ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በሶማሊያ በበለደወይን አካባቢ በመንገድ ላይ
የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጉዳት ማድረሱን መረጃዎች አመልክተዋል።
ፍንዳታው የተከሰተው
የኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ፣ ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ለማምራት ጉዞ ሲጀምር ነው። ምንም እንኳ የሟቾች
ቁጥር ባይገለጠም፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ ሁለት ሲቪሎችን መግደላቸው ታውቋል።
እስካሁን
ድረስ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰው አልታወቀም። የኢትዮጵያ ወታደሮች አካባቢውን አጥረው ፍተሻ መጀመራቸው ታውቋል።
No comments:
Post a Comment