- ‹‹ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም››
ከትናንት በስቲያ ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ ዘ-ሐበሻ የዘገበችላቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከሐላፊነት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለዐቃቤ መንበሩ ማቅረባቸውን ምንጮቻችን ገለጹ። የዘ-ሐበሻ ምንንጮች እንደሚሉት ዋና ጸሐፊው ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ የወሰኑት ከጥር 6 እስከ ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተጠናቀቀ ነው ያሉት የዜና ምንጮቻችን “ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም” በሚል የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማቅረባቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል። እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ከሆነ ለሕሊናቸው ያደሩ እውነተኛ አባቶች የአቡነ ሕዝቄልን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚችሉ ያላቸውን ግምት ገልጸዋል።ውድ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ይህ ዘገባ ከደረሰን በኋላ ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ድረ ገጽ በአቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ዙሪያ የሚከተለውን ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Friday, January 18, 2013
የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ የተቃወሙት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ
ኢትዮቴሌኮም የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሰ መንጸባረቂያ መሆኑን የግንቦት ሰባት የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ አጋለጠ
የመረጃ ቴክኖሎጂ መሠረት የሆነዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ አፍሪካ፤ ላቲን አሜሪካና ኢሲያ ዉስጥ የሚገኙ በእደገት ወደ ኋላ የቀሩ አገሮችን ለዘመናት ከተዘፈቁበት የኋለ ቀርነት ማጥ
ዉስጥ ጎትቶ አዉጥቶ ወደ ፈጣን የእድገት ጎዳና ይወስዳቸዋል ተበሎ የታመነበትና በአንዳንድ አገሮች ዉስጥ ይህ
ለእድገት አመቺነቱ በተግባር የተመሰከረለት ዘርፍ ነዉ። ይህንን ጥናት በPDF ዳወንሎድ ለማድረግ ከዚህ ላይ ይጭሃኑ
ይህ ዘርፍ ገበሬዉ፤ ሰራተኛዉ፤ ተማሪዉ፤ ወታደሩና ለሌላም
በማንኛዉም የስራ ዘርፍ ለተሰማራ የህብረተሰብ ክፍል የእዉቀት ምንጭ በመሆን የስራ ምርታማነቱን እንዲያሳድግ
የሚረደና በህብረተሰብ መካከል ፈጣን የሆነ የመረጃ ልዉዉጥ አንዲኖር የሚያደርግ ዘርፍ ነዉ። በእድገት ወደ ኋላ
ለቀረችዉ አገራችን ኢትዮጵያም ይሀ ዘርፍ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ዘርፍ ነዉ። ነገር ግን በአፍሪካ ዉስጥ
አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ወደኋላ ከቀርችባቸዉና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ሆን ብሎ
እድገታቸዉ እንዲገታ ካደረጋቸዉ ኋላ ቀር ዘርፎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ይሄዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ ነዉ።
Monday, January 14, 2013
ቻይና በኢትዮጵያዊያን ላይ የምታደርሰው ሰቆቃ
ቻይና ከወያኔ ጋር በሚያደርገው የጠበቀ ግኑኝነት በኢትዮጵያ ያሉ ቻይናዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያደርሱት ሰቆቃ ለማመን የሚከብድ ነው። ቻይናዊያን በኢትዮጵያ በጣም ወጣት የሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ጉልበት መበዝበዝ (ባርነት) ፣ አስገድዶ መድፈር ፣ ማስር ፣ የአካል ጉዳት ማድረስ (ቶርቸር) እና እስክ መግደል ድረስ ስልጣን አላቸው። በዚህ ቪዲዎ ውስጥ ይህን የቻይናዊያንን ኢ-ሰባዊ ተግባራት የሚያረጋግጡ በኢሳት ራዲዩዎ ከሁለት ሰዎች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ይገኝበታል።
Sunday, January 13, 2013
አዲስ አበባ በህገወጥ ልማዶችና የወሲብ ድርጊቶች እየተናጠች ነው
ኢሳት ዜና:-እንደ አዲስ አድማስ ዘገባ፤ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ፖሊሶችና ነጋዴዎች የአነቃቂ እፆች ተጠቃሚ ናቸው ተባለ በአዲስ አበባ ህገወጥ ተግባራት የሚከናወኑባቸው ቤቶች በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ መምጣታቸውንና ከተማዋ አደጋ ላይ እንደሆነች ሰሞኑን ይፋ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት ይፋ የተደረገው ጥናት “መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች
በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም በወጣቶችና ሴቶች ላይ እያስከተሉት ያለው አሉታዊ ተጽእኖ” በሚል ርዕስ
የተካሄደ ሲሆን ከ3600 በላይ ህገወጥ የወሲብ ድርጊት የሚፈፀምባቸው ቤቶች እንዳሉ ጠቁሟል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)