By መ/ር ቀለሙ ሁነኛው, Finote Netsanet
የሰው ልጅ ምን ቢጀግን ጥቂት ፍርሃት በውስጡ ትኖራለች፡፡ ይህች ቅንጣት ፍርሃት በእድሜ ርዝማኔ እያቆጠቆጠች ጀግንነቱን ልትሸረሽረው ትችላለች፡፡ “የውሃ ጠብታ አለትን ትበረብራለች” እንዲሉ፡፡ ከሁሉም በላይ የሰው ልጅ አይቀሬውን ሞት ይፈራል፡ ፡ ምን ቢቸገሩ ምድራዊ ህይወት ታጓጓለች፡፡ የኢራቁ ሳዳም ሁሴን በአሜሪካ መራሹ ህብረ ብሄር ጦር ላይ ሲፎክሩ ከርመው በመጨረሻው ከተሸሸጉበት ጉድጓድ ወጥተው በስቅላት የሞትን ፅዋ ተጎነጩ፡፡
ቅምጥሉ ሙአመር ጋዳፊ ተቃዋሚዎቻቸውን “በረሮዎች፣ አይጦች . . .” እያሉ ሲዝቱባቸው ቆይተው ተሸሽገው ከነበረበት የውሃ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ሲያዙ “Don’t kill me” ሲሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፡፡ ወኔ ከዳቸውና ሞታቸው የተራ ወሮበላ ሞት ሆነ፡፡ ሞትን ፈርተው መኖርን ቢመኙም በነገሱባቸው ረጅም አመታት የሰሩት ግፍና ኢ-ሰብአዊ ተግባር ህይወትን ነፈጋቸው፡፡ ወደ ገፅ 14 ይዞራል.... ወደ ገፅ 8 ይዞራል.... በአለማችን ላይ ብዙዎች ራሳቸውን በሞት ይቀጣሉ፡፡ በህይወት ሳሉ ከመሰቃየት ለዘዓለለም መሰናበት ዕረፍት መስሎ ይታያቸዋል፡፡
በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምን ጊዜም ጀግናችን አድርገን የምናስባቸው አፄ ቴዎድሮስ በጠላት እጅ መውደቅን ፈርተው ሞትን ደፈሩ፡፡ በውርደት ከመኖር በሞት መሰናበትን መረጡ፡፡ “ስም ከመቃብር በላይ ይውላል” እንዲሉ ስማቸው ምንጊዜም ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡ ሕወሓት/ኢህአዴግን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የመሩት ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ በ17 ዓመታት መራር ትግል ውስጥ የነበራቸውን ሚና በተመለከተ አያሌ ፀሐፍት ብዙ ብለዋል፡፡ የትግል አጋሮቻቸው ይመሰክራሉ፡፡
አቶ መለስ በጦር ግንባር ላይ በመሰለፍ ረገድ የነበራቸው ድርሻ ኢምንት እንደሆነ ይነገራሉ፡፡ ጠብመንጃ ደግነው ምላጭ የሳቡባቸው ወቅቶች ከፍ ሲል ከነ ጄኔራል ሀይሎም አርአያ ዝቅ ሲል ደግሞ ከነታምራት ላይኔና ተፈራ ዋልዋ ተርታ አያሰልፋቸውም፡፡ እሳቸው ትናንትም ሆነ ዛሬ የፖለቲካው ቁማር ዘዋሪ ናቸው፡፡ የቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ መሽገው የእነ ማኬቬሌንና የእነ ማኦሴቱንግን ፍልስፍና የሚያጠኑ ተጋዳላይ ነበሩ፡፡ በወቅቱ ለፍርሃት የሚዳርጓቸውን ነገሮች ለማስወገድ ጊዜ አያባክኑም፡፡ ዛሬም ቢሆን ከጨዋታ ውጭ ማድረግን ተክነውበታል፡፡
ፍርሀት አንድ፡- ዘፈንና ዘፋኞችን (ሙዚቃ) መፍራት የጥንቶቹ ነገስታት በጦር ሜዳ ውሏአቸው ለሚያስመዘግቡት ድል ሽለላና ፉከራ ወኔ አቀጣጣይ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ጀግኖች አባቶቻችን እየሸለሉና እየፎከሩ በዋሉበት የጦር ሜዳ ድልን ዘክረዋል፡፡ ሕወሓት ሽምቅ ተዋጊዎች የጀግና ዘፈን ሞተራቸው ነበር፡ ፡ በተፋፋመ ጦርነት ላይ እያሉ ከበስተኋላ የሚሰሙት የከበሮ ድምፅና የክራር ቅኝት እንዲሁም ዘፈን ደረታቸውን ለጥይት እንዲሰጡና ጥለው እንዲወድቁ ያጀግናቸው ነበር፡፡
በጦሩ መሀል የሚቋቋሙት የኪነት ቡድኖች ከተዋጊው ጀርባ ጠብመንጃ ካነገበው ሽምቅ ተዋጊ የማይተናነስ የጀግንነት ተግባር ፈፅመዋል፡፡ ወታደራዊው ደርግም ከወያኔና ከሻዕቢያ ጋር በነበረበት ጦርነት ይህንን ለመጠቀም ሞክሯል፡፡ በየክፍለ ጦሩ የኪነት ቡድኖችን እያቋቋመ የጦር ሠራዊቱን የውጊያ ሞራል ለመገንባት ጥሯል፡፡ አልፎ ተርፎ ነፍሱን ይማረውና ታዋቂውን ድምጻዊ ጥላሁን ገሰሰን ከታዋቂ የሙዚቃ ባንድ ጋር ወደ ሰሜን አዝምቶ ነበር፡፡ ጥሌ በመረዋ ድምፁ፡-
“ግፋ በለው፣
ገስግስ በለው
ግደል ተጋደል በርታ ወገኔ
በጥንቱ ታሪክ በባትህ ወኔ”
እያለ ሲዘፍን ሠራዊቱ ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ አቶ መለስ የስልጣን ኮርቻው ላይ ከወጡ በኋላም በህዝብ ዘንድ የሚወደዱ ድምፃውያን የዘፈን ግጥሞቻቸው የሰነቁትን ጭብጥ በብርቱ ይፈትሹ ነበር፡፡ ባንድ ወቅት ኦነግ የሽግግር መንግስቱን ጥሎ ከአገር ከወጣና የትጥቅ ትግል ካወጀ በኋላ ኦሮሚያ ክልል ላይ የነበረው እንቅስቃሴ ያሰጋቸው አቶ መለስ የኦህዴድ ከፍተኛና መካከለኛ ካድሬዎችን ሰብስበው ወርፈዋቸዋል፡፡ “ከሺህ የኦህዴድ ካድሬ የፀጋዬ ደንዳና አንድ ሙዚቃ አገር ያናውጣል፡፡” ሲሉ የካድሬዎችን ብቃት ተችተዋል፡፡
“ግፋ በለው፣
ገስግስ በለው
ግደል ተጋደል በርታ ወገኔ
በጥንቱ ታሪክ በባትህ ወኔ”
እያለ ሲዘፍን ሠራዊቱ ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ አቶ መለስ የስልጣን ኮርቻው ላይ ከወጡ በኋላም በህዝብ ዘንድ የሚወደዱ ድምፃውያን የዘፈን ግጥሞቻቸው የሰነቁትን ጭብጥ በብርቱ ይፈትሹ ነበር፡፡ ባንድ ወቅት ኦነግ የሽግግር መንግስቱን ጥሎ ከአገር ከወጣና የትጥቅ ትግል ካወጀ በኋላ ኦሮሚያ ክልል ላይ የነበረው እንቅስቃሴ ያሰጋቸው አቶ መለስ የኦህዴድ ከፍተኛና መካከለኛ ካድሬዎችን ሰብስበው ወርፈዋቸዋል፡፡ “ከሺህ የኦህዴድ ካድሬ የፀጋዬ ደንዳና አንድ ሙዚቃ አገር ያናውጣል፡፡” ሲሉ የካድሬዎችን ብቃት ተችተዋል፡፡
በዘመናችን ስማቸው በፍጥነት ገንኖ ከወጡ ድምጻውያን መሀከል ወጣቱ ሙዚቀኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን “ቴዲ አፍሮ” ተወዳዳሪ አይገኝለትም፡፡ በተለይም ወጣቱ “. . . አዲስ መንግስት እንጂ ለውጥ መቼ መጣ” የተሰኘው የሙዚቃ ግጥም ለአቶ መለስ ግዙፍ መርዶ ሆነ፡፡ ኢህአዴግ ለአመታት የኳተነበትን የልማትና የዕድገት ፕሮፓጋንዳ የቴዲ አንድ ዘፈን መሬት ላይ ፈጠፈጠው፡፡ አርቲስቱም በአቶ መለስ ጥርስ ውስጥ ገባ፡፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሕዝብ ዘንድ ያለውን ዝና ለማደብዘዝ ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም ቴዎድሮስ ታደሰ በክብር ታጅቦ ከአሜሪካ አዲስ አበባ ገባ፡፡
