Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, May 14, 2012

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ፕሬዝዳንት መንግሥት ለደህንነታቸው ከለላ ሰጣቸው

ኢሳት ዜና:-
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ፕሬዝዳንት ሸህ አህመዲን ሸህ አብድላሂ ጩሌ የኢህአዴግ መንግሥት ለደህንነታቸው ሲል ባመቻቸላቸው ቤት ውስጥ መኖር መጀመራቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች አስታወቁ፡፡

የአዲስ አበባ እና አካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ በአወሊያና ሌሎች መስኪዶች የመጅሊስ ይፍረስና የኢህአዴግ መንግሥት በላያችን ላይ በሥልጠና በግድ የሚጭነውን የአሕባሽ አስተምህሮ  ያንሳልን ሲሉ የተጠናከረ ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ መጅሊሱ የሰጣቸውን ፒያሳ በኒ መስጂድ ገባ ብሎ የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው ወጥተዋል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ አህመዲን ሸህ አብድላሂ ጩሌ መንግሥት ደህንነታቸው የሚጠበቅበት ቤት ጦር ኃይሎች ቶታል አካባቢ ቀደም ሲል የትምህርት ሚንስትር የነበሩት ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ይኖሩበት የነበረውን በአምስት መቶ ካሬ ሜትር ላይ ተንጣሎ የሚገኘውን ቪላ ቤት ከሰጣቸወ በሁዋላ በደህንነት ሰዎች 24 ሰአት ሙሉ እየተጠበቁ  ናቸው ።

ከኢህአዴግ መንግሥት ጋር ሚሥጥራዊ ሥምምነት በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የአሕባሽን አስተምህሮ  በግድ በሥልጠና እንዲሰጥ የተባበሩት ሸህ አህመዲን ሸህ አብድላሂ በመጪው ሁለት ወራት ውስጥ ሥልጣናቸውን ይለቃሉ ቢባልም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ያካሂደዋል የተባለው ምርጫ በቀበሌና በዑላማዎች ምክር ቤት ስለሚካሄድ ተመልሰው የመመረጥ አሊያም ደጋፊዎቻቸው ቦታውን እንደሚይዙ በመንግሥት ቃል ተገብቶላቸው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment