Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, November 13, 2012

ኢትዮጵያ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አባል ሆና መመረጡዋ ተተቸ

United Nations human right
ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰሞኑን ባካሄደው ምርጫ አስከፊ ሰብአዊ መብቶችን ጥሰት የሚፈጽሙ በርካታ አገሮችን መምረጡ በሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ትችት ቀርቦበታል።

የሰብአዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅቶች እንዳሉት ሰኞ እለት ከተመረጡት 18 አገሮች መካከል መስፈርቱን የሚያሟሉ አገሮች ሶስት ብቻ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ለአፍሪካ 5 መቀመጫዎችን የሰጠ ሲሆን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ኬንያና ሴራሊዮን ለቦታው ተመርጠዋል። ጃፓን ፣ ካዛኪስታን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ፓኪስታንና ዩናይትድ አርብ ኤምሬትስ ደግሞ የኤስያ ፓስፊክ አገሮችን መቀመጫዎች ወስደዋል። 


አርጀንቲና፣ ብራዚልና ቪንዙዌላ ደግሞ የላቲን አሜሪካና የካረቢያን አገሮችን መቀመጫዎች ወስደዋል። የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቡድን አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ካዛኪስታን፣ ፓኪስታን፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና ቪንዙዌላ የሰብአዊ መብት አያያዝ ችግር ያለባቸው አገሮች ናቸው ብሎአል።

የሂውማን ራይትስ የተመድ ዳይሬክተር የሆኑት ፊሊፒ ቦሎፒዮን ኢትዮጵያን አስከፊ ሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነጥለው በማውጣት ተችተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ይህን እድል በመጠቀም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የመደረጃት መብቶች እንዲከበሩ፣  የጸጥታ ሀይሎች በሚፈጽሙት የሰብአዊ መብት ጥሰት በህግ ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር እንዲጀምር፣ እንዲሁም አሁን አባል እንዲሆን ለተመረጠበት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ቀና ትብብር እንዲያሳይ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። 

አዲሶቹ ተመራጭ አባላት ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ያገለግላሉ። አሜሪካና ጀርመንም እንዲሁ የአብአዊ መብት ጉባኤው አባላት ሆነው ተመርጠዋል።ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብቶች አያያዙዋ በተደጋጋሚ እንደምትተች ይታወቃል። በአገሪቱ ዜጎች ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ለሚፈጽሙት ጥቃት እስካሁን ድረስ ህግ ፊት ቀርበው ሲቀጡ አልታየም።

No comments:

Post a Comment