ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ እንደቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የኦሮሞ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት አሁንም በችግር እየታመሰ ነው፡
Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Friday, November 16, 2012
በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱ ተነገረ
ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱን ጮህቱም ሰሚ ማጣቱን አንዲት የመንግስት ባለስልጣን ገለጹ።
ሥለችግሩ ብናነሳም የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ምን አገባችሁ በሚል መሳለቂያ ያረጉናል ሲሉም ምሬታቸውን ሲገልጹ
በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ታይተዋል።
አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያ የመደራጀት መብትን አግዳለች አለ
ኢሳት ዜና:-አለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያን የማህበራትን የመደራጀት ነጻነት ከገደቡ ቀንደኛ 5 ሀገራት አንዶ መሆኖን አስታወቀ።
ጄኔቫ
የሚገኘው አለም አቀፉ የሰራተኞች ማህበር ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳስታወቀው የመሰባሰብና የመደራጀት ነጻነት
ካፈኑና አደገኛና ፍጹም የሆነ ገደብ የጣሉ ሲል ካወጣቸው 32 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ካምቦዲያ፣ ፊጂ፣
አርጀንቲናና ፔሩ በዋነኝነት አስቅቀምጦቸዋል።
የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ
ኢሳት ዜና:-በሀና ማሪያም አካባቢ መንግስት የሚያደርገውን መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ
አስፈፃሚ የሆኑ የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው
ተዘገበ።
በደራ ወረዳ በአንዲት ሴት ላይ የተፈጸመውን ግፍ በይፋ ያጋለጡት የቀበሌው ሊቀመንበር ቃለምልልስ ሰጡ
ኢሳት ዜና:- በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ
የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን
ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ
ማድረጉን፣ እንዲሁም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ከተደረገ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን
የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም ብልቱን እንድትስም ማስደረጉን እንዲሁም የመንግስት ሹሙ
ግለሰቡዋን በእርግጫ በመምታቱ የስድስት ወር ልጅ እንድታስወርድ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።
Thursday, November 15, 2012
የ”ጉዞ ኃይለማሪያም” አንድምታ
“ቤተመንግስት ለመግባት፤መለስ ልብ መግባት”
ከጥበቡ ግርማ ሙላቱ
ጥቅምት 10 2005 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው የሪፖርተር ጋዜጣ ልዩ ዕትም ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኋላ ታሪክ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡ የዘገባውን ተኣማኒነት ለማጎልበት ጋዜጣው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቀድሞ የሥራ ባልደረቦችንና ወዳጆች አግኝቶ ለማነጋገር ብዙ የደከመ ይመስላል፡፡
የእምዬን ወደ አብዬ ይብቃ ለዴሞክራሲ ያልበቃው ኢህአዴግ ነው!
Sibehat Nega |
በቅርቡ የመወያያ አጀንዳ ሆነው ከሰነበቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ የሚጠቀሰው አንድ የህወሓት አንጋፋ ባለስልጣን “የኢትዮጵያ ህዝብ ለዴሞክራሲ ብቁ አይደለም” በማለት ህዝቡን መዝለፋቸውን የሚገልፀው መረጃ ነበር፡፡ እኚህ አንጋፋ ባለስልጣን በተለያዩ ጊዜያት የህወሓት/ኢህአዴግን እኩይ አላማና ፍላጎት ያለአንዳች እፍረት በይፋ በመናገር አነጋጋሪ መሆን ጀምረዋል፡፡
ሰውየው ሆነብለውም ይሁን አምልጧቸው የሚናገሯቸው ሀሳቦች፣ የአምባገነናዊ ስርዓቱን እኩይ አስተሳሰብ ለአደባባይ እንዲውል የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን አይነት አስተሳሰብ ባላቸው አካላት እየተገዛ እንደሆነ እንዲገነዘብ የሚረዳ ነው፡፡
አምባሳደር ተወልደ ዓጋመ ከፓርቲው ለቀቁ (እየሩሳሌም አርአያ)
የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ (በቅጽል ስማቸው ተወልደ ዓጋመ) በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው እንደለቀቁ ምንጮች አረጋገጡ። ባለፈው በተካሔደው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበው ከማ/ኰሚቴ አባልነት እራሳቸውን እንዳገለሉ አስታውቀዋል።
በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ከ 1993ዓ.ም በሑዋላ ተዛውረው በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ያለሙያቸው ተመድበው ቆይተዋል። በተጨማሪ ባለቤታቸው ሮማን ገ/ስላሴ በፓርቲው ሊ/መንበር « አይኖዋን ማየት አልፈልግም» ተብለው ከፓርቲው ርቀው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰዋል።
በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ከ 1993ዓ.ም በሑዋላ ተዛውረው በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ያለሙያቸው ተመድበው ቆይተዋል። በተጨማሪ ባለቤታቸው ሮማን ገ/ስላሴ በፓርቲው ሊ/መንበር « አይኖዋን ማየት አልፈልግም» ተብለው ከፓርቲው ርቀው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰዋል።
Tuesday, November 13, 2012
የሀይንሪኽ በል ድርጅት ከኢትዮጵያ የመውጣት ውሳኔ
መንግሥታዊ ያልሆነው የጀርመናውያኑ የሀይንሪኽ በል ድርጅት ኢትዮጵያን ለቆ እንደሚወጣ እና በአዲስ አበባ የሚገኘውን ጽሕፈት ቤቱንም እስከ ፊታችን ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚዘጋ አስታወቀ።
በደራ ወረዳ አንዲት ሴት የባሉዋን ብልት በአደባባይ በገመድ እንድትጎትትና እንድትስም ተደረገ
Torturing |
ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ
የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን
ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ
አድርገዋል።
የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊውና ፖሊሶች በመቀጠልም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር
ካስደረጉ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም
ብልቱን እንድትስም አስደርገዋል። በእርግጫ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጅ አስወርዳለች። በድርጊቱ አልሳቃችሁም
የተባሉትም ተደብድበዋል።
ኢትዮጵያ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አባል ሆና መመረጡዋ ተተቸ
United Nations human right |
ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰሞኑን ባካሄደው ምርጫ አስከፊ ሰብአዊ
መብቶችን ጥሰት የሚፈጽሙ በርካታ አገሮችን መምረጡ በሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ትችት ቀርቦበታል።
የሰብአዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅቶች እንዳሉት ሰኞ እለት ከተመረጡት 18 አገሮች መካከል መስፈርቱን የሚያሟሉ አገሮች ሶስት ብቻ ናቸው። የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ለአፍሪካ 5 መቀመጫዎችን የሰጠ ሲሆን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣
ጋቦን፣ ኬንያና ሴራሊዮን ለቦታው ተመርጠዋል። ጃፓን ፣ ካዛኪስታን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ፓኪስታንና ዩናይትድ አርብ
ኤምሬትስ ደግሞ የኤስያ ፓስፊክ አገሮችን መቀመጫዎች ወስደዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)