ከዚህ
በፊት ታማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮች ባገኘነው መረጃዎች ላይ ተመስርተን ባስነበብናቸው የተለያዩ ዘገባዎች
ኮሚቴዎቻችንና ሌሎች ታሳሪ ወንድሞቻችን ላይ በማዕከላዊ የደረሰባቸውን ግፍና ሰቆቃ በመጠኑ ለማስቃኘት ሞክረናል፡፡
ዘወትር ሰላምን ሲሰብኩና መቻቻልን ሲያስተምሩ የኖሩትን ኮሚቴዎቻችንንና ዓሊሞቻችንን በግድ የሽብር ድርጊት
ልትፈጽሙና ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ስትንቀሳቀሱ እንደነበር የሀሰት ቃል ስጡ በሚል አንድ ኢትዮጵያዊ የራሱ
ወገን የሆነ ኢትዮጵያዊ ላይ ያደርሰዋል ተብሎ የማይታሰብ አረመኒያዊ ድርጊት ፈጽመውባቸዋል፡፡
ከነዚሁ ታማኝ ምንጮች
የደረሰን ተጨማሪ መረጃ ደግሞ እነዚህ ተርቦ እንደተለቀቀ አንበሳ ደም የጠማቸው የማዕከላዊ መርማሪዎች እነማን እንደሆኑና ሲያደርሱባቸው የነበረው ሰቆቃ ምን ይመስል እንደነበር ዘርዘር ባለ ሁኔታ ያሳያሉ፡፡
ኮሚቴዎቻችንና ዳዒዎቻችን ከዚህ በፊት ከጠቀስናቸው ለረዥም ቀናት በጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል ማቆየት፣ እርቃናቸውን በማድረግ መግረፍ ፣ ለረዥም ሰዐታት ያለ እረፍት ማቆም… በተጨማሪ ሞትን የሚያስናፍቁ በርካታ ኢሰብአዊና አረመኒያዊ ተግባራት ሲፈጸምባቸው እንደቆየ ማወቅ ተችሏል፡፡
በተለይ ደግሞ በተከበሩት የረመዳን የመጨረሻዎቹ ሌሊቶች
ለተከታታይ ቀናት ከቤተሰብ የሚመጣላቸውን ምግብ በመከልከልና በረሃብ ከመቅጣት አንስቶ ኤልክትሪክ ወንበር ላይ
አስቀምጦ እስከማሰቃየትና በግድ ‹‹ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት እንሰራ ነበር›› ብላቹህ ፈርሙ እስከማለት የደረሰ
የሽፍታ ስራ ሲሰራባቸው ቆይቷል፡፡ የውስጥ እግራቸውና ሰውነታቸው በደም እስኪጨማለቅ ድረስ ገልብጦ የመግረፍና
ስለታማ ነገሮች በተበተኑበት መሬት ላይ በባዶ እግር በጨለማ እንዲሄዱ የማድረግ ጭካኔ የተሞላበት ቅጣት
አስተናግደዋል፡፡
ከሁሉ በከፋ ሁኔታ ደግሞ አንዳንዶቹን እርቃናቸውን በማድረግ ብልታቸውን ለይቶ በመግረፍ እንኳን
ለመፈጸም ለማሰብ እንኳ የሚዘገንን ግፍ ፈጽመውባቸዋል፡፡ መሪዎቻችንን እና ወንድሞቻችንን ከብረት በተሰሩ ሰውን
እንደሳንድዊች መሃል አስገብተው በሚጨፈልቁ ዘመናዊ መሳሪያዎች ውስጥ አስገብተው በመኖርና መሞት መሃል የሚከቱ
ቅጣቶችን አስተናግደዋል፡፡
በነዚህ ሁሉ ቅጣቶች መሀል ‹‹ኢስላማዊ መንግስት ለመመሰረት እንሰራ ነበር›› ብላችሁ
እመኑ ለሚለው ጥያቄ የሚሰጡ መልሶች ሁሉ ይመዘገቡና እንዲሁም በድብቅ ካሜራ እየተቀረጹ በአሳፋሪው የጸረ ሽብር ህግ
አንቀጾች መሰረት መልሶ ቢካድ እንኳን በፍርድ ቤት ተቀባይነት በማያገኝበት ሁኔታ በመረጃነት ይቀርባሉ፡፡ ይህ ነው
እንግዲህ አገራችን የደረሰችበት የፍትህ ደረጃ! በዚህ መሰሉ ህግ ነው ኮሚቴዎቻችንን ለመዳኘት የታሰበው!
