Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Saturday, September 22, 2012
በቂ የውጪ ምንዛሬ ያለው በወጋገን ባንክ ብቻ ነው ተባለ
ኢሳት ዜና:-የአገሪቱ ባንኮች በውጪ ምንዛሬ እጥረት በተጠቁበት በአሁኑ ጊዜ የወጋገን ባንክ ደንበኞች ብቻ ያለምንም እጥረት ንግዳቸውን እያቀላጠፉ መሆናቸው ተጠቆመ።
የአይ.ኤም.ኤፍ
የ ኢትዮጵያ ተወካይ አገሪቱ ለሁለት ወራት የሚበቃ የውጪ ምንዛሬ እንዳላት በቅርቡ ቢገልጹም ዋናውን ንግድ ባንክ
ጨምሮ በ አገሪቱ የሚገኙ ባንኮች በሙሉ በከፍተኛ እጥረት በመጠቃታቸው ደንበኞቻቸውን ማገልገል እንደተሳናቸው
የአዲስ አበባ የ ኢሳት ወኪሎች ከተለያዩ ባንኮች ያሰባሰቧቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።
አቶ መለስ ዜናዊ ሞተውም በከፍተኛ እጀባ እተጠበቁ ነው
ኢሳት ዜና:-አራት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ለተቀበሩት ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ መለስ ዜናዊ ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ፡፡ ኢትዮጵያ
ውስጥ እንዳይታተም ቢከለከልም “ኦን ላይን” ጋዜጣ በመሆን በኢንተርኔት ስርጭቱን የቀጠለው ፍኖተ-ነፃነት
እንደዘገበው፤ አቶ መለስ ከተቀበሩ በኋላ ባልተለመደ ሁኔታ የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በሮች የተቆለፉ ሲሆን፤
መቃብራቸው በተለየ ኃይል ልዩ ጥበቃ እየተደረገለት ነው፡፡
Sunday, September 16, 2012
በሐሰት ወሬ ሕዝብን ለአመፅ አነሳሳ የተባለ ግለሰብ በአንድ ዓመት እስራት ተቀጣ
By reporter: የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ የወንጀል ችሎት፣ በመንግሥት ላይ ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ሕዝብን በሐሰት ወሬ አነሳስቷል የተባለውን ግለሰብ፣ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጠ::
ወታደራዊ ሚስጥሮችን ለኦነግና ለኤርትራ አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተከሰሱ
አገርን አደጋ ላይ የሚጥል ሚስጥር አሳልፈው መስጠታቸው ተጠቁሟል::
በሚስጥር የሚጠበቁና በሕዝብ በይፋ የማይታወቁ ወታደራዊ ሚስጥሮችን ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እና ለኤርትራ የደኅንነት ሠራተኞች አሳልፈው ሰጥተዋል በሚል የተጠረጠሩ ሁለት መከላከያ ሠራዊት አባላትና ሁለት ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው::
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
ኢሳት ዜና:-ከተጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን የያዘውና180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጉባዔ በሞት በተለዩት
የግንባሩ ለቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ የብአዴኑን
ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል አድርጎ መምረጡን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡
ጉባዔው በዛሬው ውሎው በገጉት
ሲጠበቅ የነበረውን የግንባሩን ሊመንበር ምርጫ ያከናወነ ሲሆን አዲሱ ተመራጭ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ምንጫችን እንዳለው በኢህአዴግ የእስከዛሬ ልምድ ግንባሩ ሊቀመንበር
ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆን ጠቁሞ ይህ ግን ተለምዶያዊ አሰራር እንጂ ሊቀመንበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል የሚል
በግንባሩ መተዳደሪያ ደንብም ሆነ የመንግስት ሕግ አለመኖሩን አስታውሶአል፡፡በዚህ መሰረት ግንባሩ ከሊቀመንበሩ ከአቶ
ኃይለማርያም ውጪም ሊመርጥ የሚችልበት ዕድል ዝግ አለመሆኑን ያስታወሰው ምንጫችን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን
የአቶ ኃይለማርያም መሾም አጠራጣሪ አለመሆኑን አመልክቶአል፡፡
የፋና ራዲዮ ዘገባ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን አስቆጣ
ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ኢንዶውመንት ድርጅቶች አንዱ እንደሆነ የሚታወቀውና ራሱን “የግል ራዲዮ ጣቢያ”
በማለት የሚጠራው ራዲዮ ፋና “ኢትዮፒካሊንክ” በሚል ርእስ በኤፍ ኤም የሚያሰራጨው ፕሮግራም ከአቶ መለስ ዜናዊ፤
ዜና ዕረፍት ዘገባ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ቁጣ ታገደ፡፡
አቶ መለስ፤ ዜና ዕረፍታቸው በይፋ በመንግስት
ከተነገረ በኃላ እስከቀብር ዕለት ድረስ የጣቢያው መደበኛ ፕሮግራሞች ታጥፈው የነበረ ቢሆንም የኢትዮፒካሊንክ
አዘጋጆች ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2004 ዓ.ም ከአቶ መለስ ሕልፈተ ሕይወት ጋር በተያያዘ ልዩ ፕሮግራም እንዳላቸው
በመግለጽ ጣቢያውን አስፈቅደው ያስተላለፉት ፕሮግራም በተለይ የአቶ መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን
አስቆጥቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን እስረኞች በአስከፊ የስቃይ ሁኔታ እንደሚገኙ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች አጋለጡ
ኢሳት ዜና:-የታሰሩት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች በአስከፊ የስቃይ ሁኔታ እንደሚገኙ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች አጋለጡ።
ባለፈው
ዓመት ሐምሌ ወር ወደ ኦጋዴ ክልል በመግባት በአካባቢው እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቅረጽ ሲሞክሩ
በታጣቂዎች ተይዘው ላለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ከታሰሩ በሁዋላ ሰሞኑን የተለቀቁት ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች
ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በኢትዮጵያ እስር ቤት በእስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት
አስከፊ መሆኑን ገልጸዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)