Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, February 19, 2013

ኢህአዴግ ከምርጫ በፊት ለአዲስ አበባ ከንቲባ መሰየሙ ተጠቆመ

የምርጫ ምህዳሩን በማጥበብ ብቻውን ለአዲስ አበባ ምክር ቤትና ለአካባቢ ምርጫ የተዘጋጀው ኢህአዴግ የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮችን መመደቡንና ካንቲባም በስውር እንደሾመ ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት የዜና ምንጮች አስታወቁ፡፡ ወ/ሮ ሀዜብ መስፍንም አዲስ አበባ ላይ ይወዳደራሉ፡፡

የዜና ምንጮቻች እንደሚናገሩት ኢህአዴግ የመንገድ ትራንስፖርት ሚንስትሩ አቶ ድሪባ ኩማን በከንቲባነት፣ የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳንና የግብርና ሚንስትሩ አቶ ተፈራ ደርበውን በም/ከንቲባነት መድቧል፡፡