ሚዲያዎች ሁሉ ያን ሰሞን ቴዎድሮስ ታደሰን አነገሱ፡፡ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃዎች በኢቴቪ እና በሬዲዮ እንዳይተላለፍ መመሪያ የተላላፈ ይመስል ዛሬም ቢሆን በተከታታይ አይቀርቡም፡፡ አቶ መለስ ወደረኞቻቸውን የሚበቀሉት ቀናት ቆጥረውና አድብተው በመሆኑ አርቲስቱ በመኪናው ሰው ገጭቶ ገድሏል በሚል ሰበብ ተከሶ ዘብጥያ ወረደ፡ ፡ አቶ መለስም የፍርዱ ሂደት በሚታይበት ሰሞን “የአዲስ አበባ ህዝብ ብዙ መሠረታዊ ችግሮች እያሉበት አንድ ዘፋኝ ለምን ታሰረ ብሎ ይጮሀል” ሲሉ ተናገሩ፡፡
የድምፃዊው መታሰር ግን እጅግ የላቀ እውቅናን አስገኘለት እንጂ አልጐዳውም፡፡ በሚሊዮን በሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ዛሬም እንደገነነ አለ፡፡ ለፋሲካ በዓል በለቀቀው አልበሙ ምድሪቱ እየተናወጠች ስናይ ህዝቡ ለእሱ ያለውን ፍቅር እናስተውላለን፡፡ ሁሉም የዘፈኖቹን የግጥም ስንኞች እንደ እውቀት ደረጃው እየመረመረ ከኢህአዴግ ፖለቲካ ጋር ሲያያይዘውና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሲያቆራኘው ይደመጣል፡፡ እርግጥ የቴዲ አፍሮ አልበም በተለቀቀ ቁጥር በኢህአዴግ ቤት የፍርሃት መርዶ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምስራች እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ ካንድ የመድፍ ጥይት የአንድ ክራር ቅኝትና የከበሮ ድለቃ ለህወሓቶች የላቀ ዋጋ እንዳላቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡
ለዚህም ከነሱ ርዕዮት ፈንገጥ ባሉ አርቲስቶች ላይ የማይቀኙት፡፡ ፍርሃት ሁለት፡- መያዶች NGO (መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ለህወሓት /ኢህአዴግ ድል የመያዶች አስተዋፅኦ የላቀ ነበር፡፡ ደርግ ይከተለው የነበረው የሶሻሊዝም ርዕዮት ዓለም (Ideology) ከምዕራቡ ዓለም ጋር በብርቱ ያቃቃረው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ በየአደባባዩ ክንዳቸው እስኪዝል ድረስ የአሜሪካንን ኢምፔሪያሊዝም ማውገዛቸውና የኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በአሜሪካ መንግስት ዘንድ ተፈላጊ በመሆኑ በወቅቱ ህወሓት በምዕራቡ ዓለም ተቀባይነት ነበረው፡፡ በዚህ መነሻነት በሰብአዊ ድርጅቶች ሰበብ የህወሓት መሪዎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኙ ነበር፡፡ አልፎ ተርፎ በእርዳታ ሰበብ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍም ነበራቸው፡፡
