ልንነግራቸው አንችልም፤ በኢትዮጵያም(አቶ መለስ ዘንድም) ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው፡፡ በምርጫ 1997 ዓ.ም ተቃዋሚዎች ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ማሸነፋቸውን ሲያውጁ መንግስት መሪዎቹን ከማሰሩም በላይ በሀገር ክህደት ነበር  የከሰሳቸው፡፡ ግማሾቹ ታሰሩ፤ የቀሩት ሀገር ጥለዉ ተሰደዱ፡፡ አሁን ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ 99.6% ድምጽ በማሸነፍ ሰማዕታቱ ቀና ብለው ያዩት የቴሌቪዥንዋን ‹‹ ኢትዮጵያ ›› ነው የአንድ ፓርቲ ስርዓት በሀገሪቷ ዘርግቷል፡፡

ባለፈው ሁለት ሳምንት ከአቶ መለስ ጋር በነበረኝ ቃለ መጠይቅ አቶ መለስ በመላ ሀገሪቱ ካሉ መንደሮች ተቃዋሚዎች የተመረጡበትን አንዲት መንደር እንኳ እንደማያውቁ ነግረውኛል፡፡ አንዳንዶች ያልሰመረ አምባገነናዊ ልማታዊነት ነው ይሉታል፡፡ መንግስት የሚለውን ካደረክ ከመንግስት የመሬት የውሃና የአገልግሎት ድጋፍ ታገኛለህ፡፡ ካላደረክ ምንም ታጣለህ፡፡ በህገ መንግስቱ የተደነገጉት የፖለቲካ መብቶች በባለስልጣናት ትእዛዝ ሲጣሱ ይውላሉ፡፡ የሚዲያ ነፃነትማ አይነሳም፤ በቅርቡ በወጣው ህግ መሠረት አታሚ ህገ ወጥ ነው ብሎ ያሰባቸውን ይዘቶች ያለማተም መብቱ እንደሆነ ደንግጓል፡፡ የህትመት ሚዲያው ያበቃለት መሆኑ የሚገባችሁ በኢትዮጵያ ጋዜጣ ማተም የሚችለው ማሽን የተያዘው በመንግስት መሆኑን ስታውቁ ነው፡፡

በ1983 ዓ.ም ስልጣን በኃይል ከያዙ ጀምሮ የአቶ መለስ ትልቁ ስኬት በዝቅተኛ ግብር እንደዚሁም ከክፍያ ነጻ በሆነ መሬት የውጭ ባለሀብቶችን መሳባቸው ነው፡፡ የቻይና ሞዴል በመከተል ባለሀብቶችን በመሳብ ግብርናውንና ፋብሪካዎችን ለማልማት ይሞክራሉ፡፡ አቶ መለስ “ከዚህ በፊት  በማርክሲዝም ፍቅር የነደዱ ናቸው በሚል እንተማ ነበር፤ አሁን ደግሞ የቤተሰብ ማንኪያ ለውጭ ባለሀብቶች በመሽጥ እንከሰሳለን፤ ማካካሻ መሆኑ ነው” ብለውኛል፡፡ መለስ ለአበባ እርሻና ለምግብ እህል ከ4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለውጭና ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ስጥተዋል፡፡ የመብራት ሀይል እንዲያገኙም ግድብ እየገነቡ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ከተሰሩ ግድቦችም ከአካባቢ ጋር ተስማሚ እንዲሁም ብዙ የውሃ ትነት የሌለበት ነው ይላሉ፡፡

 ነገር ግን ዞሮ ዞሮ ነፃ ገበያ አሟልተው ኢይፈቅዱም፤ ባንክና ቴሌኮም በመንግስት ሞኖፖል ስር ናቸው፡፡ ሁሉም መሬት የመንግስት ነው፤ ይህ በዚህ እንደሚቀጥል መለስ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ መለስ ‹‹እንከን የማይወጣለት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብተናል? አልገነባንም፤ በእድገት ላይ ያለ ጉዳይ ነው፤እግራችን የሚሮጠውን ያክል እየሮጠ ነው? አዎ፤ ይህ በአዲስ አበባ ብቻ አይደለም፤ በጣም ኪስ ነው የሚባሉ ቦታዎችም ጭምር ነው፡፡ ካለፉት መንግስታት በተቀራኒ እጅግ አስቸጋሪ ቀጠና ውስጥ የተረጋጋች ሀገር ፈጥረናል፡፡ አሰራራችን የትኛውንም መንደር ይዳስሳል፤ ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ አልታየም፤ መንግስት ሩቅና አላስፈላጊ ነበር›› በማለት ይናጋራሉ፡፡

አቶ መለስ ከምዕራብ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ወቀሳ በተቃራኒ የፖሊሲያቸውን ትክክለኛነት በግትርነት ይከላከላሉ፡፡ እድገታችሁ ከአካባቢ ጋር የማይስማማና ሀገሬውን ከትውልድ ቀየው እንደአልባሌ ነገር (bullshit) በግድ የሚያፈናቅል ነው በሚል የኦክላንድ ተቋም ያወጣውን ሪፖርትም ሙሉ በሙሉ አይቀበሉም፡፡ አርብቶ አደሮች በአርብቶ አደር የሕይወት ዘዬ እንዲኖሩ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ ስነግራቸው ትክክል መሆኑን ቢያምኑም እንኳ አስቀድመው አፍቃሬ ምዕራብ እንደሆንኩ ነግረውኝ ነበር የጀመሩት፡፡ፖለቲካውም ተመሳሳይ ነው፡፡

