Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, April 16, 2012

የአራት ኪሎ ነዋሪዎች እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለፁ

የፍትህ ዜና

በአራት ኪሎ ልዩ ስሙ ‹‹ባሻ ወልዴ ችሎት ሰፈር›› ተብሎ ለሚጠራው አካባቢ በቀበሌ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የወረዳ 8 ቀበሌ 7 ነዋሪዎች ‹‹ለፓርላማ ፕሮጀክት ማስፋፊያ›› በሚል በመስተዳድሩ ‹‹ከፋሲካ ማግስት በኋላ ተነሱ›› በመባላቸው እጅግ አደገኛ እና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለፍትሕ ገለፁ። እንደነዋሪዎቹ ገለፃ ከሆነ ልማቱን በደስታ ቢደግፉትም ልጆች ትምህርታቸውን ሳያጠናቅቁ መስተዳደሩ አባላት ከአውደ ዓመት በኋላ ‹‹ትነሳላችሁ›› መባላቸው ትልቅ ስጋትና ድንጋጤ ውስጥ እንደከተታቸው በሀዘኔታ ተናግረዋል።

የአብዛኛው ነዋሪዎች ውሳኔና አስተያየት ተመሳሳይ እንደሆነ ለፍትህ የገለፁት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ለሁለት ወር ያህል በሚኖሩበት ቦታ ሆነው የልጆቻቸው ትምህርት እስኪጠናቀቅ ይፈልጋሉ። ጉዳዩን አስመልክቶ የአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 8 ጽ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ ደሳለኝ ደበሌን በስልክ ስናነጋግራቸው በመጀመሪያ ‹‹ቅሬታ ስላቀረቡት ነዋሪዎች በቂ መረጃ ይዛችሁ ኑ›› የሚል ምላሽ ሰጥተውን ነበር። ከዚያም ኃላፊው ቢሮ በአካል በመሄድ ምላሻቸውን እንዲሰጡን ብንሞክርም ከቢሮ ለአስቸኳይ ስራ መውጣታቸውን በመግለፅ በስልክ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

No comments:

Post a Comment