በወቅቱ ህወሓት ድል አድርጎ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች መያዶች ያደረጉት የምግብና የቁሳቁስ እርዳታ በምስጢር ተሸጦ ለጦር መሣሪያ መግዣ እንደዋለ የቢቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባንድ ወቅት እንደ ዘገበውና አቶ መለስን እንዳስቆጣቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር በምርጫ 97 ዓ.ም የውጭ እርዳታ ድርጅቶች (መያዶች) የምርጫው ውጤት የተጭበረበረ መሆኑን አሳማኝ መረጃዎችን በመያዝ ለአሜሪካና ለአውሮፓ ህብረት ማቀበላቸው ኢህአዴግን በብርቱ አሸብሮታል፡፡ በምስራቅ ኢትዮጵያ ኦብነግን ለመውጋት በተደረገው መጠነ ሰፊ ዘመቻ በክልሉ ሠላማዊ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ይፋ በማውጣታቸውና የኢህአዴግ መንግስትን የሚያሳጡ በመሆናቸው እንደ ቀይ መስቀል የመሳሰሉ ሰብአዊ ድርጅቶች በአካባቢው እንዳይንቀሳቀሱ እስከ ማገድ ተደርሷል፡፡
አንዳንዶቹም ድርጅታቸውን ዘግተው ከአገር እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ በወሰዷቸው ጊዜያዊ እርምጃዎች ያልረኩት አቶ መለስ አሳሪ ህጎችን ለመደንገግ ጊዜ አላበከኑም፡፡ ሀገር በቀል እና የውጭ መያዶችን እንቅስቃሴ የሚያሽመደምድ ህግ በፓርላማ ፀድቆ ተግባር ላይ ዋለ፡፡ ታላላቅ የአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና የምዕራቡ ዓለም መንግስታት በብርቱ ቢቃወሙም አቶ መለስ “ወይ ፍንክች የአቦይ ዜናዊ ልጅ” ሲሉ በአቋማቸው ፀኑ፡፡ ዛሬ የእያንዳንዱን መያድ /NGO እንቅስቃሴ ኢህአዴግ በአይነ ቁራኛ ነው የሚከታተለው፡፡ ፍርሃት ሦስት፡- ጋዜጠኞችን መፍራት በየትኛውም ዓለም የሚታተሙ ጋዜጣዎች ያለ ጋዜጠኞች አይታሰቡም፡፡
አንድ ጋዜጠኛ የዘወትር ተግባሩ እውነትን ያለ ማድላት አንጥሮ በማውጣት ለህዝብ ማቅረብ ነው፡፡ በአደጉት አገሮች ለአገር ሕልውና የሚያሰጋ ድርጊት እንኳን ቢሆን ጋዜጠኛው ምስጢሩን ፈልፍሎ ለአደባባይ ያበቃዋል፡፡ ለአብነት ያህል እንኳን ብንጠቅስ አሜሪካ በጓንታናሞ ቤዝ በምታጉራቸው እስረኞች ላይ የምትፈፅመውን ድብቅ ኢ-ሰብአዊ ተግባር ፈልፍለው አውጥተዋል፡ ፡ አሜሪካ በተለይም በአረቡ አለም ዘንድ ውግዘት ገጥሟታል፡፡ እንደዚሁም በኢራቅ ውስጥ የአሜሪካን ወታደሮች በእስረኞች ላይ ይፈፅሙ የነበረውን አሰቃቂ ተግባር ይፋ አድርገውታል፡፡
ሌላው አስገራሚ ነገር የአሜሪካን 42ኛው ፕሬዚደንት የነበሩት ቢል ክሊንተን ሥልጣን ላይ እያሉ ሞኒካ ከምትባል ሴት ጋር በሚስጥር መማገጣቸውን ለአለም ህዝብ ይፋ ያደረጉት (ፕሬዝዳንቱን ፍርድ ፊት ያስቆሙት ጋዜጠኞች ነበሩ፡፡) ይሄ ታዲያ የሚቻለው አፍሪካ ውስጥ እንዳይመስላችሁ፡፡ አሜሪካ ወይም እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን በመሳሰሉ ዴሞክራሲ በጐለበተባቸው አገራት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ባካሄደው የ17 ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ የጎላ አስተዋፅኦ ካበረከቱ ጋዜጠኞች መሀከል ደራሲና ጋዜጠኛ በአሉ ግርማን የሚወዳደረው የለም፡፡
ደርግን የሚያህል አስፈሪና “ሰው በላ” መንግስት የአደባባ ህፀፁን በብዕር መንቀፍ ውጤቱ ሞት ነው፤ ያውም በአደባባይ መረሸን (አብዮታዊ እርምጃ! ኦሮማይ!) በመንቀፉ እሱም የሞትን ፅዋ ተጎንጭቷል (ኦሮማይ) የበዓሉ ግርማ የብዕር ትሩፋቶች ዘመን ተሻጋሪ እንደሆኑ አያሌ ምሁራን ይመሰክራሉ፡፡ በኢትዮጵያ የስነ ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ለውጥ ያመጣ በአፃፃፉ ቴክኒክና በአቀራረቡ ወደር ያልተገኘለት ደራሲ ነበር፡፡ መንግስቱ ኃ/ ማርያም እንኳን በብርቱ ያደንቁት እንደነበር ተናግረዋል፡ ፡ ነፍሱን ይማረውና ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሄርም መንግስቱ ኃ/ማርያም እንዳላስገደሉት በእርግጠኝነት ተናግሯል፡፡ በዓሉን ኦሮማይ የሬሳ ሳጥኑ ሆነ፤ መሞቻውና መቀበሪያው፤ በጦር መሣሪያ ለመድፈር የሚያስፈራውን ደርግ በብዕሩ ደፈረ፡፡
እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ አርዌል “Animal farm” በተሰኘው ዘመን በማይሽረው ልቦለድ ድርሰቱ ገሀድ ያወጣውን የነስታሊንን ገመና አካሄድ ተከትሎ ከኮሎኔል መንግስቱ ጀምሮ እስከ ዝቅተኛ ሹማምንት ድረስ በገፀ ባህሪነት የሳለበት ኦሮማይ በህወሓት በተለይም በሻዕቢያ ዘንድ ፍፁም አይወደድም፡፡ የእነሱም ገመና ተዳሷልና፡፡ በጦርነት ወቅት በጦር ሜዳ የዋሉ ከፍተኛ ማዕረግ የነበራቸው መኮንኖች ስለ በዓሉ ግርማ ድፍረት የሚናገሩት በአግራሞት ነው፡፡ በዓሉ ጥይት በጆሮ ግንዱ ስር እያለፈ ከወታደሩ ጋር የቀበሮ ጉድጓድ ወስጥ ሆኖ ሀቁን ይዘግብ እንደነበር ይመሰክሩለታል፡፡ ዛሬም ቢሆን ጋዜጠኞች የአቶ መለስ ብርቱ ስጋቶች ናቸው፡፡ ለእሳቸው የአንድ ጋዜጠኛ ፅሁፍ የኔቶ ሠራዊት በጋዳፊ ጦር ላይ ካዘነባቸው አደገኛ ቦምቦች በላይ ይገዝፉባቸዋል፡፡
የኔቶ ቦምብ የደረመሰው የድንጋይ ክምርና ተራውን ወታደር ሲሆን ጋዜጠኛው ብዕር ግን የሚያዘንበው የቃላት ናዳ በአቶ መለስና በሚመሩት ሥርዓት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ የእሳቸው ኢህአዴግ የሚፈፅመውን ህፀፅ ጋዜጠኞች ፈልፍለው ለህዝብ ጆሮ ባደረሱ ቁጥር ቁጣቸው ያይላል፡፡ የሀገር ውስጥም ሆኑ የውጭ ጋዜጠኞች በኢህአዴግ ዘንድ ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው፤ የኢቴቪ፣ የኤፍ ኤም ሬዲዮ እና የአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ካልሆኑ በቀር፡፡ እነዚያ አሸባሪዎች እነዚህ ደግሞ ልማታዊ ጋዜጠኞች እውነትን መናገር ሽብር ቅጥፈትን መደስኮር ግን ልማት የሆነባት አገር የዛሬይቱ ኢትዮጵያ በዓለማችን ላይ ጋዜጠኞች ለሞት፣ ለእስራትና ለስደት ከሚዳርጉባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያና ኤርትራ በቁንጮነት ይጠቀሳሉ፡፡
