Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, December 8, 2012

ቅዱስ ሲኖዶሱ ‘አቡነ መርቆርዮስ ቀደም ሲል በተወሰነላቸው መሠረት መመለስ ይችላሉ’ አለ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ በሰሜን አሜሪካው የሰላምና አንድነት ኰሚቴ አስተናጋጅነት፣ ፫ኛውን እርቀ-ድርድር ባለፈው ረቡዕ ዳላስ፣ ቴክሳስ ውስጥ መጀመራቸው፤ ለዚሁ ውይይት፣ ያዲሳባው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬ ልዑካን፣ የስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ ፬ ልዑካን እየተሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል። ምን ላይ ናቸው? እስካሁን የሰማንው ነገር የለም፣ ደውለን ለማግኘት ያደረግንው ጥረትም አልተሳካም።

Friday, December 7, 2012

የሹም-ሽሩ ምስጢርና ዋናው ጠቅላይ ሚኒስትር!

በሰሎሞን ተሰማ ጂ. (semnaworeq.blogspot.com)
EPRDF's election of three Deputy Prime Ministers1
New appointees

ባለፈው ሐሙስ በተደረገው የኢህአዴግ/ወያኔ የካቢኔ ሹም-ሽር ላይ በርካታ አስተያየቶች በመደመጥ ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም የበርካቶቹ አስተያየትና ትንተና እዚህ ግባ የማይባልና፣ በወያኔዎች አማርኛም “ውኃ የማይቋጥር” ሆኖ ስላገኘሁት፣ የኔን አስተውህሎት ላቀርብ ወደድኩ፡፡ 

በቅድሚያ ግን፣ በሀገር ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ ፖለቲካ ማኅበሮች/ፓርቲዎች መሪዎች እየተቀባበሉ የሚደጋግሙት ነገር ያው የተለመደውን ነው፤ “ሹመቱ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ አይደለም!” ምናምን የሚል ወቀሳ አይሉት ትችት፣ እንዲያው የንፉግና የፈሪ ጩኸት ነው፡፡ 

አስደንጋጭ መረጃዎች ፣- የማዕከላዊ ዘግናኝ ግፎችና ግፈኞቹ

ከዚህ በፊት ታማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮች ባገኘነው መረጃዎች ላይ ተመስርተን ባስነበብናቸው የተለያዩ ዘገባዎች ኮሚቴዎቻችንና ሌሎች ታሳሪ ወንድሞቻችን ላይ በማዕከላዊ የደረሰባቸውን ግፍና ሰቆቃ በመጠኑ ለማስቃኘት ሞክረናል፡፡ 

ዘወትር ሰላምን ሲሰብኩና መቻቻልን ሲያስተምሩ የኖሩትን ኮሚቴዎቻችንንና ዓሊሞቻችንን በግድ የሽብር ድርጊት ልትፈጽሙና ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ስትንቀሳቀሱ እንደነበር የሀሰት ቃል ስጡ በሚል አንድ ኢትዮጵያዊ የራሱ ወገን የሆነ ኢትዮጵያዊ ላይ ያደርሰዋል ተብሎ የማይታሰብ አረመኒያዊ ድርጊት ፈጽመውባቸዋል፡፡

የሰሞኑ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመትና ፖለቲካ

ከዋና ዋና የአፍሪቃ ቀንድ አጥኚዎችና ታዛቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት Rene Lefort የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ “መለስ ከመቃብራቸው እየገዙ ነው። ግን ይህ እስከመቼ ይዘልቅ ይሆን?” የሚል ጽሁፍ አውጥተዋል።
 
Rene Lefort ለአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ኃላፊ ፒተር ሃይን ላይን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሰሞኑን የተሰጠውን ሶስት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ይገመግማሉ። በአስተዳደሩ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች እንደገና የመንግሥቱን ስልጣን እየተቆጣጠሩ ናቸው ያሉትንም ያብራራሉ። ስለሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ዕድገት አሃዝና የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ አንድምታ በተመለከተ አውስተዋል።

Thursday, December 6, 2012

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ደብዳቤ ጻፉ

  •  “የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ” ደብዳቤውን እንዲያውቁት የተባሉት መስሪያ ቤቶች
  •  ከስልጣኔ ውጪ ነው ያደረኩት ፤ በችኮላ የተጻፈ ደብዳቤ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ፤ በስሜትና በችኮላ የሆነ ነገር ነው ፤ ስለ ሰራሁት ስህተት አቡነ ናትናኤል ይቅርታ አድርጌልሃለሁ ብለውኛል” ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ
  •  “ይህ የእናንተ ጉዳይ አይደለም አያገባችሁም” አቃቢ መንበር አቡነ ናትናኤል
(አንድ አድርገን ህዳር 27 2005 ዓ.ም)፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አራተኛ ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ ከነሙሉ ክብራቸውና ማዕረጋቸው ወደቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ የሚጋብዝ ከኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ደብዳቤ መጻፉ ተሰማ፡፡ 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች መካከል ቀኖና ተጣሰ በሚል ምክንያት በሁለቱ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት በሰሜን አሜሪካው የሰላም ኮሚቴው አስተባባሪነት ሶስተኛውን የእርቀ ሰላም ድርድር ረቡዕ ህዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ዳላስ ውስጥ መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ለዚህው እርቀ ሰላም ጉባኤ ከአዲስ አበባው  ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ አባል፣ ፫ኛ/ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ አባል ፬ኛ/ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ በጸሐፊነት  የተወከሉ ሲሆን ከአሜሪካው ሲኖዶስ ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አባል፣ ፫ኛ/ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አባል ፬ኛ/ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በጸሐፊነት ተወክለዋል፡፡ 

Tuesday, December 4, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ የካቢኔ አደረጃጀት እያነጋገረ ነው

 -    ካቢኔው በሕገ መንግሥቱ መሠረት አንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ይኖረዋል
-    የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ያላቸው ሁለት ባለሥልጣናት ተሹመዋል
-    አዲሱ አደረጃጀት ከሌሎች ሕጐች ጋር ተቃርኖ አለው እየተባለ ነው 

በዮሐንስ አንበርብር
የሥራ አስፈጻሚውን ከፍተኛ ሥልጣን በማግኘት አገሪቱን መምራት ከጀመሩ ሁለት ወራት ከቀናት ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ ካቢኔያቸውን በአዲስ መልክ እንዳደራጁ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም መሠረት የሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችንና የሌሎች ሚኒስትሮችን ሹመት አፀድቀዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ የካቢኔ አደረጃጀትም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ካቢኔ) በሕገ መንግሥቱና በመመሥረቻ አዋጁ የተጣለበትን ኃላፊነቶች በብቃት ለመወጣትና የአስፈጻሚነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ለማድረግ፣ እንደ አዲስ በሦስት ዘርፎች መዋቀሩ አስፈላጊ መሆኑን ለፓርላማው አስታውቀዋል፡፡