Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, August 13, 2012

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአረብሳት ላይ እንዲወርድ ተደረገ

የኢሳት ዜና:- ቴሌቭዝን የሳተላይት ስርጭት በኢትዮጵያ መንግስት መታወኩ ታወቀ። ይሄንን ተከትሎም፤ የአረብ ሳት የኤትዮጵያ ቴሌቭዥንን ከሳተላይት ስርጭት አግዷል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሜኒሳቴር ባለስልጣናት፤ አረብ ሳት በኤርትራ ቴሌቭዥን ላይ የሚያካሂደውን የማወክ ተግባር የማስቆም ህጋዊና ተቆማዊ ሀላፊነት እንዳለበት አሳስቧል።

አረብ ሳት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ከአየር ከማውረድ ባሻገር የሄደበት ቀጣይ እርምጃ ስለመኖሩ አልታወቀም። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከኧረብ ሳት ከመውለዱ በፊት የኤርትራ ቴሌቭን በሚታወክበት ወቅት ኢቲቪም እብሮ ሲታወክ ቆይቶል።


የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኔስቴር ባለስልጣን አቶ ይሳቅ ያሬድ፤ ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግስት ለቴክኖሎጂ ያለውን ባእድነትና የራሱ ቴሌቭዥን ጣቢያን ዋጋ ቢስነት ነው ሲሉ ለዜና ሰዎች ገልጠዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከይዘቱ ባሻገር የድምጥና የምስል ችግር ያለበት አማተር  ደረጃ ላይ ኧንኳን መድረስ ያልቻለ ሚዲያ ነው ሲሉም ተችተዋል።

የኤርትራ ቴሌቭዥን ዳይሬክተር አቶ አስመላሽ አብርሀ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ላይ ውንብድና እውነት ለመጋፈጥ አቅም እንደሌው ያሳያል ብለዋል።

የኢሳት ቴሌቪዥን ስርጭት መጀመሩን ተከትሎ ከ2002 ግንቦት ወር ጀምሮ የሳተላይት ስርጭት ማፈኛ ወይንም ማወኪያ ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ሲገለጥ ቆይቶል። የኤርትራ ቴሌቭን የአማርኛ አገልግሎት የተወሰኑ የኢሳት ፕሮግራሞች ማቅረቡን ተክትሎ የኤርትራ ቴሌቭዥንም በተመሳሳይ መመታቱ ተዘግቦል።

ይህንንም ተከትሎ መቀመጫውን ሪያድ ሳውዲ አረቢያ ያደረገው አረብ ሳት ኩባኒያ የኢትዮጵያ ቴሌቭዠንን ከአየር ላይ አውርዶ ነበር።  የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ወደ አየር ለመመለስ ያቀረቡት ጥያቄም ማላሽ ሳያገኝ ጊዜያት ከወሰደ በሆላ በቅድመ ሁኔታ የኢትዮጵያ ቴሌቭዝን ባለፈው ሰኔ ወር ወደ አየር ተመልሶ ነበር። 

የኢትዮጵያ መንግስት የተቀበለው ቅድመ ሁኔታም የኤርትራ ቴሌቭዥን ስርጭትን አላወክም የሚል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት ወደዚህ ስምምነት ከመምጣቱ በፊት ከአዲስ አበባ የሚሰራጨውን የኤርትራ ተቃዋሚዎች ቴሌቭዥን ፕሮግራም ለማቋረጥ፤ በምላሹም ኤርትራ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን ፕሮግራም እንዲያቋርጥ፤ በተለይም የኢሳት ፕሮግራሞችን እንዳያስተላልፍ ጠይቆ ነበር።

ሆኖም የኤርትራ መንግስት የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ፕሮግራም ብትፈልጉ በቀን ለ24 ሰአት አሰራጩ በማለት አማራጩን በመግፋቱና የድርድር ነጥቡን አልቀበልም በማለቱ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለበት ሁኔታ ስምምነቱን ለመቀበል ተገደደ።

በዚህ ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ ቴሌቭን ጣቢያዎች የፈለጉትንና የፈቀዱትን ማስተላለፍ ቢቀጥሉም፤ ከአንድ ወር በኋላ የአቶ መለስ ዜናዊ መሰወርና የጤንነታቸው ሁኔታ መባባሱን፤ በኋላም ህልፈታቸው መገለፁን ተከትሎ የኤርትራ ቴሌቭዥንን ማወኩን ቀጠለ። በምላሹም አረብሳት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ከአየር ላይ አውርድቶታል።

No comments:

Post a Comment