 በ1983 ዓ.ም ስልጣንን በኃይል የተቆጣጠሩት መለስ ከአናሳ ብሔር እንደመገኘታቸው የመውጫ ቀዳዳ የሚሆናቸውን የትኛውም ብሔር (ብሔረሰብ) የራሱን ነፃነት እንዲያውጅ የሚያስችላቸውን ህግ በህገ መንግስቱ ደነገጉ፡፡ የፖለቲካ ችግር በተከሰተ ቁጥር የትኛውም ብሔር ኢትዮጵያዊነት ማቆም እንደሚችል ይነገራል፤ ነገር ግን በየትኛውም ሁኔታ በህዝብ ድምጽ ተግባራዊ የሚደረግ አይደለም፡፡ አሁን በጋምቤላ ያለው ሁኔታ ኢህአዴግን ምድጃ ላይ ጥዶታል፡፡ በጋምቤላ መሬት ሁሉ ለግብርና አልሚዎች ተሰጥቷል፡፡ ሰዎች ከመሬት በሃይል ስለመፈናቀላቸው አቶ መለስ አያምኑም፡፡ መሬታቸውን የለቀቁት በፍቃዳቸው መሆኑን ለማስረዳት “የጋምቤላ ህዝብ መሬት ባለበት ነው የሰፈረው፤ ደግሞም እርግጠኛ ሁን፤ ከንግዲህ የጋምቤላ ወጣቶች ለማረስ እንጂ ለጥበቃ ወደ እርሻ አይሄዱም” ነበር ያሉኝ፡፡

መለስ የሚመሩት ፈጣን የመንግስት ካፒታሊዝም ይሰራ ይሆን? በቅርቡ አዲስ አበባ በተደረገው የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ወቅት ትችት የመጣው አንደ ከዚህ ቀደሙ ከምዕራባውያን መያዶች አልነበረም፤ የኢትዮጵያ ዋነኛ አጋር ከሆነችው ቻይና ነው፡፡ የቻይና የኢንቨስትመንት ፎረም ተጠሪ የነበረው ጋዎ ዘይፕንግ “እኛ ያደረግነውን የግድ አታድርግ” በማለት አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ጋዎ ዘይፕንግ “ሰብኣዊ ልማትን ያላገናዘበ የኢኮኖሚ እድገት አያስፈልግም፤ እኛ ከአየር መዛባትና፤ የሃብት ኢ-ፍትሃዊ ክፍፍል የተነሳ እየተሰቃየን ነው፤ እናንተ ይህ ችግር ገና አልገጠማችሁም፤ በመሆኑም ያልተነካካ ነጭ ወረቀት በጃችሁ አለ፤ ከማጨማለቃችሁ በፊት ጥሩ ነገር ሳሉበት፡፡” በማለት ምክር ብጤም ጨምሯቸዋል፡፡

በዚህ አይነት ሁኔታ የአፍሪካ መሪን በአደባባይ የወቀሰ የቻይና ባለስልጣን አለ? የውጭ ባለሃብቶችም ደስተኞች አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያን እድገት እየመሩ ቢሆንም አሁን ግን በሚገኘው ትርፍ ላይ ከመንግስት ሁሉን ፈላጊነት ጋር ግብግብ መግጠም ግድ ብሏቸዋል፡፡ የአበባ እርሻ ላይ የተሰማሩ ኩባኒያዎች ምርታቸውን ለማጓጓዝ የመንግስት ንብረት ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጭ እንዳይጠቀሙ በድንገት ተነገራቸው፡፡ ይህ ከሚያመርቱበት ማሳ እስከ አዲስ አበባ እና ከዚያ ወደ እውሮፓ መጫንን ይጨምራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ትላልቅ የአበባ እርሻዎች የአንዱ ባለቤት የሆነ ሰው በጭንቀት ተውጦ “ኢትዮጵያ እስካሁን እንዲህ አይነት ኩባኒያ የላትም” ቢለኝም ይህንን ተግባራዊ ያላደረገ ተቋም እንደሚቀማ ታውቋል፡፡ መንግስት የውጭ ኢንቨስትመንትን ወደ ሀገር ውስጥ ከሰበ በኋላ አሁን ግን እየተጫናቸው ትርፋቸውንም መቀማት ይፈልጋል፡፡

መለስ የኢኮኖሚ እድገት የማይፈታው ችግር

ከየአቅጣጫው እያዋጣቸው ነው፡፡ የዋጋ ንረቱ በ50% እየጋለበ ነው፡፡ ያናገርኳቸው ኢትዮጵያዉያን የኑሮ ውድነቱ በህይወት ዘመናቸው ብዙ የማያውቁት መሆኑን ነግረውኛል፡፡ ዋነኛ የኢትዮጵያውያን ምግብ የሆነው ጤፍ ዋጋ በ4 እጥፍ በመጨመሩ ድሆች ሕይወትን የማይኖሩባት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎች ስራ በሌለበት ተመራቂዎችን ያመርታሉ፡፡ በቅርቡ ያነጋገርኳት አንዲት ተመራቂ መቶ አካባቢ ሆነው ከተማሩ ጓደኞቿ አስሮቹ ብቻ ስራ ላይ እንዳሉ ነግራኛለች፡፡ የመንግስት ተስፋ ግን ኢኮኖሚው በፍጥነት ያድጋል የሚል ነው፡፡ ቀጣዩ የሀብት ምንጭ ማዕድን መሆኑን ተስፋ ያረገው መንግስት ነዳጅ ሊወጣ እንደሚችል አቶ መለስ በቅርቡ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡


ነገር ግን በቅርቡ ይህ ሊገጥመው ይችላል፤ አብዛኛው የከተማ ድሃ በምግብ እህል ላይ ባለው የዋጋ ንረት፤ ተመርቀው ስራ በማያገኙት የከተማ ወጣቶች፤ ነገሩ…. የአረቡ ዓለም መነሳሳት የኢትዮጵያውያንን ትኩረት አግኝቶ ነበር፡፡ ይህን በኢትዮጵያም መከሰቱ አይቀሬ ነዉ--ተመልከቱ!

