ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
“ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ዞር ሲሉ፤ ግብፆች ፦” ኢትዮጵያውያን ከጥቅማቸው በተቃራኒ ይቆማሉ” ብለው ማሰባቸው ስህተት ነው” ሲሉ አንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናገሩ፡፡
በኢፌድሪ
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ያሉት፤ አንድ የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር
ከፍተኛ ባለስልጣን የዛሬ ሳምንት ፦” ከመለስ ዜናዊ በሁዋላ የሚኖረው አዲሱ የኢትኦጵያ አመራር -ከአዲሶቹ ከግብጽ
መሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በዓባይ ወንዝ ምክንያት በአገሮቹ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ያረግቡታል የሚል
እምነት አለኝ” ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ዳይሬክተሬ አቶ ጌታቸው ለግብጹ የመስኖ ባለስልጣን በሰጡት በዚህ
ምላሻቸው ላይ፤ “በሁለቱ አገሮች ግንኙነት ዙሪያ በኢትዮጵያ በጐ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ የመሻሻል አዝማሚያ
ቢኖርም፤ በግብጽ በኩል ግን ደካማ ኢትዮጵያን የማየት ፍላጐት ግን ተቀርፏል ማለት አይቻልም” ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
የግብፁ ባለስልጣን፦ “ቢኪያ ሞሳር” ለተባለ ድረገፅ ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ፦ “አዲስ ከሚመጣው የኢትዮጵያ አመራር ጋር ባላንጣነትን በማስወገድ በመግባባት መስራት ይቻላል” ብለዋል ።
ከሥልጣን
ዋዜማቸው የኢትዮጵያን ግዛቶች ለጎረቤት አገራት እየቆረሱ በመስጠት የሚታወቁት እና በዚህም ምክንያት ከአብዛኛው
ኢትዮጵያዊ ከፍ ያለ ተቃውሞ የሚሰነዘርባቸው አቶ መለስ ዜናዊ ፤ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ በዓባይ ወንዝ ላይ
ግድብ ለማሰራት በመንቀሳቀሳቸው ከአዲሱ የግብጽ አስተዳደር ጋር ውስጥ ውስጡን ሲቋሰሉ መክረማቸውን መረጃዎች
ያሳያሉ።
ነገሩ በዚህ ሁኔታ እያለ ካለፉት ሰባት ሳምንታት ወዲህ አቶ መለስ በጤና ምክንያት ተሰወሩ።
መሰወራቸውን ተከትሎ ግብፃውያን፦” ከአዲሱ የ የኢትዮጵያ አመራር ጋር በመነጋገር ተግባብተው ለመስራት ያላቸውን
ፍላጎት ገለጹ።
“ በ እርግጥ እኛ ግብፃውያንም ማቻቻል ላይ በጣም ጥሩ የምንባል አይደለንም፤ አሁን ግን
አገሮቹ በጋራ ተግባብተው የሚሠሩበትን መንገድ በማመቻቸት በኩል ትልቅ ሥራ ልንሠራ ይገባል” ነው ያሉት የመስኖ
ባለስልጣኑ ፡፡
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት፦ “አቶ መለስ ህክምና ጨርሰው እረፍት ላይ ናቸው” በሚሉበት ጊዜ
የግብጹ ባለስልጣን ፦”ከኢትዮጵያ አዲስ አመራር ጋር….” ማለታቸው፤”ግብፆች ስለ አቶ መለስ ምን ቢያውቁ ነው
እንዲህ ያሉት?” የሚል ጣያቄ አስነስቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው
ረዳ ግን፦ “የጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊን ሁኔታ አስመልክቶ ግብፆች የሚያውቁት ሌላው አለም የሚያውቀውን ነው፤ ሌላ
ምንም ሚያውቁት ነገር የለም” ባይ ናቸው።
No comments:
Post a Comment