Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, April 16, 2012

የአራዳ ክ/ከተማ ባለስልጣን ከግድያ ለማምለጥ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ዘለሉ

By Feteh News

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ የእረከበ ሱቅ (የኮንቲነር ሱቅ) በመስራት ላይ ያለ እንዲሁም ከ6 ኪሎ ፈረንሳይ ባለው የታክሲ ቀጠና ተራ አስከባሪ የሆነው ወጣት ‹‹የታክሲ ተራ አስከባሪም፣ ባለሱቅም ሆነህ መስራት አትችልም›› አለኝ ያለውን የወረዳ 6 ስራ አስፈፃሚ አቶ ሻረው ዘለቀ ላይ በክላሽንኮቭ መሳሪያ ያደረገው የግድያ ሙከራ ከሽፎበት በቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮቻችን
ገለፁ።
እንደምንጮቻችን ገላፃ ከአመት በፊት መንገድ ትራንስፖርት ‹‹በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጀ በታክሲ ተራ ማስከበር ስራ አይሰመራም›› በሚለው መመሪያ ሱቁ እንዳይነጠቅ በወደሙ ስም ለማዞር በወቅቱ የአነስተኛና ጥቃቅን ፅ/ቤት ኋላፊ ወደነበሩት አቶ ሻረው ዘለቀ ቢያመለክትም ጉደዩ ተቀበይነት ሳያገኝ ይቀራል፡፡ ይሁንና ተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረበ ሳለ ሳይመለስለት ቅሬታውን ለወና ስራ አስፈፃሚው እንዲያቀርብ ይነገረዋል፡፡ 

ወጣቱም ወደዋና ስራአስፈፃሚው ቢሮ ሲሄድ አቶ ሻረው ዘለቀን በእድገት ዋና ስራአስፈፃሚ ሆኖ ያገኛቸዋ ‹‹ከዚህ በኋላ›› አሉ ምንጮቻችን መፍትሄ አላገኝም ሲል ያሰበው ተጠርጣሪ ‹‹ሰኞ ሚያዝያ 1/2004 ዓ.ም. ከጠዋት 3፡30 ላይ በቀጥታ ወደ ወረዳው ፅ/ቤት ይሄድና ከጊቢው ጠባቂ አንድ ክላሽንኮቭ መሳሪያ በኃይል በመቀማት የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ወልዴ ላይ መሳሪያውን በመደቀን ዋና ስራአስፈፃሚው ወደሚገኙበት 4ኛ ፎቅ እንዲመሩ ያስገድዳቸዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ማራኪውና ተማራኪው 2ኛ ፎቅ ላይ ሲደርሱ ድንገት ለስራ ጉዳይ ከቢሮአቸው ወጥተው ወደታች እየወረዱ ከነበሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ጋር ፊት ለፊት ይገናኛሉ፤ በዋናነት የሚፈልገውን ኃላፊ ያገኘው ተጠርጣሪም በያዘው መሳሪያ ለመተኮስ ሙከራ ሲያደርግ መሳሪያው ነከሰበት፡፡ ይህን ጊዜም ዋና ስራ አስፈፃሚው ከጥይት ለማምለጥ ከ2ኛ ፎቅ ላይ ቁልቁል ራሰቸውን ወረወሩ፤ ከዚህ በኋላም ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውል ዋና ስራ አስፈፃሚውም እግራቸው ተሰብሮ ወደ ሆስፒታል ሄዱ ›› ሲሉ ምንጮቻችን በተለይ ለፍትህ ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment