ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም, የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ነው።
መንግሥታዊው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ሃሙስ ምሽት ሳንሱር አድርጎ አላትምም ብሎ ያቋረጠውን የፍትህ ጋዜጣ
ቅጽ 5 ቁጥር 197 ፣ ከፌዴራል ጸረ ሽብር ግብረይል፣ ዐቃቤ- ሕግ፣ የደህንነት ኃይሎች እና ከፍትህ ሚንስትር
ተወካዮች ጋር ከተነጋገረና ይዘቱን ካስገመገመ በኋላ ትላንት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በደህንነት ኃይሎች ቅርብ
ክትትል ሥር ሆኖ ጋዜጣው እንዲታተም ቢፈቅድም ፣ በዛሬው ማለዳ ለሥርጭት እንዳይውል አድርጓል።