Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, August 16, 2012

የአቡነ ጳውሎስ ዜና እረፍት የተደበላለቀ ስሜት ፈጥረ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጻውሎስ ፓትሪያሪክ ርዕሰ ሊቀጻጻስት ዘኢትዮጵያ ሊቀጻጻሳት ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣የዓለም አብያተክርስቲያናት ፕሬዚዳንት በ76 ዓመታቸው አርፈዋል።

20ኛ ዓመት የሲመት በዓላቸውን ሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል ያከበሩት አቡነ ጻውሎስ በባልቻ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት ለሊት አርፈዋል።

ኢትዮጵያውያን በተለይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በጳጳሱ ዜና እረፍት የተደበላለቀ ስሜት ተስምቷቸዋል። የአዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች ዘጋቢዎቻችን እንዳሉት ህዝቡ በዜና እረፍታቸው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲነጋገር ውሎአል።

የአዲስ አበባው ወኪላችን ከቤተክህነት እና ከጳጳሱ ጽህፈት ቤት ካሉ የዜና ምንጮች ባገኘው መረጃ ጳጳሱ ሰሞኑን በጸና ታመዋል ተብሎ የተወራው ሀሰት ሲሆን፣ እንደዘወትራቸው ያሉባቸው የጤና መቃወሶችን ተቋቁመው መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ የነበሩና የፍስለታ ጾምን በቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ጸሎት በመምራትና ቡራኬ በመስጠት ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን እስከ ማክሰኞ ድረስ ጸሎት በመምራት ሲቀድሱና ሲያስቀድሱ ነበር።

ይሁን እንጅ ማክሰኞ እለት ጸሎት ሲመሩ እየተዳከሙና ድምጻቸው የቀነሰ ሲሆን ወደ ህክምና ተቋማት ተወስደው እርዳታ ቢደረግላቸውም ትላንት ሌሊት አርፈዋል::

የአቡኑን እረፍት ተከትሎ የፌደራል ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እና አቶ አባይ ጸሀየ በዚህ ጉዳይ ላይ ከቤተክርስቲያኑዋ የበላይ ሀላፊዎች ጋር እየሰሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

አቡነ ጳውሎስ በቅርቡ 20 አመት የስልጣን ዘመናቸውን ድል ባለ ግብዣ በሸራተን ሲያከብሩ፣ በአቡኑ ጽህፈት ቤት ዋና በር ላይ ደግሞ ስኬታማ 20 አመታት የሚል ቢል ቦርድ ተሰቅሎአል። 

ለመሆኑ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማናቸው፡፡ከሞላ ጎደል ታሪካቸው  እንሆ! (ESAT Special analysis - Who was Abune Paulos? | August 17, 2012)

          

No comments:

Post a Comment