“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ
ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል
ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ
ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር
ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት ቤንሻንጉል ክልል ያቀናሉ፡፡
Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Saturday, May 11, 2013
Sunday, May 5, 2013
“ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን እያፈረሰ የራሱን ይፈጥራል”
የመኢአድ ሊቀመንበር ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ስለገዢው ፓርቲ ምን ይላሉ?
- “ከ97 ወዲህ ፍርሃት የተጠናወተው ፓርቲ ሆኗል”
- “ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ሰላዮችን አሰማርቷል”
- “ምርጫኮ የለም ፤ ያለተወዳዳሪ ምረጡኝ ይላል”
በአገራችን የምርጫ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጠው የ97
ምርጫ ቅንጅትን በከፍተኛ ደረጃ ይመሩ የነበሩት እና በአሁኑ ሰዓት የመኢአድ ሊቀመንበር የሆኑት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፤
መጽሐፍ ይጽፋሉ ተብሎ ከተጠበቀበት ጊዜ ዘግይተውም ቢሆን “ህይወቴና የፖለቲካ እርምጃዬ” የሚል መጽሐፍ ለንባብ
ሊያበቁ ተቃርበዋል፡፡ መጽሐፉ 200 ገጽ ያለው ሲሆን ቀጣይነት አለውም ተብሏል። ኢ/ሩ በእንግሊዝኛም ሰፋ ያለ
መጽሐፍ እየፃፉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በአዲሱ መጽሐፋቸው፣ በአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ
የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ከኢንጂነር ሃይሉ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)