Source: http://www.ethiomedia.com/2012_report/fenote_forty_four.pdf, ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ, page 3

መታወቂያችን አማራ ስለሚል ተመርጠን ታሰርን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ

 By ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ
ከሚዛን ተፈሪ ወደ ዲማ ለሥራ ስንሄድ ኬላ ላይ መታወቂያ እየተመለከቱ ሲፈትሹ መታወቂያችን ብሔር በሚለው ቦታ ላይ አማራ ስለሚል መርጠው እስር ቤት ከተቱን፡፡ ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ እነዚህ እስር ቤት ቆይተን ተፈታን የሚሉ ሰዎች እንደሚሉት “ዲማ በጉልበትህ ሠርተህ የምታገኘው ገንዘብ አለ የሚል መረጃ ስለደረሰን ሥራ ፍለጋ በመጓዝ ላይ ነበርን፡፡ ሚዛን ተፈሪ ስንደርስ ለፍተሻ ከመኪና ውረዱ አሉን፡፡ 

ወርደን ለፍተሻ ዝግጁ ሆንን፡፡ መታወቂያቸው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጋምቤላ፣ አፋር የሚል እንዲሳፈሩ ተፈቀደላቸው፡፡ አማራ የሚለውን 16 ሰዎች ሰብስበው እናንተ እንድታልፉ አይፈቀድም ብለው ሚዛን ተፈሪ ፖሊስ መምሪያ ወሰዱን፡፡ ከዚያም እስር ቤት አስገቡን፡፡ ከዚያም ሌላ 20 አማርኛ ተናጋሪዎች ተይዘው ታሰሩ፡፡ ምን አጠፋን? ወንጀል ሳንፈጽም ለምን ታስሩናላችሁ? ብለን ስንጠይቃቸው ወደዚያ ከሄዳችሁ አደጋ ይደርስባችኋል፡፡ ወደዚያ አማራ ሄዶ እንዲሰራ አይፈቀድም ብለውናል፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልፃሉ፡፡

“ትኬት ቆርጣችሁ ወደ አማራ ክልል ተመለሱ ብለው ከሦስት ቀን በኋላ የተወሰንን ሰዎችን ለቀቁን፡፡ ብዙዎቹ አሁንም በእስር ላይ ናቸው፡፡ እኛ ወደ ትውልድ መንደራችን ለመሄድ ገንዘባችንን ጨርሰናል፡፡ ብንሄድም ቦታ ስለሌለን ማረፊያ የለንም፡፡ ለዚህ ነው የቀን ሥራ ሠርተንም ጉርጓድ ቆፍረንም ህይወታችንን እንቀይራለን ብለን ጉዞ ጀምረን የነበረው፡፡ ሆኖም ግን አማራ በመሆናችን ተዘዋውረን ሠርተን እንዳንበላ ተደርገናል፡፡” ሲሉ አማረዋል፡፡

በመቀጠልም ሲናገሩ “እኛ ታስረን መፈታት ችለናል፡ ፡ ዛሬም ሥራ ፍለጋ ወደ ምንፈልግበት እንድንሄድና በነፃነት ከቦታ ቦታ እንድንቀሳቀስ አልተፈቀደልንም፡ ፡ ህጋዊን መንገድ ትተው በእግራቸው ጫካ ለጫካ ጉዞ የጀመሩ በርካታ ሰዎች ተገላዋል፡፡ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ሲገደሉም በአውሬ ሲበሉም የአካባቢው ኃላፊዎች ምንም የሚሰማቸው ፀፀት የለም፡፡ ህገ ወጦች ናቸው፡፡

እንኳን ሞቱ እንኳን ተበሉ እያሉ ሲሳለቁ ይሰማል፡፡” ካሉ በኋላ “የሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን በጥሞና ተመልክቶ ውሳኔ ይሰጠን፡፡ ተዘዋውረን የመኖርና ሠርቶ የመብላት መብታችን እንዲከበርልን አሳውቁልን፡፡” በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ የሚዛን ተፈሪ ፖሊስ መምሪያ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

Source: http://www.ethiomedia.com/2012_report/fenote_forty_four.pdf, ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ, PAGE 16

ወ/ሮ አዜብ መስፍን መሬት መውሰዳቸውን ያጋለጠው ሠራተኛ ታሰረ

Source: Finote Netsanet
በቅርቡ በቡራዩ ከተማ በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በተመራው ሙሰኞችን የማጋለጥ ስብሰባ ላይ “ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያለ አግባብ በወንድማቸው ስም መሬት ወስደዋል” ብሎ ያጋለጠው የማዘጋጃ ቤቱ ሠራተኛ መታሰር በከተማው መነጋገሪያ መሆኑን በአካባቢው ያነጋገርናቸው የከተማው ነዋሪዎች ለሪፖርተራችን ገለፁ፡፡

ነዋሪዎች እንደሚሉት “መድረኩ የተዘጋጀው በቡራዩ አካባቢ የመሬት ቅርምት ተፈጽሟል፤ በመንግስትና በህዝብ መሬት ግለሰቦች አላግባብ በልጽገዋል፤ ከፍተኛ ሙስና ተፈጽሟል ተብሎ ነበር” ይላሉ፡፡ ሆኖም ግን ይላሉ ምንጮቻችን “የመድረክ አመራሩ ተሰብስበው በአካባቢው ኃላፊዎችና ከቁጥር በማይገቡ ሙሰኞች ላይ ብቻ ጣቱን እንዲቀስር እንዲያጋልጥ ግፊት ይደረግ ነበር፡፡ 

ይህንን የተገነዘበው አቶ ኃይሉ ንጉሴ የተባለው የማዘጋጃ ቤቱ የፋይናንስ ሠራተኛ ተነስቶ ትኩረቱን ለምን በትንንሾቹ ብቻ ታደርጋላችሁ፡፡ ሙስናን በቁርጠኝነት የምትታገሉ ከሆነ ወደላይም አትመለከቱም፡፡ በዚህ በከተማችን ወ/ሮ አዜብ መስፍን በወንድማቸው ስም መሬት ወስደዋል፡፡ ለምን አይጣራም? ለምን እሳቸውም አይጠየቁም” ብሎ ተናግሯል፡፡

በወቅቱ ስብሰባውን የሚመሩት ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ “ጥቆማው አንድና አንድ ነው፡፡ ጥቆማው በማስረጃ መረጋገጥ አለበት፡፡ ዝም ብሎ መጠቆም አይደለም፡፡” እያሉ ጥቆማውን ለማጣጣልና ለማንቋሸሽም ሞክረዋል፡፡ ይህ ሲገርመን በቅርቡ ጠቋሚውን በሙስና ትፈለጋለህ ተብሎ ታስሯል፡፡ መንግስት በተለይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሙስናን ለመዋጋት ያለውን ቁርጠኝነትና ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከመሆኑም በላይ በመንግስት ላይ ያለን እምነት እየተሸረሸረ ነው፡፡” ሲሉ ሥጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

