(ደጀ
ሰላም፤ የካቲት 18/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 25/2013/ PDF)፦ ቅዳሜ የካቲት 16/2005 ዓ.ም ቀርበው በአብዛኛው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ይሁንታ አግኝተዋል የተባሉት
አምስት ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው ሐሙስ ለሚካሄደው የፓትርያርክ ምርጫ ያለፉ መሆናቸውን አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።
ከፍተኛ ታቃውሞና የከረረ ተግሳጽ የደረሰባቸውን አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌምን
ጨምሮ ሌሎቹ አራት አባቶች የተካተቱበት የአስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማ ለቅ/ሲኖዶስ ቢቀርብም ተጨማሪም ተቀናሽም ሳይደረግበት መጽደቁ
ዛሬ ይፋ ሆኗል። በዚህም መሠረት ሐሙስ በሚደረገው ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር የሚያገኘው ተወዳዳሪ ስድስተኛ ፓትርያርክ ተብሎ ይሾማል
ማለት ነው።