ከሁለት አመታት በፊት አዲስ ነገር ጋዜጣ ተዘግታ እነ መስፍን ነጋሽ ከአገር ተሰደዱ፣ በቅርቡ የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ በኢህአዴግ ወከባ ወደ አሜሪካ ተሸኝቷል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ የፍትህ ዋና አዘጋጅ በስበብ አስባቡ ፍርድ ቤት እየቀረበ ነው፡፡ ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣም ገና የአንድ ዓመት ልደቷን ሣታከብር ሳንካ እንደገጠማት ባለፈው እትም ላይ አንብበናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፀረ ሽብር ህጉ የተነሣ ኢትዮጵያ ውስጥ እውነትን አንጥረው የሚዘግቡ ጋዜጠኞችና ጋዜጣዎች ህልውና አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡ ዛሬ በቃሊቲው ማጎሪያ ብዙ ጋዜጠኞች በእስር ላይ ናቸው፡፡
ግማሹም ተፈርዶባቸው ሌሎቹ ፍርዳቸውን እየጠበቁ አገር ወዳዱና ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሀቅን በብዕሩ በማንጠቡ ዘብጥያ ከተወረወረ ወራቶች ተቆጠሩ፡፡ የአቶ መለስ መንግስት በአሸባሪነት ሲፈርጀው “pen International” የተሰኘው የጋዜጠኞችን ተግባር የሚዘክረው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የ2012 ተሸላሚ አድርጎ መረጠው፡፡ በ2004 ዓ.ም ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በቱሪስት መልክ ወደ አገር ውስጥ ገብቶ በደቡብ ህዝቦች ክልል በተለይም በከምባታና ሀዲያ ዞኖች የእርዳታ እህል ለኢህአዴግ የፖለቲካ ቅስቀሳ መዋሉን በሚስጥር በመዘገብ ለአለም ህዝብ ማሳወቁን ሰምተናል፡፡ ይህን ተከትሎ ኢህአዴግ ሁኔታውን ለማስተባበል ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፡፡
አልፎ ተርፎ በተከታታይ ሚዲያዎች ሲያወግዝ ነበር፡፡ የአሥራ አንድ ዓመት እስራት የተፈረደባቸውም የስዊድን ጋዜጠኞች ከአቶ መለስ ፍርሃት በመነጨ ለሌሎች መቀጣጫ እንዲሆኑ ነው፡፡ መቼም በአገራቸው የተቀማጠለ ኑሮ የሚኖሩና ተርፏቸው እኛን ስንዴ የሚታደጉን ስዊድኖች አድፍጦ ጥይት ከመተኮስ የዘለለ አቅምም ሆነ አለም አቀፍ እውቀትና ለሌላው ኦብነግ ቅጥረኛ ሆነው ይመጣሉ ብሎ የሚያምን ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ እርግጥ ነው ኢ-ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በሚያቀነቅኑ መሪዎች ዘንድ ጋዜጠኞች ብርቱ ፍርሃትን ይፈጥራሉ፡፡
