Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, April 29, 2012

 ፓርተር ጋዜጣ
 -    ንብረታቸው እንዲወረስ ትዕዛዝ ተሰጠ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት አቶ ዳኛቸው ካሣ፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ አምሳለ መኮንንና፣ አቶ ታደሰ ትዕዛዙ በእስራት እንዲቀጡ ሚያዝያ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ተወሰነ፡፡ ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ አቶ ዳኛቸው በዘጠኝ ዓመታት እስርና በ30 ሺሕ ብር፣ ባለቤታቸው በስድስት ዓመታትና በአንድ ሺሕ ብር፣ እንዲሁም የእሌኒ ማተሚያ ቤት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ በአራት ዓመታት እስርና በአንድ ሺሕ ብር እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡

ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ውሳኔ የአቶ ዳኛቸው ንብረት የሆነውና ግምቱ 610 ሺሕ ብር የሆነ የጋራ መኖርያ ቤትና አንድ ባለ አራት ፎቅ ሕንፃ ተሸጦ ለመንግሥት ገቢ እንዲደረግ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ቤቱ ከተሸጠ በኋላ ግለሰቡ ለቤት ማደሻ ያወጡት 195 ሺሕ ብር እንዲመለስላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አቶ ዳኛቸው የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው በሌሉበት ነው፡፡ ለቅጣቱ መነሻ የሆነው ወንጀል የተፈጸመው፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፋይል ፎልደሮችን ለመግዛት ያወጣውን ጨረታ እሌኒ ማተሚያ ቤት የሚባል ድርጅት አሸናፊነቱን ተገን በማድረግ፣ ከመንግሥት የፋይናንስ አዋጅና ግዥ መመርያ ውጭ ከድርጅቱ ተጨማሪ የፋይል ፎልደሮች እንዲገዙ በመደረጉና ለአቶ ዳኛቸው 170 ሺሕ ብር ከማተሚያ ቤቱ ሥራ አስኪያጅ በባለቤታቸው አማካይነት በመሰጠቱ መሆኑን መዘገባችን ታወሳል፡፡ 

No comments:

Post a Comment