የኢሳት ዜና የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተሰቦች ለመስከረም 10 ታቅዶ የነበረ ሰርግ እንዲሰረዝ ማድረጋቸውን ታማኝ የኢሳት ምንጮች ጠቁመዋል።
ከጠቅላ ሚኒስትሩ ደብዛ መጥፋት ጋር በተያያዘ በቤተመንግስት አከባቢ በተፈጠረው ቀውስና ትርምስ የተጨነቁት እነዚሁ የቤተሰብ አባላት የወ/ሮ አዜብ ታናሽ እህት ሶሻል ይልማ ሰርግ ለመሰረዝ መገደዳቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኢሳት ምንጮት ጠቁመዋል።
ምንም እንኳ ለዚህ ሰርግ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ሳይቀር ቁሳቁስና አልባሳት ተገዝተው የነበረ ቢሆንም ሰርጉ ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ታውቋል። ወይዘሪት ሶሻል ይልማ ከወ/ሮ አዜብ ጋር የሚዛመዱት በእናታቸው በወ/ሮ ቆንጂት ጎላ በኩል ሲሆን ከወ/ሮ አዜብ ምስፍን ቤተሰቦች ጋር የቅርብ ዝምድና ያለው አንድ የኢሳት ምንጭ በተለ በሃገር ቤት ያሉ የቤተሰብ አባላት በጭንቀት መዋጣቸውን ገልጧል።
በተለይ የወ/ሮ አዜብ እናት ወ/ሮ ቆንጂት ጎላ ስለ አቶ መለስም ይሁን ስለ ልጃቸው ጉዳይ ምንም እንደማያውቁና ወ/ሮ አዜብ በአሁኑ ጊዜ የት እንደሚገኙ በውል ባለማወቃቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ለቅርብ ዘመዶቻቸው መናገራቸው ታውቋል።
No comments:
Post a Comment