Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, August 18, 2012

ልዑል ሙሉጌታ አስራተ ካሳ ተባረሩ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ከውጭ ጉዳይ ሰራተኞች በደረሰው መረጃ ልኡሉ በትናንትናው እለት በ2 የደህንነት ሰዎች ታጅበው ምርር ብለው እያለቀሱ ከለንደን ኢምባሴ ወጥተዋል።

የኢህአዴግ ካድሬ በመሆናቸው ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የአማካሪነት ቦታ አግኝተው የነበሩት አስራቴ ካሳ ፣ ከስራ የተባረሩት ያለ ኢምባሲው ፈቃድ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ዝግጅት ጳጳሱን በተመለከተ ቃለምልልስ ሰጥተዋል ተብሎ ነው።

 እርሳቸው ግን ቃለምልልሱን የሰጠሁት በአቡነ ጳውሎስ ጓደኝነት እንጅ በኢምባሲ ሰራተኛነት አይደለም በማለት ለመከራከር ሞክረዋል።

ከትናንት በስቲያ ህይወታቸው ያለፈው ብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ በመቀጥል እንደ ታማኝ ጓደኛ የሚያዩዋቸው አስራተ ካሳን ነበር።

No comments:

Post a Comment