በየዕለቱ መሪዎችና መንግስታቸው በዜጎች ላይ የሚጭኑትን የጭቆና ቀንበርና የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት በማጋለጥ በህዝብ ዘንድ እንዲጠፉና አመኔታን እንዲያጡ ስለሚያደርጋቸው ፍርሀታቸው ትክክል ነው፡፡ “ምን ያለበት ዝላይ አይችልም” እንዲሉ መቼም የአቶ መለስ መንግሥት ጠቅልሎ የያዛቸው ብዙሃን መገናኛዎች የኢህአዴግን ቅድስና እንጂ እንከኑን አያወሩም፡፡ በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ሥር እየሰደደ የመጣ የብሄረሰብ ግጭት በየአቅጣጫው ይስተዋላል፡ ፡ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት የአገሪቱ ሀብት በየጊዜው በጥቂት ሹመኞችና ስግብግብ ነጋዴዎች እየተመዘበረ ከሀገር ይወጣል፡፡ የህዝብ ንብረት በጠራራ ፀሐይ ይዘረፋል፡፡
የኑሮ ውድነቱ የህዝቡን ጉሮሮ ሰንጎታል፡፡ ጠቅላይ ሚ/ሩም እስከዛሬ አምነው የሽንፈት ቃል ተናግረው አያውቁም ነበር፡፡ በሚያዝያ 9/2004 የፓርላማ ማርፈጃቸው ግን የመንግስታቸው አንድ እጅ በኪራይ ሰብሳቢዎች በመታሰሩ ሽባ እንደሆኑ አመኑ፡፡ ትግሉ መራራ ከመሆኑ የተነሳ “ወይ ኪራይ ሰብሳቢዎች ወይም ልማታዊነት ያሸንፋል” ሲሉ በተስፋ መቁረጥ ተናገሩ፡፡ በሊዝ ፖሊሲውም ዙሪያ “እንደ እንዝርት አሽከረከሩን፣ አጦዙን . . .” በማለት ያጋጠማቸውን እጅግ ፈታኝ መሰናክል ለኢትዮጵያ ህዝብ አሰሙ፡፡
ባለፈው ሰሞን ደግሞ በኦሮሚያ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ውስጥ ከእምነት ጋር በተያያዘ የተከሰተውን አሳሳቢ ግጭትና ግጭቱ ያስከተለውን ውጤት፣ እንዲሁም በጋምቤላ አካባቢ ለውጭ ባለሀብቶች በሊዝ በተሸጠ የእርሻ ሥራ ላይ በተሰማሩ የውጭ አገርና ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግድያ የኢህአዴ ብዙሃን መገናኛዎች መዘገባቸው የሚያመላክተው በአሁኑ ወቅት አንድን ክስተት በምስጢር መያዝ በማይችልበት ደረጃ መድረሳችንን ነው፡፡
ችግሮች እየተባባሱ በመምጣታቸው ሚዛን የደፉትን እንስማ እንጂ በመላ አገሪቱ በተለይም በገጠሩ አካባቢ የሚከሰቱትን አይደለም ገለልተኛ ጋዜጠኞች የኢህአዴግ ሚዲያዎችም እንዲሰሙትና እንዲዘግቡት አይፈቅድም፡፡ የየክልሉ ባለሥልጣናት ጉዳዩን ይደብቁታል፤ የችግሮቹም ፈጣሪዎች እነሱ ናቸውና፡፡ ዛሬ ለአቶ መለስና ለመንግስታቸው ቪኦኤና የጀርመኑ ዶቼቤሌ ሬዲዮ ጋዜጠኞች ብርቱ ፍርሃት ናቸው፡፡ ጣቢያዎቹን ለማፈን (ጃም ለማድረግ) ከፍተኛ የአገር ገንዘብ ዛሬም ይፈሳል፡፡ ከአሜሪካን መንግስት ጋርም በጉዳዩ ላይ ለመደራደር የተሞከረው ከ ፍርሃት በመነጨ ነው፡፡ ግና ምን ያደርጋል፤ አንድ ቀን “የፈሩት ይወርሳል” እንዲሉ መሆን የሚገባው መሆኑ የግድ ይላል፡ ፡
ከዚህ ሁሉ ግን ራስን በህዝብ መስታወት መመልከትና አካሄድን ማስተካከል፡፡ አሊያም እንደ ጀግናው አጼ ቴዎድሮስ የክብር ሞትን መድፈር ቢያዳግትም እንደ አንዳንድ አስተዋይ መሪዎች ስልጣን ለህዝብ ለማስከበር መድፈር በ21ኛው ክ/ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያችን የሚዘከር አኩሪ ተግባር ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ የሳምንት ሰው ይበለን !
No comments:
Post a Comment