አቶ ኃይሉ ንጉሴ በገፈርሳ ቡራዩ ውስጥ ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቡራዩ ማዘጋጃ ቤት የፋይናንስ ሠራተኛ ነበር ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ያለአግባብ ከፍተኛ ሀብት አፍርተዋል ተብሎ ከሚታሙት ግለሰቦች ውስጥ አንዷ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

የአቶ መለስ ምስል ከአደባባይ ተሰረቀ


Source: Finote Netsanete
በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች መሰረቁ ተገለፀ፡፡

 በኢሳያስ ማስታወቂያ ታትሞ የተተከለው የአቶ መለስ ምስል “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደደፈረ ጀግና” የሚል መፈክር የያዘ እንደነበር የድርጅቱ ባለንብረት አቶ ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ተናግሯል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ገለፁት ምስሉ ተተክሎ የቆየው ለአምስት ቀናት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የምስሉን መጥፋት ግራ አጋቢ ያደረገው የአቶ መለስ ፎቶ በላዩ ላይ የታተመበት ከመሆኑ በተጨማሪ በቀን መሰረቁ ነው፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የአቶ መለስን ተክለ ስብዕና የሚገነቡ ምስሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተበራክተዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ በየትኛውም የአቶ መለስ ምስል ላይ ጉዳትም ሆነ ጥፋት ደርሶ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ አቶ ኢሳያስ ለምስሉ ከ35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ) ብር በላይ ማውጣቱን ገልፃóል፡፡ አቶ ኢሳያስ ክሎም 28 ካሬ የሚሆነው ይህው ምስል በመጥፋቱ እንደተደናገጠ ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡

ይኽው የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምስል ከተሠቀለበት ቦታ ተገንጥሎ የተወሰደ ሲሆን በዘመናዊ ዲጂታል የህትመት መሣሪያ በኢሣያስ ማስታወቂያ ታትሞ በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢሳያስ ማስታወቂያ ባለቤት ወጣት ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገረው የምስሉ መጠን 7 ሜትር በ4 ሜትር መሆኑን በመግለፅና ስራውን ለእይታ ለማብቃትና አጠቃላይ የፍሬም ሥራውን በማካተት 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) ወጭ እንደተረገበት ገልፃóል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠ/ሚኒስትሩ ምስል ግዙፍ ሆኖ ከፊት ለፊት አሁን በመገንባት ላይ ያለው
የህዳሴው ግድብ በአንድ ላይ ሆኖ ከምስሉ ስር “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ
ጀግና” የሚል ፅሑፍ እንደነበረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢህአዴግ የጥፋት ሀይሎችን በዝምታ እንደማያይ ተናገረ

ኢሳት ዜና:-
ገዢው ፓርቲ የግንቦት20 በአልን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ ተቃዋሚዎች እያሳደሩ ያለውን ተጽእኖ በዝርዝር አቅርቧል።

ኢህአዴግ በመግለጫው ” አገሪቱ የተያያዘችው ፈጣን ልማትና የዳበረ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ያስደነገጣቸው የጥፋት ሀይሎች ከውጭ ሆነው ለኢትዮጵያ ድጋፍ አታድርጉ፣ ብድር አትፍቀዱ ከማለት ጀምሮ ከሻዕብያ መንግስት ስልጠናና ምክር በመውሰድ በሽብር ስራ ላይ መሰማራታቸውን፣ በአገር ውስጥ ደግሞ የሀይማኖት፣ የኑሮ ውድነቱንና ሌሎች አጀንዳዎችን በማራገብ ላይ ይገኛሉ” ብሎአል።
ኢህአዴግ የእነዚህን አፍራሽ ሀይሎች ተልእኮ በቸልታ እንደማይመለከት ፣ ህዝቡም የጥፋት ሀይሎችን በጽናት ለመታገል ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።

ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠው መግለጫ ሀገሪቱ በፈጣን የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ብትገኝም ድህነትና ኋላቀርነት፣የኑሮ ውድነት፣በህብረተሰቡ ውስጥ የሚታየው በአቋራጭ የመክበር አስተሳሰብና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሥርዓቱን የሚፈታተኑ ችግሮች መሆናቸውን አብራርቷል።

እነዚህ ችግሮች ዘላቂ ልማትና መልካም አስተደደርን በማስፈን እንደሚፈቱ ኢህአዴግ ፅኑ አቋም እንዳለው ያብራራው መግለጫው አጣዳፊ የሆኑ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ችግሮች ለመፍታት መሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብና የሥራ ዕድሎችን በስፋት በመፍጠር የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ለማሳደግ ኢህአዴግ ትኩረት ሰጥቶ በመረባረብ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኢህአዴግ በአንድ በኩል ተቃዋሚዎች ህዝብን በሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየቀሰቀሱብኝ ነው በማለት ቢናገርም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ድህነትና ሁዋላ ቀርነት፣ የኑሮ ውድነትና በህብረተሰቡ ውስጥ የሚታየው በአቋራጭ የመበልጸግ እና የመልካም አስተዳዳር ችግሮች ስርአቱን የሚፈታተኑ ችግሮች ሆነዋል  ይላል።

ኢህአዴግ  የመልካም አስተዳዳር እጦት፣ የኑሮ ውድነትና ስርአጥነት የመሳሰሉት ችግሮች የስርአቱ ፈተና ሆነዋል በማለት ለማመን ከተገደደ፣ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች እነዚህን ችግሮች ያራግባሉ በማለት ክስ ማሰማቱ እርስ በርስ የሚቃረን ነው ሲል ዘጋቢያችን ገልጧል። እነዚህ ችግሮች ባይኖሩና ተቃዋሚዎች ፈጥረው ቢያወሯቸው የኢህአዴግ ወቀሳ ትክክል ይሆን ነበር የሚለው ዘጋቢያችን፣ አሁን ግን ኢህአዴግ ችግሮች በስፋት መኖራቸውን ካመነ በሁዋላ ተቃዋሚዎች እነዚህን ችግሮች እያራገቡ ነው በማለት ክስ መሰንዘሩ ኢህአዴግ የገባበትን አጣብቂኝ ያሳያል ብሎአል።

