የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ በሰሜን አሜሪካው የሰላምና አንድነት ኰሚቴ አስተናጋጅነት፣
፫ኛውን እርቀ-ድርድር ባለፈው ረቡዕ ዳላስ፣ ቴክሳስ ውስጥ መጀመራቸው፤ ለዚሁ ውይይት፣ ያዲሳባው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬
ልዑካን፣ የስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬ ልዑካን እየተሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል። ምን ላይ ናቸው? እስካሁን የሰማንው
ነገር የለም፣ ደውለን ለማግኘት ያደረግንው ጥረትም አልተሳካም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ማክሰኞ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ከኢትዮጵያው ፕሬዚደንት ግርማ
ወልደ-ጊዮርጊስ የተጻፈ «ከሙሉ ክብርዎና ሥልጣንዎ ወደ አገርዎ ገብተው መንበርዎ ላይ እንዲሆኑ» የሚል፣ ፊርማቸውና
ቲተራቸው ያረፈበትን፣ በኋላም እራሳቸው ያረጋገጡትን ደብዳቤ፣ በኋላ ደግሞ በራሳቸው አንደበት ተሰርዞ «በማያገባኝ
ነበር የገባሁት» ያሉበትን ማሰማታችንና ማስተላለፋችን ይታወሳል።
ብፁዕ አቡነ ናትናዔል |
ቅዱስ ሲኖዶሱ ‘አቡነ መርቆርዮስ ቀደም ሲል በተወሰነላቸው መሠረት መመለስ ይችላሉ’ አለ::
No comments:
Post a Comment