Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, November 28, 2012

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ላለመውሰድ ወሰኑ

ኢሳት ዜና:-በ2005 ዓ.ም ለሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማና የአካባቢ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፓርቲዎች ጋር ለመነጋገር በአዳማ ከተማ ምርጫ ቦርድ በጠራው ስብሰባ ፒቲሽን የተፈራረሙት የ34 ፓርቲዎች ህብረት፤ የምርጫ ችግሮች ሳይፈቱ  የመወዳደሪያ ምልክታቸውን እንደማይወስዱ በአንድ ድምጽ መወሰናቸው ታወቀ፡፡


34ቱ ፓርቲዎች  የምርጫ ምልክት ላለመውሰድ የወሰኑት ፤ ህዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በመላው  ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ጽ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ  ነው።

የ34ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የአንድነት ፓርቲ  ዋና ፀሐፊና የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ በጉዳዩ ዙሪያ ፍኖተ-ነፃነት ላቀረበላቸው  ጥያቄ በሰጡን መልስ፦ “እውነት ነው፡፡ ህዳር 8 ቀን 2005 ዓ.ም  በመኢአድ ጽ/ቤት ተሰብስበን ነበር፡፡

ያለፈው ስብሰባ ቃለ ጉባኤ  ተነቦና መጠነኛ መሻሻል ተደርጐበት ፀድቋል>>ብለዋል። ሰነዱ የሁሉም ፓርቲዎች ሰነድ ሆኖ እንዲፀድቅ  መደረጉን የጠቀሱት አቶ አስራት፤ የኮሚቴው የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት እንደቀረበና    ውይይት እንደተደረገበት፤ እንዲሁም ኮሚቴው  በአጭር ጊዜ ውስጥ ባከናወናቸው ተግባራት አድናቆትን እንዳገኘ ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ  ምርጫ ቦርድ ፀሐፊ አቶ ነጋ ጠርተው  ሲያነጋግሯቸው፦<< ተፈራርማችሁ ባታመጡም ቦርዱ ፓርቲዎችን ለማወያየት እቅድ ይዞ  ነበር፡፡ ይህንን ያህል ማጯጯህ ለምን አስፈለገ? የቦርዱ ሰብሳቢና ም/ሰብሳቢ ከአገር ውጪ ስለሄዱ ነው፡፡ ሲመጡ ያነጋራችኋል” እንዳሏቸው ጠቅሰዋል፡፡

<< እኛ ደግሞ ለምን እንደ ጮህን  በ2002 ዓ.ም የተደረገውን  የዝርፊያ ምርጫ በመጥቀስ  ነግረናቸዋል>>ያሉት አቶ አስራት <<ከዚህም በላይ  ብዙ ማለት እንደሚቻል አስረድተናቸው ተመልሰናል” ብለዋል።

በተያያዘ ዜና በሞት፣ አንድነት ፓርቲ በሥራ ዝውውርና በተለያየ ምክንያት በተጓደሉ የብሔራዊ ም/ቤቱ አባላት ምትክ ዘጠኝ አመራሮችን  ተክቷል፡፡

ከተተኩት ውስጥ አምስቱ ተለዋጭ  አባላት የነበሩ ሲሆኑ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ለብሔራዊ ም/ቤቱ በሚሰጠው ሥልጣን መሠረት አራቱ በቀጥታ ከአባላት  ተመርጠው ብሔራዊ ም/ቤቱን ተቀላቅለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment