Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, July 7, 2013

የሰብአዊ መብት ረገጣንና ኢትዮጲያዊውያንን በገዛ ሀገራቸው የዜግነት መብት ያሳጣውን ዘረኛ ሥርዓት በጽኑ እየታገልን አባይም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሚጠቅም መልኩ ይገደባል።


አገራችን በዓባይና በመጋቢ ወንዞች ላይ ግድብ ለመሥራት ሙከራ ስታደርግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። 1959 / (..) በግብፅና በሱዳን መሃል በተናጠል የተደረገውን ስምምነት በመቃወም አስር ሚሊዮን ዶላር በመመደብና በአሜሪካ ሙያተኞች አማካኝነት አያሌ ግድቦችን ለመገንባትና የውሃ ሃብቷን ለመስኖ አገልግሎት ለመጠቀም 1964 / (..) ጥናቶችን ማጠናቀቋን መጥቀስ ይቻላል።

የዚህን ዓይነት ብሔራዊ ጉዳይ ለማስፈጸም ወያኔ ብቻውን አመራሩን ጨብጦ በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ያለነውን ዜጎች በማስገደድም ይሁን በማታለል ገንዘባችንን ለመሰብሰብ ሲነሳሳ እኛም እንደ ዜጋ ይህ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሙሉ መብቱ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠብቆና ተከብሮ በአገሩ ኮርቶ በፈቃደኝነትና በደስታ የሚሳተፍበት እንዲሆን እንፈልጋለን።

Saturday, May 11, 2013

ሚኒስተር መላኩ ፈንታ በሙስና ተጠርጥረው ታሠሩ

 ሚኒስተር መላኩ ፈንታ በሙስና ተጠርጥረው ታሠሩ [የመግለጫው ሙሉ ቃል]: ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የፌዴራል የስነ ምግባር ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠ የዜና መግለጫ በዛሬው እለት የፌዴራል የስነ ምግባር ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚገኙባቸውን 12 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
እንደሚታወቀው ሁሉ ኮሚሽኑ በህዝብና በመንግስት ንብረት ላይ የሚፈፀምን የሙስና ወንጀል ተከታትሎ አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብ ተጠርጣሪዎችን በህግ ፊት አቅርቦ በማስጠየቅ ሙስናን የመከላከልና የመቆጣጠር ሃላፊነት በአዋጅ የተሰጠዉ አካል ነው፡፡

Sunday, May 5, 2013

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ

“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት ቤንሻንጉል ክልል ያቀናሉ፡፡ 

“ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን እያፈረሰ የራሱን ይፈጥራል”

የመኢአድ ሊቀመንበር ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ስለገዢው ፓርቲ ምን ይላሉ?
  • “ከ97 ወዲህ ፍርሃት የተጠናወተው ፓርቲ ሆኗል”
  • “ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ሰላዮችን አሰማርቷል”
  • “ምርጫኮ የለም ፤ ያለተወዳዳሪ ምረጡኝ ይላል”
በአገራችን የምርጫ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጠው የ97 ምርጫ ቅንጅትን በከፍተኛ ደረጃ ይመሩ የነበሩት እና በአሁኑ ሰዓት የመኢአድ ሊቀመንበር የሆኑት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፤ መጽሐፍ ይጽፋሉ ተብሎ ከተጠበቀበት ጊዜ ዘግይተውም ቢሆን “ህይወቴና የፖለቲካ እርምጃዬ” የሚል መጽሐፍ ለንባብ ሊያበቁ ተቃርበዋል፡፡ መጽሐፉ 200 ገጽ ያለው ሲሆን ቀጣይነት አለውም ተብሏል። ኢ/ሩ በእንግሊዝኛም ሰፋ ያለ መጽሐፍ እየፃፉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በአዲሱ መጽሐፋቸው፣ በአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ከኢንጂነር ሃይሉ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች፡፡

Friday, May 3, 2013

ሦስት:- ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮእስካሁን ድረስ ያሳየነው ችሎታ የማጥፋት ወይም የማክሸፍ እንጂ አዲስ ነገርን ወይም አዲስ ሥርዓትን የመፍጠር አይደለም፤ በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ቢያንስ ሦስት የአስተዳደር ሀሳቦች መቅረባቸውን አውቃለሁ፤ አንዱ በአቶ ሀዲስ አለማየሁ፤ ሁለተኛው በኤንጂኒር-የሕግ ባለሙያ ደመቀ መታፈሪያ፣ ሦስተኛው የኔ ናቸው

አእምሮአቸውና ልባቸው በማርክሳዊ-ሌኒናዊ ጦር ተቀስፎ የተያዘባቸው ወጣቶች ሌላ ሀሳብን የማይሰሙበት ጊዜ ነበር፤ ማርክሳዊ-ሌኒናዊ ጥራዝ-ነጠቅነት ብቻ የሁሉም ዓይነት የእውቀት ምንጭ ብለው በጭፍን የሚያምኑ ወጣቶች በተለይም ከኢትዮጵያዊ የፈለቀ ሀሳብን ለማጥላላት ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን አይቆጥቡም ነበር፤ የሌኒን የጡት ልጆች እርስበርሳቸው ተፋጁና ያሸነፉት ዛሬም ከፋፍለው ይገዙናል፤ የት እንደሚያደርሱን ገና አላወቅንም።

