በአባ ዙምራ
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጣው ላይ ባተማቸው ፅሁፎች የተነሳ የአራት ወር እስራት ወይም የ2000 ብር ቅጣት ተበየነበት፡፡ ጋዜጠኛ
ተመስገን ደሳለኝ የተከሰሰው በሽብርተኝነት ስም በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዱአለም አራጌ፤ የጋዜጠኛ
እስክንድር ነጋ፤ የአቶ ናትናኤል መኮንንና የአበበ ቀስቶን የፍርድ ቤት ቃላቸውን በማተሙ ነው፡፡
በዚህ የተነሳም
አቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ሲታይ የቆየ ሲሆን አበበ ቀስቶ(ክንፈሚካኤል አበበ) ለምስክርነት ተጠርቶ ሙሉ ቃሉ የእሱ
እንደሆነ መስክርዋል፡፡ ለሚያዚያ 22 ቀን 2004ዓ.ም የተቀጠረው ውሳኔም ጋዜጠኛ ተመስገን ላይ የአራት ወር
እስራት ወይም የ2000 ብር ቅጣት ሲበይን አበበ ቀስቶ ላይ የ8 ወር እስራት ፈርዶበታል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት ሚዲያዎች በተለይም በአዲስ ዘመንና አይጋ ፎረም ላይ በፍትህና አምደኞቹ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ መከፈቱ የሚታወስ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment