አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መስራችና የድርጅቱ የሞራልና የፍልስፍና
አባት ተደርገው የሚወሰዱት አቶ ስብሐት ነጋ በ1993 ዓ.ም ክፍፍል ወቅት ከድርጅቱ የተሰናበቱ አባላትን አንድ
በአንድ በማነጋገር ድርጅቱ በአዲስ መልክ ህልውናውን እንዲያጠናክር በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ የአውራምባ ታይምስ
አስተማማኝ ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል፡፡
‹‹መለስ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሀወሓትንም ጭምር ገድሎ ነው የሞተው››Nየሚሉት ስብሐት ነጋ ‹‹በትጥቅ ትግሉ
ወቅት የጎላ ድርሻ የነበራቸውና ችግርና መከራን ተጋፍጠው ህወሓት ውስጥ በጽናት የዘለቁ አመራሮች ወደ ጎን
ተገፍተው፤ ዛሬ ድርጅቱ የእነ አዜብ መፈንጫ ሆኗል››Nማለታቸውን ጠቅሰው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