Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Saturday, September 8, 2012
3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል
(Sept.
8) ድርቅ አሁንም ለኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንደሚቀጥልና፤ ከነሀሴ እስከ መጪው ታህሳስ ድረስ፤ 3.7 ሚሊዮን
ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፤ የግብርና ሚኒስቴር አቶ ምትኩ ካሳ ገለጡ።
ከነሀሴ በፊት
በነበሩት ስድስት ወራት ውስጥ፤ የምግብ ተረጂዎች ቁጥር 3.2 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ 4 ወራት ግን
የተረጂዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨምሮ፤ በአሁኑ ሰዓትና እስከሚቀጥለው ታህሳስ መጨረሻ፤ የተረጂዎች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን
እንደሚደርስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ መናገራቸውን ካፒታል ኢትዮጵያ ዘግቧል።
የጋንቤላው ተወላጅ እንግሊዝን ሊከሱ ነው
(Sept. 8) ከእንግሊዝ መንግስት በተገኘ ድጋፍ የሰብአዊ መብቴ ተጥሶብኛል ያሉ አንድ የጋምቤላ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ፤ የእንግሊዝ መንግስትን ሊከሱ እንደሆነ ቢቢሲ ዘገበ።
ስማቸው ያልተጠቀሰውና በስደተኝነት በኬንያ የሚገኙት ከሳሽ በጠበቆቻቸው በኩል እንደተናገሩት፤ በጋምቤላ አካባቢ
በሚካሄድ የሰፈራ መርሀግብር የተነሳ፤ ከመሬታቸው እንደተፈናቀሉና እንደተደበደቡ፤ እንዲሁም ሴቶች ሲደፈሩ
እንደተመለከቱ ተናግረዋል።
Friday, September 7, 2012
በኢትዮጽያ የዋጋ ንረት በ30 በመቶ አሻቀበ
ኢሳት ዜና:-የነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሸበት በ30 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ ኤጀንሲው
ትላንት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚጠቁመው ከ12 ወራቱ አጠቃላይ አገራዊ የዋጋ ግሸበት ውስጥ የምግብ ዋጋ ግሸበት
36 ነጥብ 5 በመቶ፣ምግብ ነክ ያልሆኑ 20 ነጥብ 9 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ ከምግብ ውስጥ ሥጋ በ57 በመቶ ጭማሪ
በማሳየት ከፍተኛውን ሪከርድ ይዟል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ፈጣን ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊው ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ የግንቦት7 አመራሮች ተናገሩ
ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ከፍተኛ የአመራር አባላት የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ እና ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከኢሳት ጋር
ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት፣ ንቅናቄው በስልጣን ላይ ያለውን ሀይል አስገድዶ ከተቻለ ወደ ድርድር ካልተቻለም
ለማስወገድ፣ ፈጣን የሆነ ውጤታማ ስራ የሚሰራበትን ዝግጅት እያደረገ ነው።
ገዢው ፓርቲ ህልውናውንም
አገሪቱንም ከጥፋት ለመከላከል በአፋጣኝ የፖለቲካ ለውጥ በማድረግ ሁሉም በእኩል የሚሳተፉበት የሽግግር ጊዜ
አስተዳደር እንዲመሰረት የግንቦት7 መሪዎች አሳስበው፣ ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊው መስዋትነት ተከፍሎ ለውጥ ይመጣል
ሲሉ ተናገረዋል።
“ወደ ሥልጣን የመጣው አመራር ባለፈው መንገድ ሊቀጥል አይችልም” ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አስጠነቀቁ
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ |
ኢሳት ዜና:-“በቀጣይ በኢትዮጵያ የተሸለ ነገር የሚመጣው፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ተገናኝተው፣ በክብ ጠረጴዛ
ዙሪያ ተመካክረው መፍትሔ ማምጣት የሚችሉበት ዕድል ሲፈጠር ብቻ ነው።” ሲሉ አቶ ቡልቻ ወደ ሥልጣን እየመጣ ላለው
አዲስ አመራር ቡድን መልዕክት አስተላለፈዋል።
የቀድሞው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር ይህን ያሉት፤ዛሬ ለንባብ ከበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። “ከጠ/ሚኒስትር
መለስ ዜናዊ ሞት በኃላ አስተዳደሩን ከተረከበው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?” በማለት ጋዜጣው ላቀረበላቸው
የመጀመሪያ ጥያቄ አቶ ቡልቻ ፦” አዲስ አመራር አለን’ንዴ?”በማለት ነበር ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት።
ኢትዮጵያዊው አርሶአደር የእንግሊዝን መንግስት ሊከስ ነው
ኢሳት ዜና:-አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶአደር በእንግሊዝ የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ ድርጅት የሰብአዊ መብቴን ጥሶብኛል ሲሉ ነው ክስ ለማቅረብ የተነሳሱት ።
ሚስተር ኦ የተባሉት ሰው ለእንግሊዝ ጠበቆች እንደተናገሩት በመንደር ምሰረታ መርሀ ግብር የተነሳ ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል፣ ተገርፈዋል እንዲሁም አስገድዶ መድፈሮች ሲፈጸሙ ተመልክተዋል። የአርሶአደር ኦ ጠበቆች እንዳሉት የመንደር መስረታው መርሀ ግብር ከእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል።
የልማት ትብብሩ መስሪያቤት በበኩሉ ለሰፈራ መርሀግብሩ ገንዘብ አለመስጠቱን አስታውቋል። በስደት
ኬንያ ውስጥ የሚኖሩት በጋንቤላ የተወለዱት አርሶአደር ኦ የስድስት ልጆች አባት ናቸው። አርሶአደሩ ብዙ ሰዎች
መደብደባቸውን፣ሴቶች መደፈራቸውንና ተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ለጠበቆች ተናግረዋል።
Thursday, September 6, 2012
በአቶ በረከት ስምኦንና በህወሀት መካከል ያለው ፍጥጫ ተካሯል
ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት አቶ በረከት ስምኦን ፣ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት እንደተፈጸመ ፣
የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ስልጣን ፓርላማው በአስቸኳይ ተጠርቶ ያጸድቀዋል የሚል መግለጫ
መስጠታቸውን ተከትሎ የመንግስቱ የመገናኛ ብዙሀን አቶ ሀይለማርያምን ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ እስከመጥራት
ደረሱ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረትም አቶ ሀይለማርያም እስከ 2007 ዓም የጠቅላይ
ሚኒሰትርነቱን ቦታ በመያዝ ስራቸውን እንዲሰሩ ፈቅዷል። አቶ በረከት ብአዴኖች እና ኦህአዴዶች የሚበዙበትን
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመጠቀም እንዲተላለፍ ያስደረጉትን ውሳኔ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ ተጣድፈው በፓርላማ ለማጸደቅ
ሲሩዋሩዋጡ፣ የህወሀት ቡድኖች አካሄዱ ልክ አይደለም የሚል ቅሬታ በማቅረባቸው ጉዳዩ ከቀብር በሁዋላ እንዲታይ
ተወሰነ።
በአማራ ክልል የመንግስት ስራተኛዉ የወር ደሞዙን እንዲለግስ ተጠየቀ
አ ማ ራ ክ ል ል |
ኢሳት ዜና:-ሰራተኛው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀዱትን ልማት ለማስቀጠል በሚል ሰበብ የወር ደሞዙን በግድ እንዲለግስ እየተገደደ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። የመንግስት
ሰራተኛዉ በኑሮ ዉድነት እየተንገላታ ባለበት ባሁኑ ወቅት እንዲህ አይነቱን ውሳኔ ማስተላለፍ እጅግ የሚዘገንን ነው
በማለት አንድ የመንግስት ሰራተኛ ምሬታቸውን ለኢሳት ገልጠዋል። ከዚህ ቀደም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የከፈሉት
ገንዘብ አራቁቷቸው መሄዱን የገለጡት ሰራተኛው አሁን ደግሞ በድጋሚ ለግድቡ ማሰሪያ አውጡ መባሉን ሰራተኛው በሙሉ
እየተቃወመው መሆኑን ተናግረዋል።
ኢሳት በአውስትራሊያ የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አደረገ
ኢሳት ዜና:-አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን መርጃ እንዲውል በአውስትራሊያ ከተሞች ባካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከ 115 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ።
የሜልቦርን
ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ቡድን ባደረገለት ግብዣ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ባለፈው ኦገስት 12 ቀን አውስትራሊያ
የገባው ተወዳጁ አርቲስት፤ በአምስት የአውስትራሊያ ከተሞች ማለትም በሜልቦርን፣ በሲድኒ፣ በአድላይድ፣ በብሪዝበንና
በፐርዝ እንዲሁም በኒውዝላንድ-ኦክላንድ ባካሄዳቸው ደማቅ ዝግጅቶች በድምሩ ከ 115 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ
ለማሰባሰብ ችሏል።
Wednesday, September 5, 2012
የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መናሩ ነዋሪዎችን አስግቷል
በታምሩ ጽጌ
ምክንያቱ ባልታወቀና ነጋዴዎችም ሲጠየቁ ምላሽ መስጠት ፈቃደኛ ባልሆኑበት ሁኔታ፣ የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መናሩ ስጋት እንደፈጠረባቸው በተለይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፣ ከወር በፊት አንድ ኩንታል ማኛ ጤፍ 1‚450 ብር ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን
ዋጋው በጣም አሻቅቦ 2‚100 ብር መሸጥ ጀምሯል፡፡ አንዳንድ ነዋሪዎች ጤፍ ከሚመረትበት ቦታ ወይም በቀጣይ
የሚፈጠር ችግር እንዳለ በሚል ነጋዴዎቹን ሲጠይቋቸው፣ “ከፈለጋችሁ መውሰድ ትችላላችሁ አለበለዚያ ተውት”
እንደሚሏቸው ገልጸዋል፡፡
ወይዘሮ ቀለሟ ፈለቀ የሚባሉ ገበያተኛ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ውስጥ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በየሁለት ወሩ ግማሽ ኩንታል ማኛ ጤፍ ይገዙ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ግማሽ ኩንታል ማኛ ጤፍ የገዙት 725 ብር ነበር፡፡ ሰሞኑን ወደ ደንበኛቸው መደብር ሲሄዱ ዋጋው ባልጠበቁትና በሚያስገርም ሁኔታ ጨምሮ 725 ብር ይገዙት የነበረው ማኛ ጤፍ ወደ 1,050 ብር አሻቅቦ ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡
Tuesday, September 4, 2012
ፓትርያርክ ጳውሎስና ያስፈጇቸው ሊቃነ ጳጳሳት
ገብረ ኪዳን
የፓትርያርክ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ ፣ ታዋቂው ደራሲና ሰባኪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “ለምጣዱ ሲባል አይጧን ” በሚል ርእስ ፣ አጭር ግን ጠንካራ መልእክት ለመላው ኢትዮጵያውያን አስተላልፎ ነበር ። የጽሁፉም ዋና ጭብጥ አንድና ግልጽ ነው— ” ለቤተ ክርስትያኒቱ ክብር ሲባል ለተወሰኑ ቀናት ስለ ፓትርያርኩ ክፉ ስራና ደካማ ጎኖች የሚያትቱ ጽሁፎችም ሆነ ውይይቶች አንዲዘገዩ “
የሚማጸን ነበር ። ለቤተ ክርስትያኗ ክብር ሲባል መራሄ ቤተ ክህነቱ አቡነ ጳውሎስ ከበቂ በላይ የሀዘን (
ይገባቸዋል ብዬ ባላምንም) ስርአት ተካሂዷል ። እነሆ አሁን በዘመናቸው ስለተከናወኑ አሰቃቂና አስጸያፊ ወንጀሎች
እናውሳ።
ወ/ሮ አዜብ አቶ መለስን ለመተካት እየታገሉ ነው
ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለቤታቸውን በሞት ካጡ
በኃላ በእሳቸው እግር ተተክተው የህወሃትን የሊቀመንበርነት ቦታ ተቆናጥጦ ወደ ኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበርነት
ለመሳብ ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ላይ መክረማቸውን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡
በኢህአዴግ 36 የሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴ ውስጥ ብቸኛ ሴት ሆነው በመስከረም ወር 2003 ዓ.ም ከፍተኛውን የፓርቲ ሥልጣን በባለቤታቸው በአቶ መለስ
ዜናዊ ልዩ ድጋፍ ማግኘት የቻሉት ወ/ሮ አዜብ የሰሞኑን ሐዘናቸውን ለድጋፍ ማሰባሰቢያ እንደተጠቀሙበት ምንጮቻችን
ተናግረዋል፡፡
አቶ ሀይለማርያም ግልገል ጊቤ ሦስት በታሰበው ጊዜ አይጠናቀቅም አሉ
ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በቀጣዮቹ ዓመታት የሀይል እጥረት ያጋጥማል
የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለ ከአንድ ዓመት በሁዋላ ይጠናቀቃል ተብሎ እቅድ የተያዘለት የግልገል ጊቤ ሀይል ማመንጫ
ግንባታ በተባለው ጊዜ እንደማይጠናቀቅ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ።
በመስከረም 2006 ዓ.ም.
ይጠናቀቃል ተብሎ ዕቅድ የተያዘለት የግልገል ጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ግንባታ በወቅቱ እንደማይጠናቀቅ በመረጋገጡ፣
ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ ያስችላል የተባለ አዲስ ስትራቴጂ ተነደፈ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ይተካሉ ተብለው የሚጠበቁት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንደተናገሩት፣ ግልገል ጊቤ ቁጥር ሦስት በመስከረም 2006 ዓ.ም. አይጠናቀቅም፡፡
Monday, September 3, 2012
አቶ መለስ ዜናዊ ለትውልድና ለሀገራችን ጥለውት ያልፉት እኩይ፣ መራራና አሳዛኝ ሀቆች(ከፊሊጶስ)
የአቶ መለስ፣ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ግንኙነት ሁሌም ይደንቀኛል። በሀገርና በትውልድ ላይ የፈጸሙትንና
ጥለውት የሄዱትን ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሚትላልፍ መርዝ ሳስብ፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን የነበራቸውን ጥላቻ
ስቃኝ ፤በ’ርግጥ የሰው አዕምሮ ተመራምሮ ይደርስብት ይሆን? እላለሁ። አሁንም ከኢትዮጵያና ከዚች ዓለም ተለይተው
ሄደው ግፋቸውን ሳስታውስ እጅግ አድርጎ ይገርመኛል ። ዘፋኙ ምን ነበር ያለው?……’’….ግርም ያደርገኛል ያሰበኩት
እንደሆን ሰው በገዛ ሀገሩ ስደተኛ ሲሆን።….”እስቲ ባለፉት አመታት አቶ መለስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ
የሰሩትንና የፈጸሙትን መራራ ሀቆችና ለዚህ ትውልድ ጥለውት ያለፉትን ታሪክ እጅግ ባጭር ባጭሩ (የውቅያኖስን ውሀ
በጭልፋ ጨለፎ ለመጨረስ እንደመሞከር ይቆጠራል።) እናስታውስ።
Subscribe to:
Posts (Atom)