በሌላ ዜና ደግሞ አቶ መለስ የግንቦት20ን በአል በማስመልከት ምንም ቃል ሳይተነፍሱ ያሳለፉበት አመት ቢኖር የዘንድሮው ነው። አቶ መለስ እስካሁን በቴሌቪዥን ወይም በራዲዮ ወይም በጋዜጦች ቀርበው ዘወትር ያደርጉ እንደነበረው ቃለምልልስ አልሰጡም። አቶ መለስ ያለፈውን ሳምንት ያሳለፉት በ21 አመት የስልጣን ዘመናቸው አጋጥሞአቸው የማያውቅ ተቃውሞ አስተናግደው ነው። በጋዜጠኛ አበበ ገላው እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከደረሰባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ያገገሙ የማይመስሉት አቶ መለስ፣ ወደ ስልጣን ኮርቻ ያመጣቸውን ግንቦት20ን ሳይዘክሩ  መቅረታቸው መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
__________________________________________________________________________________________________________

Monday, May 28, 2012

Ethiopia: ‘Special Police’ Execute 10


Investigate Paramilitary Abuses, Permit Access to Closed-Off Somali Region
Source: Human Rights Watch
(Nairobi) – An Ethiopian government-backed paramilitary force summarily executed 10 men during a March 2012 operation in Ethiopia’s eastern Somali region. Detailed information on the killings and other abuses by the force known as the “Liyu police” only came to light after a Human Rights Watch fact-finding mission to neighboring Somaliland in April.

On March 16 a Liyu police member fatally shot a resident of Raqda village, in the Gashaamo district of Somali region, who was trying to protect a fellow villager. That day, men from Raqda retaliated by killing seven Liyu police members, prompting a reprisal operation by dozens of Liyu police in four villages on March 16 and 17. During this operation the Liyu police force summarily executed at least 10 men who were in their custody, killed at least 9 residents in ensuing gunfights, abducted at least 24 men, and looted dozens of shops and houses.

“The killing of several Liyu police members doesn’t justify the force’s brutal retaliation against the local population,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director at Human Rights Watch. “The Liyu police abuses in Somali region show the urgent need for the Ethiopian government to rein in this lawless force.”

The Ethiopian government should hold those responsible for the killings and other abuses to account and prevent future abuses by the force.

Ethiopian authorities created the Liyu (“special” in Amharic) police in the Somali region in 2007 when an armed conflict between the insurgent Ogaden National Liberation Front (ONLF) and the government escalated. By 2008 the Liyu police became a prominent counterinsurgency force recruited and led by the regional security chief at that time, Abdi Mohammed Omar (known as “Abdi Illey”), who is now the president of Somali Regional State.

The Liyu police have been implicated in numerous serious abuses against civilians throughout the Somali region in the context of counterinsurgency operations. The legal status of the force is unclear, but credible sources have informed Human Rights Watch that members have received training, uniforms, arms, and salaries from the Ethiopian government via the regional authorities.

Human Rights Watch spoke to 30 victims, relatives of victims, and witnesses to the March incidents from four villages who had fled across the border to Somaliland and who gave detailed accounts of the events.

Witnesses told Human Rights Watch that on the evening of March 16 the Liyu police returned to Raqda following the clashes with the community earlier in the day that left seven police force members dead. The next morning, March 17, the Liyu police rounded up 23 men in Raqda and put them into a truck heading towards Galka, a neighboringvillage. Along the way the Liyu police stopped the truck, ordered five randomly selected men to descend, and shot them by the roadside. “It was three police who shot them,” a detainee told Human Rights Watch. “They shot them in the forehead and shoulder: three bullets per person.”

Also on March 17, at about 6 a.m., Liyu police in two vehicles opened an assault on the nearby village of Adaada. Survivors of the attack and victims’ relatives described Liyu police members going house to house searching for firearms and dragging men from their homes. The Liyu police also started shooting in the air. Local residents with arms and the Liyu police began fighting and at least four villagers were killed. Many civilians fled the village.

After several hours the Liyu police left but later returned when villagers came back to the village to bury those killed earlier that day. Fighting resumed in the afternoon and at least another five villagers were killed. The Liyu police took another four men from their homes and summarily executed them. A woman whose brother was a veterinarian told Human Rights Watch: “They caught my brother and took him outside. They shot him in the head and then slit his throat.”

For five days Liyu police also deployed outside Langeita, another village in the district, and restricted people’s movement. The Liyu police carried out widespread looting of shops and houses in at least two of the villages, residents said.

Human Rights Watch received an unconfirmed report that following the incidents local authorities arrested three Liyu police members. However it is unclear whether the members have been charged or whether further investigations have taken place.

The Ethiopian government’s response to reports of abuses in the Somali region has been to severely restrict or control access for journalists, aid organizations, human rights groups, and other independent monitors. Ethiopia’s regional and federal government should urgently facilitate access for independent investigations of the events by independent media and human rights investigators, including the United Nations Special Rapporteur on extrajudicial and summary executions.

“For years the Ethiopian government has jailed and deported journalists for reporting on the Somali region,” Lefkow said. “Donor countries should call on Ethiopia to allow access to the media and rights groups so abuses can’t be hidden away.”

Liyu Police Abuses, March 2012

Summary Executions and Killings
Human Rights Watch interviewed witnesses and relatives of the victims who described witnessing at least 10 summary executions by the Liyu police on March 16 and 17. The actual number may be higher.

On March 16 in Raqda, a Liyu police member shot dead Abdiqani Abdillahi Abdi after he intervened to stop the paramilitary from harassing and beating another villager. Several villagers heard the Liyu police member saying to Abdiqani, “What can you do for him?” and then heard the shot.

The shooting ignited a confrontation between the Liyu police and the local community. The nine Liyu police who were deployed in Raqda then left via the road to the neighboring village of Adaada. A number of Raqda residents, including members of Abdiqani’s family, took their weapons, went after the Liyu police, and reportedly killed seven of them in a confrontation that followed.

The next morning, on March 17 at around 11 a.m., the Liyu police selected five men from a group of 23 men they had detained in Raqda and were taking towards Galka village in a truck. The Liyu police forced the five men to sit by the roadside and then shot them. Another detainee described what happened:
In between Galka and Raqda they stopped the truck. There were four other Liyu police vehicles accompanying the truck. This was around 11 a.m. They told five of us to get out of the lorry. They [randomly] ordered five out – none in particular. The man standing near the lorry ordered them to “Kill them, shoot them.” It was three police who shot them. They shot them in the forehead and shoulder: three bullets per person.
Another detainee saw the five being shot in the head and said the Liyu police threatened the remaining detainees, saying, “We will kill you all like this.”

The same day the Liyu police summarily executed four men in Adaada, where they had carried out house-to-house searches that morning. In all four cases multiple witnesses described the victims as unarmed and in custody when they were shot, either in the neck or head, shortly after having been dragged from their homes.

Witnesses described the summary execution of a veterinarian. The Liyu police dragged him from his home and shot him in the head, but when they realized that he was not dead, they slit his throat. The veterinarian’s middle-aged sister told Human Rights Watch:
They entered the home and asked where the man responsible for the home was. There were seven of them. They caught my brother and took him outside. They shot him in the head and then slit his throat. After killing him, they asked my niece where her father’s rifle was, but she could not find the keys and they hit her on the back of the shoulder with the butt of a gun.
Witnesses also told Human Rights Watch that a teenage boy was dragged from his uncle’s home, taken nearby, momentarily interrogated, and then shot. One witness heard him reciting a prayer before being killed. His body was left on the ground near a trash dump. A third victim, an elderly man, was taken from outside his home, interrogated for a short time, and then shot while standing. Several witnesses heard him pleading with the police to spare his life. The fourth victim was also taken from his home and shot shortly after.

At least nine other men were killed by the Liyu police in Adaada, but the circumstances of their deaths are unclear. There was armed resistance to the Liyu police attack, and some of the nine may have been armed. However, according to witnesses, the Liyu police shot several men, in the upper body and head, who were trying to escape. Two men fleeing were reportedly run over by Liyu police vehicles.

Abductions, Torture, and Ill-Treatment
During the house searches in Adaada, the Liyu police abducted a number of village men and tortured and mistreated several people, including at least three women.

An Adaada resident, one of the first to be taken from his home on the morning of March 17, described to Human Rights Watch his treatment by the Liyu police:
They entered and told my wife to shut up. Four men entered the house with four waiting outside. They came over to me and took me. They also took the gun from my house. They hit me with the butt of a gun and took me to a small river near my home. They tied a belt around my neck. I lost consciousness. They threw me in a berket [small water hole] that was 15 meters deep and then they threw branches over me. There was mud in the berket. I managed to climb up when I woke up.
The Liyu police seriously beat at least three women during house searches in Adaada. A young woman said that Liyu police members who had entered her home beat her after she told them that her husband was absent: “They said I was lying, they kicked me and crushed my head with the back of the gun. I had some injuries in my kidney. I lost a tooth.”

Three men who had been abducted in Raqda on March 17 told Human Rights Watch they were each detained for nine days. During the first 24 hours they were without water. For four days the Liyu police drove them around in an open truck between villages and towns in an apparent attempt to hide them from local residents, and possibly also from federal authorities.

During the first four days of their detention they were beaten by the police with sticks and gun butts. On at least two occasions the paramilitaries guarding them threatened to execute them. However, disagreements among the Liyu police on how to proceed apparently saved the men’s lives. One former detainee told Human Rights Watch:
We were driving around different villages and some of the police said they should release us because the federal government will give them problems, they will discipline us, as we have committed a crime. Others said, “Let us kill all 24.” There were different ideas among the police.
After four days in the truck they were detained for at least another four days out in the sun near the village of Langeita, where they received only minimal food and water. After that the Liyu police took them to Gashaamo, where they were released on March 25 as a result of negotiations between the regional government and clan elders.

Looting
Residents of Adaada and Langeita described widespread looting of property, food, and money from shops and houses by the Liyu police. Six villagers who spoke to Human Rights Watch said that their own houses, belongings, and property had been looted on March 17.

A 45-year-old woman from Langeita said that the Liyu police moved around the village in groups of five to seven and entered 10 stores. Two or three would enter a shop and steal shoes, clothes, drinks, and food. Two women said they could not return to their villages because they had lost all their property.

Reports from local authorities in neighbouring Somaliland suggest that discussions have taken place between clan elders from the affected villages and the regional authorities to negotiate a solution to the situation. None of the local residents who spoke with Human Rights Watch had current plans to return to their homes.

Background
Ethiopia’s Somali region has been the site of a low-level insurgency by the Ogaden National Liberation Front (ONLF) for more than a decade. The ONLF, an ethnic Somali armed movement largely supported by members of the Ogaden clan, has sought greater political autonomy for the region. Following the ONLF’s April 2007 attack on the oil installation in Obole, which resulted in the deaths of 70 civilians and the capture of several Chinese oil workers, the Ethiopian government carried out a major counterinsurgency campaign in the five zones of the region primarily affected by the conflict.

Human Rights Watch’s June 2008 report of its investigation into abuses in the conflict found that the Ethiopian National Defense Force and the ONLF had committed war crimes between mid-2007 and early 2008, and that the Ethiopian armed forces could be responsible for crimes against humanity based on the patterns of executions, torture, rape, and forced displacement.

These abuses have never been independently investigated. Ethiopia’s Foreign Affairs Ministry initiated an inquiry in late 2008 in response to the Human Rights Watch report, but that inquiry failed to meet the basic requirements of independence, timeliness, and confidentiality that credible investigations require. The government has repeatedly ignored calls for an independent inquiry into the abuses in the region.

Since the escalation of fighting in 2007 the Ethiopian government has imposed tight controls on access to Somali region for independent journalists and human rights monitors. In July 2011 two Swedish journalists who entered the region to report on the conflict were arrested, convicted, and sentenced to 11 years in prison under Ethiopia’s vague and overbroad anti-terrorism law.

