Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, July 14, 2012

ሰበር ዜና በአዋሊያ ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢሳት ሰበር ዜና 
ዓርብ ሐምሌ 6 ቀን 2004 ዓ.ም፡- በኢህአዴግ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ የተፈጠረው መቃቃር ወደ አጠቃላይ አካላዊ ግጭት አመራ፡፡ ዛሬ ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በአወሊያ መስኪድ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለእሁድ አጠቃላይ የአንድነትና የድምፃችን ይሰማ ተቃውሞ ዝግጅት በማድረግ ላይ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ቅጥር ጊቢውን ጥሶ በመግባት ሙስሊም ማህበረሰቡን በቆመጥ በአስለቃሽ ጭስ በመደብደብና መሳሪያ ወደ ላይ እና ወደ ሰው በመተኮስ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

እነ አቶ አንዱአለም አራጌ ተፈረደባቸው

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በእነ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ በተከሰሱት ላይ ከ8 አመት እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ፍርድ አስተላለፈ በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ከተላለፈባቸው መካከል በእስር ላይ የሚገኙና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ይገኙበታል።

አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሲፈረድባቸው፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ እስክንድር ነጋ፣ ውቤ ሮቤ እና ኦባንግ ሜቶ እያንዳንዳቸው በ18 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

በሲዳማ ዞን ያለው ውጥረት እየተባባሰ ነው

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በቅርቡ ከሲዳማ ዞን እጣ ፈንታ እንዲሁም አጠቃላይ የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተነሳው ውጥረት መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ ባለፈው ሳምንት የግንቦት7 አባላት ናቸው ተብለው የተረጠረጠሩ በርካታ ወጣቶች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ዘጋቢያችን የገለጠ ሲሆን፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑት አቶ በረከትንና አቶ አባይ ጸሀየን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ፓርቲዎች በችግሩ ዙሪያ በአዋሳ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።

የተባበሩት የሲዳማ ፓርቲዎች ለነጻነትና ለፍትህ ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደንቦባ ናቲ ለኢሳት እንደተናገሩት የሲዳማ ሽማግሌዎችና የአካባቢው ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ሲሆን ተቃውሞው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል:: አቶ ደንቦባ እንዳሉት የሲዳማ የኢህአዴግ አባላት በብዛት አባልነታቸውን እየሰረዙ ነው::

Source:  ኢሳት ዜና

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤“ሰላማዊ ትግሉም እየተበላሸ እና ወደ አላስፈላጊ ጫፍ እየተገፋ ነው” አለ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአመራር አባሉ በጥይት ተደብድቦ የተገደለበት  የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤“ሰላማዊ ትግሉም እየተበላሸ እና ወደ አላስፈላጊ ጫፍ እየተገፋ ነው” አለ። ”የዳኝነት ሥርዓቱም  ቅጥ ባጣ መልኩ በኢህአዴግ  አመራር የሚሽከረከር አሻንጉሊት ሆኗል” ሲልም  መኢአድ የፍትህ ስርዓቱን አጥብቆ ኮንኗል።

ድርጅቱ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤  በርካታ አመራሮቹና አባላቱ   ያለምንም ጥፋታቸው በኢህአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች  ሰብዓዊ ክብራቸው እየተገፈፈ እና ዲሞክራሲያዊ መብታቸው እየተጨፈለቀ እንደሚገኝ  አመልክቷል። በተለይ በ አማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አመራሮቹ  በግፍ እየተያዙ ወደ ወህኒ እየተወረወሩ መሆናቸውን የጠቀሰው መኢአድ፤ በሽብርተኝነት ህግ ሽፋን እየተፈፀመ ባለው ግፍ  ሰላማዊ ትግሉ እየተበላሸ እና ወደ ጠርዝ እየተገፋ እንደሆነ ገልጿል ።

Wednesday, July 11, 2012

ለአስቸኳይ ልዩ ስብሰባ የተጠራው ፓርላማ የቴሌን ህግ አጸደቀ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
99 ነጥብ ስድስት በመቶ በአንድ ድርጅት አባላት የተሞላው ፓርላማ ለአስቸኳይ ልዩ ጉባኤ የተጠራው አዲሱንና አወዛጋቢውን የቴሌ ህግ ለማጽደቅ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። ዘጋቢያችን እንዳለው በጥሪው ላይ አስቸኳይና ልዩ የተባለው ፓርላማው ካለፈው ሰኔ ሰላሳ ቀን ጀምሮ እንደተዘጋ በመቆጠሩ ነው።

የፍትህ ዋና አዘጋጅ ደህንነት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በሳምንታዊው ፍትህ የአማርኛ ጋዜጣና በዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የግል እንቅስቃሴ ላይ የደህንነት ኃይሎች የሁለት ቀናት የሃያ አራት ሰዓታት ግልጽ ክትትል ማድረጋቸውን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡ በጋዜጣው የኢሜል አድራሻም ከአልሸባብ ለዋና አዘጋጁ የተላከ የሚያስመስል ቁጥር 2 የፈጠራ ደብዳቤ ከሰሞኑ ተልኳል፡፡

ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን እና እሁድ ሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጋዜጠኛ ተመስጌን ራሳቸውን በግልጽ ባቀረቡ የደህንነት ሰዎች ሙሉ ክትትል ሥር የዋለ ሲሆን ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ዙሪያ፣ በመመገቢያ ሥፍራው፣ በቢሮው አቅራቢያ፣ በቤተሰቦቹ መኖሪያ ቤት ዙሪያ እና በሚንቀሳቀስበት ሁሉ እየተፈራረቁ  በመከታተል አእምሮው እረፍት እንዲያጣና እንዲጨናነቅ ጫና ለመፍጠር ሞከራውል በማለት ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

በጭቆናና በክፋት ያደገ አእምሮ አደገኛ እንደሆነ በባለሞያ ተገለፀ

እንክብካቤ እየተደረገለት ያላደገ በጭቆናና በክፋት ያደገ በተዛባ አያያዝ ያደገ አእምሮ ለራሱ ለህብረተሰቡና ለአገርም ጐጂ እንደሚሆን ተገለፀ፡፡ ይህን የገለፁት ታዋቂው የህክምና ባለሞያ ዶ/ር መስፍን አርአያ ናቸው፡፡ ዶ/ር መስፍን ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ ሴት ደራሲያት ማህበር ከፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ጋር በመተባበር “ትውልዱን ከሱስ እናድን” በሚል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት ኤጀንሲ ባዘጋጀው ኪነጥበባዊ ምሽት ላይ ነው፡፡

በኢህአዴግ ውስጥ የጐላ ልዩነት እየተፈጠረ ነው


ከስድስት ወራት በላይ የስቆጠረውን ሀገር አቀፍ የሙስሊሞች ተቃውሞና ከዋልድባ ገዳምና የስኳር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በኢህአዴግ ውስጥ የጐላ ልዩነት እየተፈጠረ መምጣቱን ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለገዢው አብዮታዊ ግንባር ኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን እንዳመለከቱት ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣናቱን በሀይማኖት ዙሪያ በተደጋጋሚ በማወያየት ላይ ይገኛል፡፡

ግራ የተጋባው ፓርላማ ነገ ለልዩ ስብሰባ ተጠራ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት የመዝጊያው ጊዜ እስከዛሬ ድረስ ባልተለመደ ሁኔታ የተራዘመው ፓርላማ ፣ ነገ ረቡእ ለልዩ ስብሰባ ተጠርቷል። በነገው ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ይገኙ እንደሆን ለምንጫችን ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ፣ “እስካሁን ድረስ ይገኛሉ የሚል ፍንጭ አለመሰማቱን፣ ይሁን እንጅ ይገኛሉ ብለው እንደማያስቡ” ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጸናት ግንባር በቶሮንቶ የተሳካ ስብሰባ አደረገ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በብርጋዲየር ጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው የአሮሞ ነጸናት ግንባር ባለፈው ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጁላይ 6 ቀን 2012 በቶሮንቶ ካናዳ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አድረገ። 

በዚህ በቶሮንቶ አካባቢ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት የግማሽ ቀን ስብሰባ ላይ፤ የድርጅቱ የበላይ አመራር አካላት፡ ማለትም ብርጋዲየር ጄነራል ሀይሉ ጎንፋ ከአስመራ በስልክ፡ ዶ/ር ኑሮ ደደፎና የድርጅቱ ቃል አቀባይ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ባለሟል አቶ ተማም ባቲ፤ በአካል ተገኝተው፤ ንግግር በማድረግ ከተሰብሳቢው ጋር ተወያይተዋል።

የህዝበ-ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆቴላቸው በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በኮምቦልቻ ከተማ በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ደማቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ተካፍለዉ የነበሩት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሼህ መከተ ሞሄ በፖሊስ ታፍነዉ መታሰራቸዉን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘግቧል።

ሼህ መኸተ ሞሄ የታሰሩት ፕሮግራሙን ጨርሰዉ ወደ ማረፊያ ሆቴላቸዉ ከገቡ ቡሁዋላ በበርካታ ፖሊሶች ታፍነው ነው።

ከሸህ መከተ በተጨማሪ በኮምቦልቻ ፕሮግራም ላይ ከተካፈሉት መካከል፤  ታዎቂዉ “ዳኢ” እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነዉ ኡስታዝ ያሲን ኑሩም በፖሊሶች እየተፈለገ መሆኑን ወኪላችን ያጠናቀረው ዘገባ ያመለክታል።

በአሁኑ ጊዜ  የአካባቢው ፖሊስ ኡስታዝ ያሲን ኑሩን ለማሰር ከተማዋን እያሰሰ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል!!
Source: Ethsat news :የህዝበ-ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆቴላቸው በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ

Monday, July 9, 2012

የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሁንም ሚስጢር እንደሆነ ነው

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የፓርላማ አባላት ግራ ተጋብተዋል፣ የተለያዩ ዝግጅቶች ተሰርዘዋል ፣ አንዳንድ መረጃዎች አቶ መለስ የወራት እድሜ እንዳላቸው ይጠቁማሉ ዝርዝሩ ኢሳት የፓርላማው መዝጊያ በአንድ ሳምንት እንደሚራዘም፣ ምክንያቱ ደግሞ የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ችግር እንደሆነ ከዘገበ በሁዋላ ፣ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ የመላው ኢትዮጵያውያን የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። 

በኢህአዴግ ዙሪያ የተሰባሰቡ አባላት ሳይቀሩ ግራ ተጋብተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ በተገኙበት በፈጠራና ምርምር የላቀ ውጤት ላስገኙ ስድስት ኢትዮጵያዊያን በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሰሞኑን ሊሰጥ የታሰበው ሸልማት ለሁለተኛ ጊዜ  ተላልፏል፡፡ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሰኔ 21 ቀን 2004  ዓ.ም ሊሰጥ ታሰቦ የነበረው ሸልማት በሥራ መደራረብ ምክንያት ለሰኔ 28 ቀን 2004 ዓ.ም መተላለፉን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጭምር ይፋ ከተደረገ በኃላ እንደገና  ምክንያት ባልተገለጠበት ሁኔታ ዝግጅቱ እንዲቀር ተደርጓል፡፡

በደርግ ዘመነ መንግስት የነበረውን ጥበባዊ አሻራ ለማስቃኘት ታሰቦ የተከፈተው የሥዕል ኤግዚቢሸን በኢቲቪ እንዳይተላለፍ ታገደ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የኤግዚቢሸኑ ዜና በኢቲቪ ከተዘገበ በኃላ እንዳይተላለፍ የታገደው ያለፈውን ሥርዓት የሚያንቆለጻጽስ ነው በሚል ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእስክንድር በጎሲያን ሥነ ጥበባት ኮሌጅ ሥር የሚገኘው ትምህርት ቤት ከ1967 እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ተማሪዎቹ ከሠሯቸው ልዩ ልዩ ሥዕሎች መካከል የተመረጣቸውን ሥዕሎች በሰኔ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለእይታ አብቅቷል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ከተከሰሱት ሰዎች በአራቱ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በእነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ አሰናብቷቸው የነበሩ አራት ተከሳሾች ላይ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከ10 እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ ዛሬ አሳለፈ።

የመንግስት አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ በነኚሁ አራት ግለሰቦች ላይ፣ ማለትም በ21ኛው ተከሳሽ ኮሎኔል አለበል አማረ፣ በ12ኛ ተከሳሽ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፤ በ19ኛው ተከሳሽ አቶ ኤልያስ ሞላ እና በ20ኛው ተከሳሽ አቶ ደሳለኝ አራጌ  ላይ ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሾቹ የተወነጀሉት ከግንቦት 7 ፓርቲ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ተግባርን ለመፈጸም በማቀዳቸው እንደሆነ ይጠቅሳል።

‹‹ይቅርታ›› የኢህአዴግ ቃጭል? ወይስ…

1998
አዲስ አበባ በለውጥ ፍላጐት ከአፍ እስከ ገደቧ ታጥናለች። እዚህም እዚያም የፖለቲካ ወግ ጠሰቃል። በቡድን ሆነው፣ በስሜት ተውጠው በፖለቲካ ጉዳይ የሚከራከሩ በርክትዋል፡፡ ለዓመታት የፖለቲካ ጉዳይ ‹‹ፆም›› የሆነባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሳይቀሩ ጎራ ለይተው በሚከራከሩ ራተኞቻቸው ተፈስገዋል፡፡ ‹‹ቅንጅቱ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ድምፅ አግኝቷል›› ይላል አንዱ። ‹‹ቢሆንም ኢህአዴግ ይገግማል!›› ሲል ይመልሳል፤ ኢህአዴግ በምርጫ ስልጣን አይለቅም የሚል አቋም ያለው ተከራካሪ፡፡

…የጋዜጦች እትሞች ከምርጫው በፊት ከነበረው ቅጂ ከሶስት እስከ አምስት እጥፍ ድረስ ጨምረዋል። ማንበብ የሚችለውም፣ ማንበብ የማይቻለውም ቋሚ የጋዜጣ ሸማች ሆኖአል-እድሜ ለምርጫው። በኢትዮጵያ ‹‹መንግሥት…›› ሲባል የተቃወመውን በሙሉ የሚገድል እንደሆነ ከልምድ የተገነዘቡ ወላጆች ለልጆቻቸው በመስጋታቸው ጭንቀታቸው ጨምሯል፡ ፡ እነዚህ ኩነቶች የድህረ ምርጫ 1998 ዓ.ም. ዋነኛ መገለጫዎች ነበሩ፡፡

ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!

By ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! 

ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም!