Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, April 21, 2012

የቦብ ማሪሊንን የህይወት ታሪክ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም ተሰራ

ኢሳት ዜና:-
በኦስካር ተሸላሚው ኬቪን ማክዶናልድ የተሰራው ፊልም የቦብ ማርሊን ህይወት ከሚገልጹት ፊልሞች ሁሉ የተሻለ ነው ተብሎአል። ፊልሙ ቦብ ማርሊንን ብሄራዊ ጀግና ለማድረግ ለተጀመረው እንቅስቃሴ እገዛ እንደሚያደርግ ታውቋል።

በኪንግስተን ፓርክ በተደረገው የመክፈቻ ዝግጅት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጃማይካዊያን ተሳትፈዋል። በዝግጀቱ እለት ለመንግስቱ ባለስልጣናት መረማመጃ ተብሎ የተነጠፈው ቀይ ቢጫ እና አረንጓዴ ባንዲራ ፣ በተመልካቹ ተቃውሞ እንዲነሳ ተደርጓል። እነዚህ ሶስቱ ቀለማት ለጃማይካዊያን የተቀደሱ ቀለማት ናቸው።

በለጋ እድሜው የተቀጨው የሬጌ ሙዚቃ ንጉሱ ቦብ ማርሊን ፣ ጌት አፕ ስታንዳፕ፣ ኖ ውመን ኖ ክራይ በመሳሰሉት ውብ ዘፈኖቹ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment