|
ገብረመድህን አርአያ |
ገብረመድህን አርአያ (ተጻፈ ሚያዝያ 6, 2004 ዓ.ም.)
ለአንድ
ሰሞን ለአመታት በአሜሪካኗ ግዛት ኦሃዮ ውስጥ በስደት ሲኖር የነበረው የወያኔ ነባር ታጋይ፣ በስለላ የሰለጠነ …
እና መሪህ ባኽታ ብስራት አማረ የጻፈው መጽሃፍ በህትመት ወጥቶ ጉድ፣ ጉድ ከተባለለት በኋላ እኔም እንደ
ኢትዮጵያዊነቴ እና እንደ ቀድሞ የህወሃት ቀዳሚ ታጋይነቴ መጽሃፉን አግኝቼ ለማንበብ እና የግሌን ግምገማ ለማድረግ
መፈለጌ አልቀረም። ዘግይቶም ቢሆን መጽሃፉ በእጄ ገብቶ የማንበብ እድል አገኘሁ። መቼም ጉድ ነው የሚባለው!!
ህወሃት እና በዙሪያው የከበቡት ጉዶች የቅጥፈት እና የክህደት ጉድ ማለቂያ የለውም።
ይህ
መጽሃፍ በተከታይ እትም ሊታረም የሚችል ግድፈት አይደለም የተሸከመው፤ እንደዚህ በአገጠጠ ውሸት፣ በህወሃታዊ
የታሪክ ክህደት፣ በጥላቻ እና በተንኮል የታጨቀ መጽሃፍ አይቼም፣ አንብቤም አላውቅም። ብስራት አማረ ታሪክ ለዚያውም
በጣም የቅርብ ጊዜ ታሪክ አንድ ሰው እንዳሻው ስለጻፈው የመጨረሻው እውነት ሆኖ ይቆያል ብሎ ያምናል። ይህ
አስተሳሰብ ላዩን ሲያዩት በጣም ገራገር ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በጊዜ አስፈላጊው የእርምት እና የማጋለጥ
እርምጃ ካለተወሰደ የኋላ ኋላ ብዙሃን እንደ እውነተኛ ታሪክ እና ትንታኔ ዋጋ ሰጥተው ሊያዩት ይችሉ ይሆናል።