Gashaamo district, where the March 2012 events took place, is in Dhagabhur zone, one of the five affected by the conflict. However, it was not an area directly affected by fighting in previous years, and is largely populated by members of the ethnic Somali Isaaq clan, who are not generally perceived to be a source of support for the ONLF.

የመድረክ አመራሮች የአበበ ገላውን ተቃውሞ ደገፉ

ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የቡድን ስምንት አገራት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ከአፍሪካ ከተጋበዙ አራት መሪዎች አንዱ የነበሩት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ፤ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚለው አጀንዳ ዙሪያ የአገራቸውን ተመክሮ ለታዳሚው ከማጋራት ውጭ ሌላ ነገር ይገጥመኛል ብለው አላሰቡም ነበር፡፡

 አገር አማን ብለው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት ጠ/ሚኒስትሩ፤ በ “ኢሳት” ተባባሪ መስራችና ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተቃውሞ ነበር ከማብራሪያቸው የተናጠቡት፡፡ ጠ/ሚኒስትሩም ሆኑ ሌሎች የስብሰባው ታዳሚዎች ያልጠበቁት ዱብዕዳ ቢሆንም ለጋዜጠኛው ግን ድንገተኛ አይመስልም – ተቃውሞው፡፡ ተቃውሞውን የአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ በኢራቅ ንግግር ሲያደርጉ በአንድ ኢራቃዊ ጋዜጠኛ ከተወረወረባቸው ጫማ ጋር ይመሳሰላል፡፡ 

ድንገተኛው ተቃውሞ ከተሰማ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን በሰጡት አስተያየት ተቃውሞው ትክክል አይደለም ብለዋል – “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጎደለው ተግባር ነው ፤ የአገሪቱን ብሎም የአፍሪካን ጥቅም ይነካል” በሚል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአገር ውስጥ በትክክለኛ መንገድ መቃወም ስለማይቻል ጋዜጠኛው ያደረገው ትክክል ነው የሚሉም አልጠፉም፡፡ ይሄን ሃሳብ ከሚጋሩት መካከል የመድረክ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ አንዱ ሲሆኑ ጋዜጠኛው ያነሳቸው ሃሳቦች እኛም በየጊዜው መግለጫ የምንሰጥባቸው ናቸው ብለዋል፡፡ 

ፕ/ር በየነ ተቃውሞውን ለምን ተገቢ ነው እንዳሉ እንዲያስረዱን ጠይቀናቸው እንዲህ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡አንድ ህዝብ ሃሳቡን ለመግለጽ ክልከላ ተደርጐበት ሲታፈን የዚህ ዓይነት ነገሮች አምልጠው መውጣታቸው አይቀርም፡፡ ሰው ሲከፋና ህጋዊ የሆነውን ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሲነፈግ”፤ ከዚህም አልፎ ሄዶ ተስፋ በቆረጠ እርምጃ ውስጥ ይገባል፡፡ የተተቹት ወገኖች ለምን እንደደነቃቸው አላውቅም፡፡የአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማ አልተወረወረም? ያም እኮ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ህዝባዊ መድረክ ላይ ያሉ የፓርቲ መሪዎች የዚህ አይነት ነገር እንደሚያጋጥማቸው አውቀው ነው መንቀሳቀስ ያለባቸው፡፡ እስከዛሬ ካየናቸው ክስተቶች የተለየ ነው ብዬ አላምንም፡፡

 ከተቃውሞው ጋር ተያይዞ የሚነሳውን “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የሚል ነገር ያለቦ መደንጐርአያስፈልግም፡ መንጎድር፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብም ሆነ የዜና ሰው በተሰማራበት ዘርፍ መደመጥን ይፈልጋል፡፡ ያ ደግሞ ሰብዓዊ፣ አለማቀፋዊ መብት ነው፡፡ ይሄንን ተነፍጐ፤ ከዚህ በፊት የሚያደርጋቸው ነገሮች እየተንቋሸሹና እየተወነጀሉ ያለ ሰው፤ የዚህ ዓይነት አጋጣሚ አግኝቶ ድምጽን ማሰማት ቢፈልግ የማይጠበቅ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የሚለውን ነገር በተመለከተ፤ ሁሉም እኮ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን አክብሮ መገኘት አለበት፡፡ የአገሪቱም ገዢዎች እኮ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን አክብረው፤ የዜጐቻቸውን ሃሳብ ማዳመጥ አለባቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት እድልና መድረክ በተነፈገበት አገር ላይ ነው የምንኖረው፡፡ 

ጋዜጠኛው እንደልቡ ጥያቄ እንዲጠይቅ ጠ/ሚኒስትሩ ለምን እዛው እያሉ ለጋዜጠኞች ፕሬስ ኮንፈረንስ አይሰጡም ነበር? ይሄ እድል ቢኖር ጋዜጠኛው ጥያቄውን በአግባቡ ማቅረብ ይችል ነበር፡፡ ያ እድል ስላልተፈጠረለት፤ ያውም ተፈቅዶለት ሳይሆን ድምፁን ከፍ አድርጐ ሲናገር ነው ፖሊስ ይዞ ያስወጣው፡፡ጠ/ሚ መለስ አፍሪካንና አገርን ወክለው ሲሰጡት የነበረውን ሃሳብ በማቋረጥ ተቃውሞውን ማሰማቱ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን የአገርንና የአህጉሪቱዋን ገፅታ የሚያበላሽ ነው ሲሉ የሚቃወሙ ወገኖች አሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?

አይ የጠ/ሚኒስትሩ ሃሳብማ አይቋረጥም፡፡ ቢቋረጥም ይቀጥላል፡፡ በተፈቀደላቸው ጊዜ ሀሳባቸውን አቅርበው እንደሚጠናቀቅ ነው የሚገባኝ፡፡ አሳፋሪው ነገር “ለካስ የማይታወቅባቸው ህዝቡ ብሶት የሚያሰማባቸው ሰው ናቸው!” የሚለው ነው፡፡ በተረፈ የሳቸው መልእክት በጋዜጠኛው ተቃውሞ ተቋርጦ አልቀረም፤ ተላልፉዋል፡፡ ነገር ግን ለመከበር ሌላውንም አክብሮ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ ለምንድነው ጠ/ሚኒስትሩና ባለስልጣኖቻቸው የኢትዮጵያውያኑን ብሶት የማያዳምጡት? ለምንድነው በደሉን ሲያሰማ የሚያንቋሽሹት? ከዚህ ጥያቄ ነው መነሳት ያለብን፡፡ ይሄ ጨዋነት የሚባለው እየየም እኮ ሲዳላ ነው፡፡

 ይሄ ሰው እኮ ሊደመጥ፤ ሊሰማ ያልቻለ ሰው ነው፡፡ ጨዋ ለመሆንም እኮ መድረክ አልተሰጠውም፤ የሞት ሞቱን እኮ ነው ተቃውሞውን የገለፀው ፤ ያውም ፖሊስ ይዞ እስኪያስወጣው ድረስ፡፡ ከተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች እንደተሰማው ጋዜጠኛው በተቃውሞው ያነሳቸው ጉዳዮች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣አምባገነናዊ መንግስት ስለመኖሩ፣ ያለነፃነት የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ አይቻልም የሚሉና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን የተመለከተ ነበር፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው?

ጋዜጠኛው ያነሳቸው ገዳዮች በአጠቃላይ እኛ የምንላቸው” በየጊዜው መግለጫ የምናወጣባቸው ሃሳቦች ናቸው፡፡ የታሰሩትንም ፍ/ቤት ድረስ ሄደን ለመከላከል እየታገልን ያለንበት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ እሱ ያነሳው ጉዳይ የስም ማጥፋት፣ የውሸት ነገር የለውም፡፡ ሁላችንም የምናነሳው ጉዳይ ነው፡፡ ያነሳበቱ አግባብ (መድረኩ) የሚነሳበት ነው ወይ ሲባል— እንግዲህ ተስፋ የቆረጠ ሰው ምን ያድርግ? የት ያሰማ፣ የት ይደመጥ? በዚያ ላይ ደግሞ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከልማት ጋር ግንኙነት የላቸውም እየተባለ ነው፡፡ 

በተለይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን መገንባት (መብቶችን መፍቀድ) ከልማትና ከአገር እድገት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም በማለት ፐብሊክ ወርልድ ፎረም ላይ ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ዲሞክራሲያዊ መብት ፈቅደው ሰው በነፃነት ሃሳቡን እንዲገልጽ ማድረግ ነበረባቸው፡፡የኢህአዴግ ስርዓት በራሱ እኮ አምባገነን ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ የአምባገነኑ ስርዓት መሪ ናቸው፡፡ በአንድ ብቸኛ ፓርቲ አውራ አመራር “ 30 እና ከዛም በላይ ዓመት ገዝተን አገሪቱን ወደ ልማት እናሸጋግራለን ብለው በጽሑፍ ማስፈራቸው ይታወቃል፡፡ አምባገነንነቱን በራሳቸው ቃል እኮ ነው ያስቀመጡት፡፡

ስለ ኢትዮጵያ ጨዋነትም ሆነ ሌላ ነገር ሲወራ ከሁሉም አቅጣጫ ነው መታየት ያለበት፡፡ አመራሩ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ተላብሶ የህዝቡን መብት አክብሮ ነው እያስተዳደረ ያለው? ህዝቡንና ወገኑን አሸባሪዎች (ቴሬሪስት) እያለ የሚያንቋሽሽ ስርዓት እንዴት ብሎ አክብሮት ያገኛል? በዚህ ህብረተሰብ ውስጥ መከባበርን መጀመር ፤ የህዝብን ሀሳብም አስተሳሰብም ማድመጥ መጀመር ይኖርበታል፡፡ ከዚያም በመነሳት መተማመን መጀመር አለበት፡፡ ጠ/ሚ የሚመሩት መንግስታቸው ደግሞ ይሄንን ጉዳይ ተቀብሎ የሚንቀሳቀስ አይደለም፡፡ ራሳቸውም በሚናገሩበት ጊዜ የምናየው ነው ፤ ዜጐችን የሚያከብር አይደለም፡፡ 

ይሄ ባልሆነበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ተስፋ የቆረጠ ትግል ውስጥ እንዲገቡ ስርዓታቸው እየገፋቸው መሆኑን ቢያውቁትና ሊያርሙት ቢገባ መልካም ነው፡፡ አቶ አስራት ጣሴ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ ዋና ፀሃፊ ናቸው፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰጡት አስተያየት ”አንድ ጋዜጠኛ ይቅርና ማንም ዜጋ ባገኘው መድረክና ባገኘበት ፎረም ላይ ጥቃት ሳያደርስ በጥሩ ቋንቋ ቅዋሜውን ማንሳት በአገርም በኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ላይም አቶ አበበ ያደረገው መጥፎ ነው የሚል አስተያየት የለኝም፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ፍትህና መልካም አስተዳደር ሊሰፍንባት ያልቻለች አገር ናት፡፡ አብዛኛው ህዝብ በድህነት እየማቀቀ ጥቂቶች የሚበለፅጉበት አገር ሆናለች፡፡ 

የሰበዓዊና የዲሞክራሲያዊ መብቶች ያለገደብ እየተጣሰ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደ አገር ትቀጥላለች ወይ? እንደ አገር አለች ወይ? የሚለው ነው የሚያሰጋኝ፡፡ የጋራ ችግር፣ የጋራ ረሃብ የፍትህ እጦት አለብን፡፡ ጋዜጦች በራሳቸው ያለባቸውን አደጋ እናውቃለን፡፡ የአሜሪካ ሬድዮና የጀርመን ሬድዮ ጃም በሚደረግባት አገር እየኖርን በተገኘው አለማቀፍ ፎረም ኢትዮጵያ ያለችበትን ችግር መግለፅና መናገር እንደዚ ዓይነት ድፍረትና ትግል የሚጠበቅ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች አለመብዛታቸው ነው የሚያሳዝነኝ፡፡ ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ስርዓት ባለበት አገር በተገኘው ፎረም መቃወም ተገቢ ነው፤ ግዴታም ነው ብየ ነው የማስበው፡፡“ ብለዋል፡፡

(ምንጭ አዲስ አድማስ)