Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, August 15, 2012

አቶ ስብሐት ነጋ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ መመለስ መናገራቸው ስህተት እንደነበረ ለኢሳት ገለጡ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ ከሶስት ሳምንት በፊት ያስታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ አባባላቸው ስህተት መሆኑን ለኢሳት ገለጡ።

አቶ በረከት ስምኦን ከአዲሱ አመት በፊት አቶ መለስ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ ይህንን የማረጋገጥም ሆነ የማስተባበል መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል።
አንጋፋው የህወሀት ታጋይ አቶ ስብሀት ነጋ ለስርአቱ ቅርበት ያላቸው ጋዜጦች አቶ መለስ ወደ ሀገር ቤት ስለመመለሰሳቸ በጻፉት ጥያቄ አንስተዋል። ከሰኔ 11/2004ዓም ጀምሮ ላለፈት 57 ቀናት አቶ መለስ ዜናዊን አለማግኘታቸውን አቶ ስብሀት ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ አመልክተዋል።

የሀገሪቱ ጦር ሀይል አዛዥነቱን ስልጣን የያዘው ማነው ፣ አቶ መለስ በህይወት ካሉ ድምጻቸውን ለምን አያሰሙም? የሚሉት ጥያቄዎች ቀርበውላቸው መልስ ሰጥተዋል።

No comments:

Post a Comment