ቤተልሔም ሰለሞን |
- አስከሬኗ ከመቃብር ወጥቶ ተገኝቷል
በታምሩ ጽጌ
የመጀመርያ ልጇን በቀዶ ሕክምና ከተገላገለች በኋላ ደም ፈሷት ሕይወቷ ያለፈው የ27 ዓመት ወጣት የቀብር
ሥርዓቷ ባለፈው ቅዳሜ፣ እሑድና ከትናንት በስቲያ ሰኞ የመፈጸሙ ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡
ሟች ቤተልሔም ሰለሞን ልጅ
ወልዳ ለመሳም ዘጠኝ ወራትን ስትጠብቅና የእርግዝናዋንም ሁኔታ ስትከታተል ቆይታ የመውለጃዋ ዕለት በመድረሱ፣ ጎፋ
ማዞሪያ ወደሚገኘው ሮያል የጽንስና የማኅፀን ሕክምና ከፍተኛ ክሊኒክ የሄደችው ኅዳር 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
ነበር፡፡