እስካሁን ድረስ ያሳየነው
ችሎታ የማጥፋት
ወይም የማክሸፍ
እንጂ አዲስ
ነገርን ወይም አዲስ
ሥርዓትን የመፍጠር አይደለም፤
በአለፉት ሃምሳ ዓመታት
ውስጥ ቢያንስ
ሦስት የአስተዳደር
ሀሳቦች መቅረባቸውን አውቃለሁ፤
አንዱ በአቶ
ሀዲስ አለማየሁ፤
ሁለተኛው በኤንጂኒር-የሕግ
ባለሙያ ደመቀ መታፈሪያ፣
ሦስተኛው የኔ ናቸው።
አእምሮአቸውና ልባቸው በማርክሳዊ-ሌኒናዊ ጦር
ተቀስፎ የተያዘባቸው ወጣቶች
ሌላ ሀሳብን
የማይሰሙበት ጊዜ ነበር፤
ማርክሳዊ-ሌኒናዊ ጥራዝ-ነጠቅነት ብቻ
የሁሉም ዓይነት የእውቀት
ምንጭ ነው ብለው
በጭፍን የሚያምኑ ወጣቶች
በተለይም ከኢትዮጵያዊ የፈለቀ
ሀሳብን ለማጥላላት ጉልበታቸውንና
ጊዜያቸውን አይቆጥቡም ነበር፤
የሌኒን የጡት ልጆች
እርስበርሳቸው ተፋጁና ያሸነፉት
ዛሬም ከፋፍለው ይገዙናል፤
የት እንደሚያደርሱን ገና
አላወቅንም።