Torturing |
ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ
የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን
ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ
አድርገዋል።
የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊውና ፖሊሶች በመቀጠልም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር
ካስደረጉ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም
ብልቱን እንድትስም አስደርገዋል። በእርግጫ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጅ አስወርዳለች። በድርጊቱ አልሳቃችሁም
የተባሉትም ተደብድበዋል።
ድርጊቱ ይፋ የሆነው አቶ ይመሩ በተባሉ የቀበሌው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ ሲሆን፣ ድርጊቱንም ይፋ ያደረጉት የዞኑና የወረዳው ባለስልጣናት በተሰበሰቡበት ወቅት ነው።
ኢሳት ጥቆማው እንደደረሰው በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን አንድ የወረዳው ባለስልጣንን አነጋግሯል፡፤ ባለስልጣኑ ስማቸው እንዳይጠቀስባቸው በመግለጽ ስለ ተፈጸመው ድርጊት በዝርዝር አስረድተዋል። የፖሊስ ምርመራ ክፍል የሀኪም ማስረጃዋን ለመቅደድ መሞከሩንና ድርጊቱም በተራው የኢህአዴግ አባላት ውስጥ ቁጣ መፍጠሩንም ባለስልጣኑ ተናግረዋል ።
ይህ ግለሰብ ባሂት በሚባለው ቀበሌ ደግሞ አንድን ግለሰብ በችቦ ማቃጣሉን ባለስልጣኑ ተናግረዋል:: የወረዳው የፍትህና አስተዳዳር ሀላፊ ከድርጊቱ ጀርባ እጁ እንዳለበትም ባለስልጣኑ ተናግረዋል::
ግለሰቡ በማዳበሪያ እና በሌሎችም ምክንያቶች እያሳበበ አባዎራዎችን ወደ እስር ቤት በመወርወር እርሱና ጓደኞቹ ሚስቶቻቸውን እንደሚደፍሩም ታውቋል።
ግለሰቡ ቀደም ብሎ በሰራው ወንጀል ተከሶ የነበረ ቢሆንም፣ ያለምንም ቅጣት ተለቆ በሀላፊነቱ ላይ እንዲቆይ መደረጉ ታውቋል።
ጉዳዩን
በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ መስፍን ታየ ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው ፣
የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊው በህግ ስር ውሎ ጉዳዩ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል። ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንዲሰጡን
ብንጠይቃቸውም ስልኩን ዘግተውታል።
የደራ ወረዳ ባለስልጣናት ከፍተኛ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸውንም
የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በወረዳው ውስጥ ለአርሶ አደሩ ማሰልጠኛ ተብሎ የተለቀቀ 800 ሺ ብር ፣ ሰዎች
ለሰዎች የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አካባቢውን ለቆ ሲወጣ ትቶአቸው ከሄዱ እቃዎች ሽያጭ የተሰበሰበ 1
ሚሊየን 700 ሺ ብር እንዲሁን ለወረዳው እየተባለ የሚለካው መድሀኒት ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ በወረዳው
ባለስልጣናት እንደሚቸበቸብ ታውቋ ማጣሪያ ከተደረገ በሁዋላ፣ ከፍተኛ ሙስና በፈጸሙት የዞኑ ባለስልጣን በአቶ
ሰለሞን መኮንን ትእዛዝ የምርመራ ሰነዱ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ተደርጓል።
ደራ ወረዳ የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ወይም ኦፒዲዮ የተመሰረተበት ቦታ ነው። አካባቢው በኦሮሚያ ክልል ስር የሚገኝ ሲሆን፣ ከኦሮሞ በተጨማሪ የአማራ ተወላጆችም ይኖራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየከፋ ቢሄድም መንግስት ምንም እርምጃ ሲወስድ አይታይም።
No comments:
Post a Comment