ይህን መሰሉን በደል ሲፈጽሙ የነበሩ የማዕከላዊው አረመኔዎች አሳፋሪ ማንነታቸውን ለመደበቅ ይህን አሳፋሪ ድርጊታቸውን በሚፈጽሙበት ዐለማቸው ሌላ ስም፣ ውጪ ደግሞ ሌላ ስም የሚጠቀሙ ሲሆን በአላህ ፈቃድ ግን ትክክለኛ ስማቸውን ለማግኘት ተችሏል፡፡ እነዚሁ ግለሰቦች ዛሬ ላይ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት በማን አለብኝነት ቢፈጽሙትም ነገ ግን በሌሎች አገራት የቅርብ ታሪክ እንዳየነው ሁሉም ፍትህ ፊት የሚቀርቡበት ቀን መምጣቱ የማይቀር በመሆኑና ህዝብም እነዚህን ሁለት ፊት ያላቸው ግለሰቦች ማወቅ ስላለበት የጥቂቶቹን ትክክለኛ ስም ቀጥሎ ይፋ እናደርጋለን፡፡
1.ኮማንደር ተክላይ፡- ግርፋትና ሌሎቹም ማሰቃያዎች እንዲፈጸሙ በዋነኛነት ትዕዛዝ የሚያስተላልፍና ሲፈጸምም ቁጭ ብሎ የሚመለከት፤
2. ምክትል ከማንደር ከተማ፡- የኮሚቴዎችን ቃል ቶርች እያስደረገ የሚቀበል፤
3. ሳጅን ርዕሶም፡- ኮሚቴዎቻችን ና ወንድሞቻችንን በፎጣ እና በእስካርፍ ፊታቸውን አፍኖ በመውሰድ በኤሌክትሪክ ወንበር እንዲሰቃዩ የሚያደርግ፤
4. ዩሱፍ (ሙስሊም ነው ይባላል) ፡- ከባድ ድብደባ የፈጸመባቸውና እና ከሌሎች በተለ የመልኩ ስቃይ እንዲደርስባቸው የሚያደርግ፤ አሳፋሪ ስድቦችን በመሰንዘርም ሲያሸማቅቃቸው የነበረ፤
እንዲሁም የተለያየ ሚና የነበራቸው
5. አለማየሁ
6. ፀጋዬ
7. ዘመድኩን
8. አብዮት የተባሉ ግለሰቦች ይገኙበታል፡፡
እነዚህ ግለሰቦች ዛሬ በሚያነክሰው የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት ተከልለው ይህን ድርጊት ቢፈጽሙም በዚህ ድርጊታቸው ፍትህ ፊት የሚቀርቡበት ጊዜ ግን ሩቅ እንደማይሆን ምንም ጥርጥር የለንም፡፡ ይህ እውን እንደሚሆን ደግሞ በሌሎች አገሮች ብቻ ሳይሆን በአገራችንም ተፈጽሞ ያየነው እውነት ነው፡፡

እነዚህ ግለሰቦች የትም አገር ሄደው ቢከለሉ፣
በየትኛውም መልኩ ራሳቸውን ሊሸሽጉ ጥረት ቢያደርጉ የወንድሞቻችን ደም ተከትሏቸው እንደሚሄድ በደምብ ሊገነዘቡ
ይገባል፡፡ እንደ አይናችን ብሌን የምንሳሳላቸው መሪዎቻችን ላይ የፈጸሙትን አረመኔያዊ ድርጊትም መቼም ቢሆን
ከአእምሯችን አይፋቅም፡፡ ይህ ቃላችን ነው፡፡
Source: Face Book/Zubayr Peace
አላሁ አክበር!
No comments:
Post a Comment