Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, November 28, 2012

የዶላር ዋጋ እየወደቀ ነው ተባለ


ኢሳት ዜና:-የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ በ17 በመቶ ጨምሮ በ16.35 ብር እንዲመነዘር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መወሰኑ ይፋ ከተደረገበት መስከረም 2003 ዓ.ም. ወዲህ ባሉት ሁለት ዓመታት፣ የብር ምንዛሪ አቅም እየቀነሰ ከ10 በመቶ በላይ ወርዷል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነው።

በኅዳር 2004 ዓ.ም. የየዕለቱ የውጭ ምንዛሪ ዋጋን በሚያመለክተው መረጃ መሠረት የአንድ ዶላር አማካይ የምንዛሪ ዋጋ 17 ብር  ከ20 ሳንቲም የነበረ ሲሆን፣ በኅዳር 2005 ዓ.ም. ያለው መረጃ የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ ወደ 18. ብር ከ20 ሳንቲም ከፍ ብሎአል፡፡


ከኅዳር 2003 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. የነበረው የምንዛሪ ዋጋ ከ5.3 በመቶ በላይ ሲጨምር፣ በ2005 በጀት ዓመት የኅዳር ወር የምንዛሪ ዋጋ በአማካይ ወደ 18. ብር ከ20 ሳንቲም  ማደጉን ተከትሎ ከሌሎች መገበያያ ገንዘቦች አኳያ የብር የመግዛት አቅምን በአንድ ዓመት ከ5.56 በመቶ በላይ እንዲወርድ አድርጎታል፡፡ በአጠቃላይ ከኅዳር 2003 ዓ.ም. ወዲህ የብር የመግዛት አቅም በ30 ከመቶ እንዲወድቅ ምክንያት ሆኗል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የታየው የምንዛሪ ለውጥ ግን በመስከረም 2003 ዓ.ም. በብሔራዊ ባንክ በአንዴ ከተደረገው ጭማሪ በተቃራኒው ቀስ በቀስ በየዕለቱ ይካሄድ በነበረው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ተመርኩዞ እየጨመረ የመጣ ብሎአል ጋዜጣው፡፡

የዋጋ ግሽበት በሚፈለገው ደረጃ ሊቀንስ ካልተቻለባቸው ምክንያቶች አንደኛው የብር አቅም መዳከምና የውጭ ምንዛሪ ጉልበት በየጊዜው እያደገ መምጣቱ ነው በማለት ባለሙያዎችን በመጥቀስ ጋዜጣው ዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment