By www.ecadforum.com
በሚያዝያ 28 – 2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በሰሜን ጎንደር፣ ሰሮቃ ልዩ ስሙ እምቡጉዳድ
በሚባል ስፍራ ከወያኔው ልዩ ሀይል ጋር ባካሄደው አውደ ውጊያ ዘጠኝ ወያኔ ገድሎ ሶስት ያቆሰለ ሲሆን
እንቅስቃሴውን በአካባቢው በማስፋፋት ህዝቡን የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን አሰራጭቷል።
የተበተኑት ወረቀቶች ከያዙት መልእክቶች ውስጥ፦
- በዋልድባ ገዳምና በተለያዩ የሀይማኖት ተከታዮች ላይ ለከት የለሽ ጥቃት በሚሰነዝረው ወያኔ ላይ ተነስ!
- ኢትዮጵያዊነት መንፈስና ስሜትን ለማጥፋት በሚባዝነው ጎጠኛ ላይ ተነስ!
- ዲሞክራሲያዊ መብትህን ገፎ ለስደት በዳረገህ ኢ-ፍትህአዊ አገዛዝ ላይ ተነስ!
- አገሬውን እንደ ግዑዝ ከቦታ ቦታ በሚያሰድደው ጠባብ ላይ ተነስ!
- የሀገሪቱን ሀብት ጥቅልሎ በመያዝና በመበዝበር ህዝቡን በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ችግር እንዲሰቃይ በዳረገው የጸረ-አንድነት ቡድን ላይ ታጠቅ!
ተነስ! ታጠቅ!
አንድነት ሀይል ነው!
የኢህአግ ፖለቲካ መምሪያ
ይህ በዚህ እንዳለ… የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በግንቦት 5 – 2004 ዓ.ም በርካታ ምልምሎችን
አሰልጥኖ አንዳስመረቀ ለማወቅ ተችሏል። ከሰልጣኞቹ መካክል ሴቶችም የሚገኙበት ሲሆን ስልጠናውን በብቃት ተከታተለው
ጨርሰዋል።
get lost... we dont want war anymore!!!!
ReplyDelete