Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, October 31, 2012

በማረቃ ወረዳ የየኔሰው ገብሬ ጓደኛ የሆነው ወጣት ራሱን በአደባባይ ሰቀለ

Yenesew Gebre best Friend hang himself
ኢሳት ዜና:-በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል የሜዳሊያ ተሸላሚ  የነበረው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም ራሱን በአደባባይ ለመስቀል የተገደደው በአካባቢው ያለውን የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ እጦት በመቃወም መሆኑን ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ለኢሳት ገልጠዋል።

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ፣ በዳውሮ ዞን ፣በማረቃ ወረዳ ፣ በዋካ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም፣ በ1980 ዓም ነበር የተወለደው ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን 3 ነጥብ 8 በማምጣት  በአንደኝነት አጠናቆ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መግባቱንና የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

Tuesday, October 30, 2012

በኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ሀዲድ ላይ ከፍተኛ ሙስና የፈጸመው ኩባንያ በተመሳሳይ ወንጀልም ይፈለጋል ተባለ

Ethio-train construction
ኢሳት ዜና:-ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የውጭ አገር ዜጎች “ኢሳት የህወሀቱ መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ በሀዲድ አምራችነት የሚሳተፍበት የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድ ግንባታ በከፍተኛ ሙስና ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም” በሚል ርእስ በኢሳት የወጣውን ዜና ከተመለከቱ በሁዋላ በዜናው ላይ ማሻሻያ ያሉዋቸውን ነጥቦች በማከልና ኩባንያው በመላው አለም ስለሚፈጽመው ሙስና የሚያትት  በጣሊያንኛ ቋንቋ የተጻፈ መልእክት ልከዋል።

ከአውሮፓ ህብረት በተገኘው 41 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 1 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ጅቡቲ ያለውን 114 ኪሎሜትር የባቡር ሀዲድ ለማስገንባት ስምምነት ተፈርሞ የነበረ ቢሆንም ፣ ኮንስታ የተባለው ኩባንያ ሰርቶ ያስረከበው 24 ኪሎሜትር ብቻ መሆኑን፣ ይህም ቢሆን አገልግሎት ላይ አለመዋሉን ጠቅሷል።

ኢትዮጵያ ለግብጽ አንድ ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር መሬት ልትሰጥ ነው

ኢሳት ዜና:-እየተገነባ ባለው የህዳሴው ግድብ ሳቢያ ግብጽ ችግር ልትፈጥርብን ትችላለች የሚል ስጋት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊ ሚዲያዎች ሲስተጋቡ  ቢሰሙም፤ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር  ግን በተቃራኒው  በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለው የልማት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱን ነው ይፋ ያደረጉት።

የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሺም ካንዲ በቅርቡ በአልጀሪያ ባደረጉት የሁለት ቀናት ጉብኝት ላይ ፤አገራቸው ፤ በአልጀሪያና በኢትዮጵያ ሁለት የኢንዱስትሪ  ዞኖችን ለመገንባት ማቀዷን አስታውቀዋል። የግብጽ የማስታወቂያ ሚኒስቴር እንዳለው ፤ግብጽ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር  2014 ዓም ከመድረሱ በፊት በ አልጀሪያ 2 ጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ይፋ አድርገዋል።

የሚኒሰትር ጁኔዲን ሳዶ ባለቤት ፍርድ ቤት ቀረቡ

ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችና ኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ ክስ ከመሰረተባቸው ሰዎች መካከል አንዷ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትሩ ባለቤት የሆኑት 28ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሀቢባ ሙሀመድ መሆናቸው ታውቋል።

አቃቢ ህግ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ክስ መሰረተ

ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛር ከጧቱ 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችናኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ ተምልክቷል።

ብርሀኑ ወንድማገኘሁ ፣ ዘረሰናይ ምስግናው እና ቴዎድሮስ ባህሩ አቃቢ ህጎች ሆነው የቀረቡ ሲሆን ለተከሳሾች ማለትም ለ29 ግለሰቦችና ሁለት ግብረሰናይ ድርጅቶች ጠበቃ ሆነው የቀረቡት ደግሞ አቶ ተማም አባቡልጋ፣ አቶ ብርሀኑ ፣ አቶ ሞሀመድ አብደላና ናቸው።

Sunday, October 28, 2012

አርበኞች ግንባር በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ የተሳካ ወታደራዊ ማጥቃት አካሄደ

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በጥቅምት 15-2005 ዓ.ም ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊትና ሚሊሻ ጋር በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ልዩ ስሙ ዳንጉራ በሚባል ስፍራ በወሰደው

ድንገተኛ ወታደራዊ ማጥቃት አስር(10) የስርዓቱን ቅጥረኛ ወታደሮች በመግደልና አምስት (5) በማቁሰል በአናሳው ቡድን የሃይል ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ድልን ተጎናጽፏል።

በእለቱ በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረው ነበልባል ሻምበል በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃትና በተመዘገበው ድል በአካባቢው የሚኖረው ማህበረሰብ አንጀቱ መራሱንና ወያኔው በአሁኑ ወቅት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እያወረደ በሚገኘው የጅምላ ጭፍጨፋና እስራት በንፁሃን የሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮች ውስጥ በሃይማኖት ጉዳዮች በመግባት የእምነቱ መሪዎችን ፣ የእምነቱ አግልጋዮችና አዳሪዎች ሳይሆኑ በሃይማኖት ሽፋን የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ አስተጋቢዎችና የፖለቲካ ሹሞች መሆን ይኖርባቸዋል በማለት እብሪተኛው ቡድን የራሱን ሰዎች የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲሆኑ ያለ የሌለ ሃይሉን በመጠቀም የሃይማኖት ነፃነት ያስጠብቃል ተብሎ የወጣው የይስሙላ ሕገ-መንግስት የሰጠውን መብት እንኳን ሕዝበ-ሙስሊሙ ሊከበርለት አልቻለም።

በእስራኤል የተደበደበው የሱዳን ሚስጢራዊ የጦር መሣሪያ ፋብሪካ ለኢትዮጵያ ሥጋት መሆኑ ተጠቆመ

Sudan weapon factory

ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት ከሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በስተደቡብ የሚገኘው ሚስጥራዊ የጦር መሣርያ ፋብሪካ በእስራኤል የሚሳይል ጥቃት እንደተፈጸመበት ከታወቀ በኋላ፣ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ሥጋት መሆኑን ዜጎችና የፖለቲካ ተንታኞች እያስረዱ ነው፡፡

እስራኤል በዚህ እጅግ ሚስጥራዊ ነው በተባለለት ወታደራዊ የጦር መሣርያ ፋብሪካ ላይ ጥቃቱን የፈጸመችው በቅርቡ በሒዝቦላህ የተላከባት ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን (Drone) ግዛቷ ውስጥ መትታ ከጣለች በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡ የእስራኤል ወታደራዊ ባለሥልጣናት ሰው አልባው የጦር አውሮፕላን የተመረተው በካርቱም የጦር መሣርያ ፋብሪካ ውስጥ መሆኑን፣ በግብፅ በኩል ተጓጉዞ ለኢራን ከደረሰ በኋላ ሊባኖስ ውስጥ ለመሸገው ሒዝቦላህ መሰጠቱን መግለጻቸው በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኅን ተገልጿል፡፡