Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, May 18, 2012

የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቡድን 8 ጉባኤ መጋበዝ

ዩናይትድ ስቴትስ ካምፕ ዴቪድ ዉስጥ በሚካሄደው የቡድን 8 ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የውይይቱ ተካፋይ እንዲሆኑ መጋበዝ ልክ አይደለም በማለት ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገተው የጀርመን ድርጅት መጨረሻ ጋዜጣዊ መግለጫ አዉጥቷል። 

የኢትዮጵያ መንግስት ለውጭ ሀገር ድርጅቶች እና ባለሀብቶች መሬት በሊዝ የሚሰጥበት ፖሊሲ ትክክል አለመሆኑን ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገት አንድ የጀርመን ድርጅት ባለፈው አርብ ባወጣው የፕረስ መግለጫ ገልጿል። 

በዚሁ ሰባት በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ምዕራብ አገራት እና ሩሲያ በሚካፈሉበት የቡድን 8 ጉባኤ ላይ ከአፍሪቃ ከተጋበዙት አራት መሪዎች መካከል ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አንዱ ናቸው። የዮናይትድ እስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጉባኤው ላይ ከአፍሪቃውያኑ መሪዎች ጋ በአህጉሩ በየጊዜው የሚከሰተውን ረሀብና የምግብ እጥረትን መታገል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገተው የጀርመን ድርጅት ተጠሪ ኡርሊሽ ዴሊዎስ ይህንኑ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በሀገራቸው በሚከተሉት የመሬት ይዞታ የተነሳ በካምፕ ዴቪዱ ጉባዔ ላይ አፍሪቃን ወክለው ሊናገሩ አይችሉም። ለተጨቆኑ ህዝቦች የሚሟገተው ድርጅት ያወጣው ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጠቅሶ እንደገለፀው፣ በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስን ያክል ስፋት ያለው መሬት ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች ዝግጁ ተደርጓል። 

ግን የድርጅቱ ተጠሪ ዴሊዮስ እንደሚሉት፣ ይህ መሬት ሕዝብ የማይገለገልበት ባዶ መሬት ሳይሆን ከ100 000 የሚበልጥ የአባባቢው ህዝብ የኑሮ መሰረቱን የገነባበት ነው ሲሉ አሰራሩን ነቅፈውታል። 

 እና ቡድን 8 በዚሁ የመሬት ፖሊሲ አኳያ ሊወስደው ይገባል ያሉትን ርምጃ ሲያብራሩ፤ «መለስ ዜናዊ በሀገራቸው የሚከተሉት የግብርና ፖሊሲ ውጤት በ10 ሺ ለሚቆጠሩ አነስተኛ የኢትዮጵያ ገበሬዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ እንዲጠየቁበት እንፈልጋለን።

 ይህ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ስለሚታየው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተለይም በመገናኛ ብዙኃን ላይ በሚወስዱት ጠንካራ ርምጃ፣ እና የኢንተርኔት አምደኞችን ፣ጋዜጠኞችን በሚያስሩበት አሰራራቸውም እንዲጠየቁበት እንፈልጋለን። እና እነዚህን የመሳሰሉ ጉዳዮች በፍፁም በቸልታ ሊታለፉ አይገባም። ካለበለዚያ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሀገሮች ተአማኒነታቸውን ያጣሉ።» ኢትዮጵያ ውስጥ በብዙ ሺህ ሄክታር የሚቆጠር መሬት ለህንድና ለሳውዲ አረቢያ ባለሀብቶች እንደተሰጠ ይታወቃል።

 ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የአፍሪቃ ሀገሮች ከእነዚህ ሁለት የእስያ አገሮች ጋ ባደረጓቸው ስምምነቶች፣ ከአፍሪቃውያቱ ሀገሮች ጋ በአጋርነት እንደሚሰሩ እና ሁለቱም ወገኖች ትርፋማ የሚሆኑበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር ይናግራሉ። እና ባለሀብቶቹ ወደ አዳጊ አገሮች ሄደው ገንዘባቸውን በሚያሰሩበት ጊዜ፤ በርካታ የግብርና መሳሪያዎች ወደ አገሪቱ ሊገቡና የስራ ዕድል የሚፈጠርበት አጋጣሚም ሊኖር እንደሚችል የሚሰማው ሀሳብ ስህተት አለመሆኑን ኡርሊሽ ዴሊዎስ ቢናገሩም በተግባር እየታየ ያለው ሁኔታ የተለየ መሆኑን ነው የገለጹት።
 
« በርግጥ ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት አሰራር ኖሮ ቢሆን ኖሮ እኛ ሁኔታውን አንቃወመውም። ግን ኢትዮጵያ ለአንድ ሔክታር መሬት በአመት 90 ሳንቲም ብቻ ካገኘች ትርፏ ምኑጋ እንደሆነ አይገባንም። እና መሬትን ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች የማከራየቱ ሁኔታ አንዳችም ትርፍ አያስገኝም።

 እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ይህ አሰራር ለአጠቃላይ የሀገሪቱ ኤኮኖሚያዊ ዕድገት ማለትም ኤክስፖርቱን የሚጠቅም እና የአካባቢውን ህዝብ ኑሮ ማሻሻል መቻሉን ማሳመኛ አላቀረበም። ስለሆነም ይሄ ሰፊ መሬትን ለውጭ ባለሀብቶች የማከራየቱ ፖሊሲ ሁኔታ የተሳሳተ አካሄድ ሆኖ እናየዋለን።»

Source: http://www.dw.de/dw/article/0,,15952039,00.html

No comments:

Post a Comment