በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩን ጨምሮ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን
በዚህ ስብሰባቸው ዋነኛ አጀንዳ የሆነው በእነ አቦይ ስበሃት ነጋ ለረጅም ጊዜ ሲመራ የነበረውን የህወሃት ድርጅትን
አፍርሶ በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያደርጉት ትልቅ ትግል መሆኑን ከውስጣዊ ምንጮች የተገኘው ሪፖርት ያሳያል ።
ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ በባህርዳር ተጀምሮ ሃሙስ እለት የተጠናቀቀው በአቶ በረከት ስምኦን ሰብሳቢነት
ቢሆንም በዚህ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ዋና ዋና ባለስልጣናት ተብለው የተገለጹት አቶ አዲሱ ለገሰ ፣የአማራው ክልል
ፕረዚዳንት ኤፍሬም አድሃኖም እና ሌሎችም የሚገኙበት መሆኑ ተገልጾአል ። በተለይም በአሁን ሰአት ጠቅላይ ሚንስትሩ
ሞተዋል እየተባለ በሚወራበት ሰአት እንዲህ አይነት ክፍፍል በሃገሪቱ ላይ የሚያመጣው ቀውስ የወደፊቱን የህወሃትን
እጣ ፈንታ ሊያዛባው ይችላል ተብሎ ተገምቶአል ።
በተለይም በነ አቦይ ስበሃት በኩል የሚመራው የዚህ ተገንጣይ ቡድን ሃሳብ በዝምተኝነት እና በቸልተኝነት ያየ
ይመስላል በእርግጥም ዝም ብሎ የተቀመጠ ሳይሆን ስራቸውን ሰርተው ይጨርሱ ብሎ በውጭ ቆሞ ተመልካች ወይንም ታዛቢ
ያስመስለዋል ቢሆንም ግን ሁሉንም እናውቃለን የሚል አንድምታ አላቸው የጅማሬአቸውን ፍጻሜ ማየት እንፈልጋለን
ብለዋል።
በተለይም ለማለዳ ታይምስ ከባህርዳር የብአዴን ልዩ ክንፍ ተብሎ ከሚጠራው አካል በደረሰው መረጃ መሰረት
ህወሃትን ለመገንጠል የሚታሰበው ፕሮግራም ከተሳካ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ ተክተው ይሰራሉ ተብለው የሚጠበቁት
አቶ በረከት ስምኦን ሊሆኑ እንደሚችል ከውስጣቸው ያፈተለከው ወሬ ይገልጻል ፣ይህንን ወሬም ተከትሎ አቶ በረከት
ስምኦን በትውልደ ኤርትራዊ የሆኑ ወዳጆቻቸውን በማሰባሰብ ለስልጣኑ የሚያበቃቸውን ሃይል እያደራጁ መሆኑን
ተነግሮአል ።
በሌላም በኩል የአማራው ክልልን ሃይል አጠናክረው ከተጓዙ በሁዋላ በኦሮሚያ ክልል መንግስት ስር
ጣልቃም በመግባት ክልሎቹን በራሳቸው እጅ ስር ለመጣል የሚሞክሩበት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችሉበትን ዘዴ በማርቀቅ ላይ
ናቸው ።ይኸው ውስጥ ለውስጥ በመፍረክረክ ላይ ያለው የህወሃት መንግስት እና እንዲሁም የኢህ አዴግ ፓርቲ ክፉኛ
ውጥረታቸው ከጠቅላይ ሚንስቱሩ መታመም በሁዋላ እየባሰ በመምጣቱ በሃገሪቱ ላይ የደም መፋሰስ ሊኖር እንደሚችል
አንዳን ሰዎች ሲጠቁሙ ይህንንም ጉዳይ አያይዘው የተከፋፈሉት የህወሃት አባሎች እርስ በራሳቸው በአይነ ቁራኛ
በመተያየት ላይ ናቸው ፍራቻቸውም ነግሶአል ብለዋል ።
የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል በትላንትናው እለት ከጋዜጠኛ አበበ ገላው ጋር ባደረገው የአጭር ጊዜ ቃለ ምልልስ
ስለ ጠቅላይ ሚንስትሩ የመኖር እና የአለመኖርን አስመልክቶ ላቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ እኛ ከአይ ሲ ጂ ውስጣዊ
ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሰረት ጠ/ሚንስትሩ በእርግጠኝነት መሞታቸውን በማረጋገጥ ገልጸናል እኛም ያገኘነው መረጃ
ሆነ የሽሽግግር መንግስት ካውንስል ተብሎ የተቋቋመው ድርጅት የሞቱበት ቀንን የገለጽነው ተመሳሳይ ቀን በ 14
እንደሆነ ለመረዳት ችለናል በእርግጥ የአቶ ፍሰሃ እሸቱን የመረጃ ምንጭ ምን እንደሆነ ብንጠይቃቸውም ሊገልጹልን
አልቻሉም ብሎ የመለሰ ሲሆን ቢሆንም ግን መረጃውን በተለያዩ አካላት እና ከተለያዩ ቦታ እንዳገኙት የገለጸው አበበ
ገላው የመረጃውን እርግጠኛነት የበለጠ ያጠናክረዋል ይላል ፣በተመሳሳይ ጥያቄ ከአይ ሲጂ ላገኙት መረጃ ለሌሎች
መገናኛ ብዙሃን ይረዳ ዘንድ እንዲሁም እውነታውን ለማወቅ ያስችል ዘንድ መረጃችሁን ልታሳዩን ትችላላችሁ ወይ ብሎ
ከማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ለአበበ ገላው ለጠየቀው ጥያቄ መልሱን ሲመልስ ይህ የአንድን ግለሰብ ወይን ድርጅት ህልውና
የያዘ ሚስጥራዊ ሰነድ እስከሆነ ጊዜ ድረስ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ለማንኛውም ሰው ለመስጠት አንችልም ብሎ መግለጹንም
ማለዳ ታይምስ ይጠቁማል።
በተያያዘ የጥያቄና መልስ ወቅት የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ እንደሚያመለክተው እና ጥያቄውን
የህዝብ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ሁሉም ነገር በማንኛውም ሚዲያ የተገኘው መረጃ ግልጽመሆን እንደሚገባው ያምናል
፣ይህንንም በማሰብ የመረጃን እኩልነት ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን ድርሻም ተወጥቶአል እየተወጣም ነው
፣ለዚህም የዜና ዘገባ ጥንቅር ላይ ከአበበ ገላው ጋር ያደረገውን ዋነኛ ጥያቄ ሲያነሳ እንዴት ከግለሰብ ያገናችሁትን
አንድ መረጃ በአንድ ትልቅ እና አንጋፋ ድርጅት ስም ዜናውን ትሰሩታላችሁ::
ይህ በድርጅቱስ አያስከሣችሁም ወይ
በሌላም በኩል የጠቅላይ ሚንስትሩን መሞት ዘግባችሁት ሳለ በህይወት ቢኖሩ እና መኖራቸውን ቢገልጹ ዬናነተን የሚዲያ
ክሬዲተበሊቲ ወይንም ታማኝነትን አያጎድለውም ወይ ይህ የጋዜጠኝነትም ስነ ምግባር አይደለም ብሎ ላቀረበለት ጥያቄ
አቶ አበበ ገላው ሲመልስ አንድ አምባሳደር መረጃ ቢሰጥህ ከአምባሳደሮች ባገኘነው መረጃ መሰረት ብለህ ታቀርባለህ
ወይንም አንድ ከዋይት ሃውስ ያገኘኸው መረጃ ቢኖርህ ከዋይት ሃዋስ ውስጥ ያገኘነው መረጃ ብለህ ትጠቅሳለህ እንጂ
የሰውየውን ማንነት የመግለጽ ግዴታ የለብህም የሰውየው ድህንነት የሁላችንንም ስጋት ሊሆን ይገባል::
አይ ሲጂ ለኢሳት
ብሎ ሳይሆን ሪፖርቱን የሰራው ለራሱ የመረጃ ክምችት ነው ሲል አብራርቶአል። በሌላ በኩልም የመገናኛ ብዙሃን
አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ደግሞ አቶ መለስ ዜናዊን እስከ መስከረም ድረስ እንጠብቃቸው በደህንነት
ይመለሳሉ አሁን በማገገም ላይ ናቸው ብለዋል፤ ህብረተሰቡም ትኩረቱ ከመለስ ዜናዊ የደህንነት ጉዳይ ወሬ ለመራቅ
የተገደደ ይመስላል በአሁን ሰአትም በይበልጥ ወደ ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ማድላቱን መርጦአል ።
ይህ በንዲህ እንዳለ በጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ህመም ጉዳይ ላይ ለረጅም ዘመን አልታመሙም ብለው መደበቃቸውን
እና ለሚያስተዳድሩት ህዝብ ለመግለጽ አለመፈለጋቸውን በይፋ በአቶ በረከት ስምኦን በኩል ተገልጦአል ። በወቅቱ አቶ
በረከት ስምኦን ሲናገሩ “የኢሃዴግን ባህል አታውቁትም “ በሚል አጭር አረፍተ ነገር ኢሃዴግ ወሸቶችን አምርቶ
ሊነግራችሁ ይችላል እንጂ እውነትን አንነግራችሁም የሚል ሃሳብ ያዘለ ወሬ እራሳቸው በሚያስተዳድሩት መገናኛ
ብዙሃናቸው ለቀዋል።
ሆኖም ግን የማለዳ ታይምስ መረጃ በወቅቱ ከህወሃት አባሎች ጋር ባደረገው ንግግር የጠቅላይ
ሚንስትሩን መታመም “ጭምጭምታ ከህወሃት መንደር ጠቅላይ ሚንስትሩ በጠና ታመዋል “በሚል ርእስ ለመጀመሪያ ጊዜ
መታመማቸውን ለህዝብ ይፋ አድርጎታል።
source: maleda times
source: maleda times
No comments:
Post a Comment