ሁለት፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ: By መስፍን ወልደ ማርያምልክ ወያኔ/ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን መገናኛ ዘዴዎች ሁሉ ለአንድ የወያኔ ዓላማ ብቻ እንዲውል እንዳደረገው ኢሳትም የኢትዮጵያን ሕዝብ ለአንድ ቡድን ዓላማ ተገዢ ለማድረግ የታሰበ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ፤ እስቲ ማስረጃ ቁጠሩ ሲባሉ ከስሜትና ከጥርጣሬ በቀር ምንም ተጨባጭ ነገር አይወጣቸውም፤ የተለያዩ ቡድኖች፣ በትጥቅ ትግል ውስጥ ነን ከሚሉ ጀምሮ በሰላማዊ የፖሊቲካ ትግል ተወስነናል የሚሉና በተገኘው በማናቸውም መንገድ ወያኔ/ኢሕአዴግን እንታገላለን የሚሉ ሁሉ በኢሳት መድረክ እንዳገኙ ይታያል፤፤
 
ኢሳት የራሱ የፖሊቲካ እምነት የለውም፤ ወይም ሁሉንም የፖሊቲካ እምነቶች ይደግፋል ማለት ይቻል እንደሆነ አላውቅም፤ ዝም ብሎ እምነት የሌለው መድረክ ነው እንዳይባል ወያኔን ተቃዋሚነቱ ጎልቶ የወጣ ነው፤ ኢሳት የጸዳ የዴሞክራሲ መድረክ ነው ከተባለ ጸረ-ዴሞክራሲ አቅዋም ያላቸውን፣ ወያኔንም ጨምሮ ማስተናገድ የሚኖርበት ይመስለኛል፤ ይህ ግን ጎልቶ እየታየ አይደለም።

አንድ ፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ: By መስፍን ወልደ ማርያም

በአለፉት ሠላሳ ዓመታት በኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ እንደኢሳት (የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ) ያለ ኃይል የትኛውንም የኢትዮጵያ አገዛዝ አጋጥሞት አያውቅም፤ በመሠረቱ የኢሳት መሣሪያነት ከባህል ውጭ ቢሆንም የባህል ይዘት አለበት፤ ይህንን ወደኋላ አመለክታለሁ፤ ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ ታሪክ በመሠረቱ ሁሌም በኃይል ላይ ቆሞ በኃይል የሚሽከረከር ነው::  

በአለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ የመጡት አብዮተኞች ሁሉ ይህንን በመሠረታዊነት የመክሸፍ ምንጭ የሆነውን የጉልበት አምልኮት እንደዓላማም እንደመሣሪያም ይዘው የተነሡ ናቸው፤ ዛሬም ቢሆን ተሸናፊዎችም ሆኑ አሸናፊዎች አብዮተኞች የሚያወሩትና የሚጽፉት ከጉልበተኛነት ከረጢታቸው ሳይወጡ ጥፋታቸውን እንደልማት፣ አላዋቂነታቸውን እንደብልህነት በማድረግ ራሳቸውን አታልለው ሌላውን ለማታለል እየሞከሩ ነው::

የእነአንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ነገር በጠቅላይፍ/ቤት (ወሰንሰገድገብረኪዳን)

ሰበር ዜናውን ከስፍራው የዘገበው ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን፤ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የነበረውን የችሎት ሂደት በዝርዝር ዘግቧል። ከዚህ ቀጥሎ እናቀርባለን። 

“ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላ፣ ታሳዝነኛለች”
– አዝማሪ

 ሌሊት ሌሊት እንደ “ዳዊት ደጋሚ” ስለማመሽ ጠዋት ጠዋት ተጋድሜ ማርፈድ ልማዴ ነበር፡፡ ዛሬ ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 26 ቀን 2005 ዓም፣ ካለወትሮዬ በጠዋት ከዕንቅልፌ ተነሳሁ፡፡ እናም ወደ ጠቅላይ ፍ/ ቤት አመራሁ።ዕለቱን እያሰብኩ፡፡

! …… ከ ፍሰሓ ደስታ ጋር ማወዳደር ! ለምን? ……!በተወሰኑ ካድሬዎች (በትግርኛ) ተፅፎ የኣብርሃን ፅሑፎች ይቃወማሉ ተብለው ለታመነባቸው ፌስቡከኞችና ለህወሓት ኣባላት የተበተነው ፅሑፍ ኣይቸዋለሁ። ፍሬ ሓሳቡኣብርሃ ደስታ ልክ እንደነ ፍሰሃ ደስታ የራሱን ክብር ኣሳልፎ ለመስጠት፣ ቤተሰቡና ሀገሩ ለመሸጥ ከትግራይ ጠላቶች ኣብሮ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ተጋሩ ግን ……” የሚል መልእክት ኣለው:: ይሄንንግብረ መልስየተሰጠው ሰው በተግባሩ (በሰራው ስራ) እንጂ በዘር ሀረጉ፣ በሃይማኖታዊ እምነቱና ፖለቲካዊ ኣመለካከቱ ሊመዘን ኣይገባምየሚል መልእክት ያለው ሓሳብ በመፃፌ ነው።

ይሄንን ታድያ የኣንድ ህዝብ ክብር ኣሳልፎ መስጠት ኣይደለም። የሰው ክብር ያለው ሰው በመሆኑ ላይ ነው። ሰው እንደሰው መከበር ኣለበት፤ ሌላው ሁሉ የግል ጉዳይ ነው። እኔ የመሰለኝን ሓሳብ ስለፃፍኩና ሌሎችን ሰዎች (ማናቸውም ከትግራይ ወይ ኢትዮዽያ ወይ ኣውሮፓ ወይ የትም) የኔን ሓሳብ ቢጋሩ እንዴትክብርን ለሌሎች ኣሳልፎ  መስጠትሊባል ይችላል? እኔ ሀገር ለመሸጥ ኣልተነሳሁም።