ኢሳት ዜና:-
ከቃልቲና እና ከቂልንጦ ማረሚያ ቤቶች ለኢሳት በተላከው ስም ዝርዝር ላይ ለመመልከት እንደሚቻለው ፣
በሁለቱ እስር ቤቶች ብቻ በመለስ መንግስት የሀሰት ክስ ተከሰው ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ 401 ሰዎች አሉ።
አብዛኞቹ
የታሰሩት ከግንቦት7 እና ከኦነግ ጋር በተያያዘ ነው። በብሄር ተዋጽኦም አብዛኞቹ አስረኞች የኦሮሞና የአማራ
ተወላጆች ናቸው። በአቶ አንዱአለም መዝገብ 24፣ በአቶ በቀለ ገርባ 9፣ በጄ/ል ተፈራ ማሞ 46፣ በአቶ ተሻለ በኬ ፣ 69፣
በአቶ አል አህመድ ሰኢድ 33፣ በአቶ አሸናፊ አዱኛ 22፣ በአቶ ጌትነት ገመቹ 20፣ በአቶ ደጃሳ ወርቁ፣ 22 እና
በአቶ ደበላ ጣፋ 35 እስረኞች ለአብነት ያክል ተጠቅሰዋል።
ከእነዚህ መካከል 217 እስረኞች ከእድሜልክ
እስከ 15 አመታት የተፈረደባቸው ሲሆን፣ 184ቱ ደግሞ እስካሁን ፍርድ አላገኙም። አብዛኞቹ እስረኞች የመገናኛ
ብዙሀንንና አለማቀፉ ማህበረሰብ የማያውቃቸው ናቸው። የመለስ መንግስት ለስልጣኑ የሚያሰጋውን ሁሉ ለእስር በመዳረጉ ዘወትር በአለማቀፍ ድርጅቶች ይወቀሳል። ኢሳት በድረገጹ የፖለቲካ እስረኞችን ስም ዝርዝር ይፋ ያደርጋል።
ከዚሁ
ጋር በተያያዘ ምናልባትም በሰኔ ወር ውስጥ የአውሮፓ ህብረት አንድ ጉባኤ ለማዘጋጀት እንዳቀደ ለማወቅ ተችሎአል።
የኢሳት ታማኝ የዲፐሎማቲክ ምንጮች እንደሚሉት ህብረቱ በአለም ደረጃ ታዋቂ ከሆኑት እና ብዙ የማግባቢያ ( ሎቢ)
ስራ ከሚሰራላቸው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ከመሳሰሉት እስረኞች በስተቀር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ እስረኞች
መረጃ የለውም።
በሰኔው ጉባኤ የእስረኞችን ስም ዝርዝርና ፎቶ በጉባኤ አዳራሹ ውስጥ ለማስቀመጥ እንቅስቃሴ መጀመሩን
ለማወቅ ተችሎአል።
No comments:
Post a Comment