Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, April 20, 2012

አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት አሀዝ ከግማሽ በላይ አወረደው

ኢሳት ዜና:-
የአለም የገንዘብ ተቋም በመህጻረ ቃሉ አይኤም ኤፍ ኢትዮጵያ በያዝነው አመት 5 በመቶ እድገት እንደምታስመዘገብ ሲገልጽ፣ በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከኢትዮጵያ የተሻለ እድገት እንደሚያስመዘግቡ ገልጧል። ምንም እንኳ አቶ መለስ በፓርላማ ንግግር ታሪካቸው ተገኝተው ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህን አመት የኢትዮጵያ እድገት ሳይናገሩ ቢወጡም፣ የመንግስቱ መገናኛ ብዙሀን ግን አሁንም ኢትዮጵያ 11 በመቶ እድገት በማስመዝገብ፣ በአፍሪካ ፈጣን እድገት ያስመዘገበች ብቸኛ አገር እንደሆነች አድርገው ፕሮፓጋንዳ መስራታቸውን ቀጥለዋል። አይ ኤም ኤፍ በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ የዚህ አመት እድገት 5 በመቶ ይሆናል ብሎአል።

አይ ኤም ኤፍ ያወጣው ሪፖርት የመለስ መንግስት የዘንድሮውን ጨምሮ በሚቀጥሉት 5 አመታት አስመዘግበዋለሁ ከሚለው ከ11 እስከ 14 በመቶ ጋር ሲነጻጸር ከግማሽም በታች ነው። የአቶ መለስ መንግስት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አገሪቱ በሚቀጥሉት አምስት አመታት 14 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ ይተነብያል። እንደ አይ ኤም ኤፍ ሪፖርት ከ5 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ያሚያመዘግቡት አገሮች ናይጀሪያ፣ አንጎላ፣ ጋቦን፣ ጃድ፣ ጋና ፣ ኮትዲቫር እና ቻድ፣ ታንዛኒያ፣ ኮንጎና ሞዛምቢክ ናቸው።


No comments:

Post a Comment